እነ መስሎ አደሮች!


  እነ መስሎ አደሮች !
 
   ከጋዜጠኛ ወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ
 
በትረ ስልጣኑን ለ28 አመታት ያለ ተቀናቃኝ ይዞ ሀገሪቱን በመምራት ላይ የሚገኘው የወያኔ/የኢሕአዲግ  መንግስት በፊት እሱን የሚቃወሙ ሁሉ  አንዴ ደርግ /ኢሠፓ እርዝራዦች ፤ ሌላ ጊዜ  የደርግ/ኢሠፓ  አፈቀላጤና 
ናፋቂዎች ፤ሌላ ጊዜ
ቦዜኔዎች ስብስብ ፤ሌላ ጊዜ የጫት ማህበር ስብስብ ፤ሌላ ጊዜ ሥራ ፈቶች ወዘተ ብላ ብላ ..እያለ እያለ የነፃው ፕሬስ  አባላትንና
ተቃዋሚ የሆነውን በሙሉ ያለግብራችን ተለጠፊ ታፔላ  ሲሰጠን ቆይቷል።
  መቼም ውጭ ሀገር ሆኖ መጻፍና ማውራት ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ ከሚጽፈው ጋር በሚዛን ቢለካ ልዩነቱ ከፍተኛ በመሆኑ እንደ ሽንታም   ስለሚያስቆጥር 
ውጪ ሆኖ መጻፍን አልፈለኩትም ነበር... ተሳሳትኩ?... ጁቡቲን እረግጦ የማያውቅ ሁሉ በቦታው ተገኝቶ ያየ ይመስል " ተወው እባክ እሱ ድራፍቱን እየጠጣ፤ እየተዝናና ... ነው ሥራ ፈት ሆኖ የሚቸከችከው..." የሚሉ የወሬ አቅማዳ ተሸክመው የሚዞሩ ለሆዳቸው ያደሩ ። እነ መስሎ አደሮች ወይንም በሌላ አነጋገርየእነ አጋሰሶች የቡና መጠጫ ነው የምንሆነው 
  ደግሞ እኮአሁን  የፕሬስ መብት ተከራካሪዎችም ለኢትዮጵያ ያላቸውን አድናቆት እየገለጹልንአይደል ?ካካካካ... መቼም አድናቆት ከተገለጸ አይቀር እንደው እስካለው ድረስበፊት ብሎጌ ላይ አሁን ደግሞ መጽሔት ላይ ጦማሪ ሆኜ መቀጠልንመርጫለው    ..ተሳሳትኩ ጎበዝ!…
  እንደኔ አይነቱ ክርስቲያን ደግሞ መቼም ውሸት
 አያምረበትም ! 
 ደግሞ እኮ መሪያችን ክቡር 
ዶክተር ጠቅላይ ሚኒስትር...
., ክርስቲያን አይደሉ ! ያውም ፕሮቴስታንት ... ?..በዚህ ላይ ንግግር ሲያደርጉ መጨረሻ በምርቃት ነው የሚያጠናቅቁት..
«እግዚአብሔር
ኢትዮጵያንና  ሕዝቦቿን ይባርክ »... ይህ ደግሞ ደስ የሚል ከአባቶች ያልተናነሰ «  ይበል ..!» የሚያሰኝ ምርቃት ነው።  
አማራ የሆነውንም ያልሆነውንም 
 ብቻ  ነፍጠኛ የሚለው ስም ተቀይሮ አሁን ደግሞ ለፕሬሱ አባላቶች ሌላ ታፔላ መስጠ ቱግን ትንሽ ከፍቶኛል...
 ነፍጥ እኔ የማውቀው በጥንት ጊዜ አባቶች ይይዙት ከነበረው እንደ ውጅግራ አይነት...መሳሪያ ወይንም ተዋጊ ጦረኛ …ማለት ነው ?…በሬና በግ በቀንዱ  ይዋጋል እኛ በምን ነው የምንዋጋው?...ከእነሱስ በምን እንለያለን ብዬ ነው!...
።በዚህ ሂድ እሺ!ተመለስ እሺ! እረፍ እሺ!ና ወደዚህ እሺ! እምቢ ብለን መች እናውቃለን...ካካካ..
 በዚህ ላይ…«የአጼ ናፋቂዎች …»  ተብለናል
በምን ሂሳብ ስሌት ነው ? ..በጣም የሚገርመው   የወያኔ/ኢሕአዲግ  መንግስት ይህን ስም የሰጠን.," የስልጣን ለወጥ ! እንጂ  የፖለቲካ ወይንም የድርጅት ለውጥ  አላይንም...! " ስላለን ነው ?
የወያኔ መሪ የነበሩትና ከጫካ በመምጣት ስልጣኑን በጡቻ ሲመሩ የነበሩት ነፍሳቸውን ይማረውና አቶ መለስ ዜናዊ ምንም እንኳ ጨቃኝና አረመኔ ቢሆኑም ከኢህ አዲግ አባላትና ደጋፊዎች በስተቀር ሰው ሁሉ እንኳን ቢጠላቸው እኔ ግን..,ሌላውን ትቼ ጭንቅላታቸውን ብቻ 
አደንቀው ነበር።.... እንዴት ካላችሁኝ? ከጫካ ሲመጡ በዚህ ላይ እንደተራበ አንበሳ አልሆኑም በዚህ ላይ ደግሞ… 
 ስለ ኢትዮጵያ ምንም ሂንቱ ስለሌላቸው ... ጎበዝ አንባቢም ጭምር
 ስለነበሩ የፕሬስ ነፃነት እንካችሁ ብለው ሰጡን ።
እኛ ስንቸከችክ..., እሳቸው ሲያነቡ..,! እኛ ስንቸከችክ እሳቸው ሲያነቡ.,,!  በድንብ ሲጠግቡና ስለ ሕዝቡ አመለካከት ሲያውቁ የፕሬስ ማነቆ በማድረገ ወደ እስር ይወረውሩን ጀመር ። እሳቸው አልተረዱትም እንጂ
ፕሬስ ይህን ያህል የሕዝብ ዓይንና ጆሮ ላካ ነበር እንድንል ቻልን!
። አሁንም ክብር ጠቅላይ ሚኒስትራችን 
ዶክተር አብይም ጋዜጠኞች የነበሩ እስረኞችን ፈቱልን ተመስገን አልን! …
 እንደፈለጋችሁ ጻፉ አሉ። አሁንም የማቱሳላ እድሜና ጤና ይስጣቸው  ብለን መረቅን!
በኋላ ላይ አሸባሪ እያሉ... ጋዜጠኞችን ዘብጥያ እያስለቀሙ ያስከትቱት ጀመር።
 ምነው ሲባሉ?  « ከጋዜጠኝነት ጋር የሚያያዝ ነገር የለም  ከመንፈቅለ መንግስት ጋር የሚያያዝ ሥራ ሲሰሩ ነው የተያዙት.." አሉን...!
 ግን እኮ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እንደው አፈር ስሆንሎት መፈንቅለ መንግስት የሚያደርገው መሳሪያ የታጠቀ እንጂ ብዕርና ወረቀት የታጠቀ ኃይል  ቢሆን ኖሮ መዋለ ዕፃናት የገቡትም እነ ማሙሽና ሚሚ ገና ብዕርና ወረቀት እንደ ጨበጡ ወይንም በኮልታፋ አንደበታቸው መሳደብ ሲጀምሩ እነሱንም አሸባሪ ብለን እንከታቸው ነበርአይደል?…ካካካ..
ልዩነቱ በእጻናቶችና በእኛ መካከል በቀለሙ የሚተላለፈው መልዕክት ላይ ነው !በዚህ ላይ…
.. የሞነጫጨሩትን የሚያሳዩት እነሱ ለቤተሰብ ወይ ለአስተማሪ ነው። እኛ ደግሞ አንጀቱ ለቆሰለ ሕዝብ ነው በቃ ይኸው ነው ልዩነቱ!
 ደግሞ እኮ መሳሪያ ይዞ የሚፅፍ የነፃ ፕሬስ ጋዜጠኛ የለም!  በዚህ ላይ ሀብት የለው! ንብረት የለው! እድሜ ልኩን እሱ ሀገር ሀገር...ሲል 
 የእሱ ጓደኞች የሆኑት  
« እነ መስሎ ነዋሪዎች »
ተተኩሰዋል እሱ ግን አሁንም  ሀገር ሀገር …እያለ ይኖራል..!  ደግሞ   እኮባይሆን በደርግ ጊዜ ሰርቶ አደር ጋዜጣ ላይ በዚህ መንግስት ደግሞ አብዮታዊ ዲሞክራሲ!…
(የኢህ አዲግ)  ወይንም የወይን …ልሳን ላይ ያሉትን ጋዜጠኞች ወይንም  በፊት ጀምሮ የምወዳት "ፖሊስና እርምጃው " ላይ የሚሰሩትን የፖሊስ ጋዜጠኞችን ከሆነ ያስኬዳል ! ደግሞ እኮ
እኛ መሳሪያ  የምንይዘው የትኛው ሀብታችን እንዳንነጠቅ ነው ? ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁ ጋዜጣ ታተመ ከተባለ 7 ሺህ ነው። መጽሔት ደግሞ ትልቁ ከሁለት ሺህ አይበልጥም ..በዚህ ላይ አብዛኛዎቹ ስፖንሰር የላቸው …እኛም ደግሞ
የምንጽፈው  የሱስ ነገር ሆኖብን ነው ይኽው 
 በደርግ ጊዜ ጀምሮ የተጠናወተን የብዕር ሱሰኝነት አለቅ ብሎን እንለዋለን! ደግሞ ለማጫጨር…ምንም የለንም ስለዚህ አይፍሩ።የፕሬስ ነፃነቱን እባኮት ለቀቅ ያድርጉት  እሺ!…
 መሳሪያ ቢኖረን ኖሮ ልክ እንደ ምንጽፈው «ዘራፍ ወንዱ ! የመይሳው ልጅ..»እንል ነበር ካካካ..እንደ በግ «እሽ ..!»እየተባለ ወደ እስር ቤት ሂድ ሲባል እንዴት ይሄድ ነብር ? «ሊበሏት ያሰቧትን...» እንደሚባለው ካልሆነ በስተቀር? ....
አቶ መለስ በዚህ ላይ አራድነት የሚባል ነገር በጭራሽ
 አይነካካቸውም ልክ እንደ መንግስቱ ኃይለማርያም «አብዮታዊ እናት ሀገር ወይም ሞት »እንደሚሉት እሳቸውም «ሕዝባዊ አርነት/ኢሕ አዲግ ወይም ሞት »  ብለው ነው የሚጓዙት ይህ ማለት በፓርቲያቸው ቀልድ የለም  ማለት ነው።
 ገና ከጫካ እንደመጡ .. ከጅምሩ  አይደለም የግል ጋዜጣ ላይ ብቻ ላይ ሳይሆን የመንግስት ልሳን የሆነው አዲስ ዘመን በ2ኛ ገጽ ላይ «ነፃ አስተያየት » የሚለው አምድ ላይ ሁሉም የተሰማውን ነገር በወቅቱ በደንብ   አድርጎ ይጽፍ እንደነበር አስታውሳለው...! ታዲያ ችግሩ  የመጣው እያደረ ሆነ እንጂ..! ፖለቲከኛውም በዛ መልኩ ይቃወም ስለነበር እውነትም በሀገራችን ዲሞክራሲ ፈነጠቀ ብለን ነበር ።
  አሁንም በዶክተር አብይ ጊዜ ያለው  የወያኔ/ኢሕአዲግ መንግስት ተመሳሳይ ጌም ነው ይዞልን የመጣው...!ልዩነቱ መፈክሩ ብቻ ነው «በፍቅር እንደመር!» የሚለው የመሪያችን መፈክር ጠዋት ማታ በየሚዲያው እንደ በቀቀን ማስተጋባት  ብቻ ነው!...
አንዱ እየበላ ሌላው እየተራበ እንዴት ፍቅርና መደመር ይኖራል?…
  ተቃዋሚ የነበሩትም በፍቅር ሳይሆን በአራድነት መደመራቸው ለምን ይሆን…?  ወያኔ
ከጫካ ልክ እንደገባ  የሽግግር መንግስት ብሎ ሀገሪቱን ይመራ እንደነበረው አይነት መሆኑ ነው ።ታዲያ አቶ መለስ በዛን ወቅት ልክ እንደ ዶክተር አብይ በዓለም አቀፍ ደረጃ በብዙ መልኩ ተቀባይነት ያገኙበት ወቅት ነበር።
   ዶክተር አብይ ስልጣናቸውን ከመረከባቸው በፊት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ገና ስልጣናቸውን በገዛ ፍቃቸው መልቀቃቸው እንደተሰማ  ይኽው   መንግስት «..አቶ ኃይለማያም ከአላፊነታቸው የለቀቁት በግፊት እንደሆነ... እሳቸውን የሚተካው ከኦሮሚያ ክልል  የሚመረጥ ሰው እንደሆነ... ዋንኛው ምክንያት በኦሮሚያ ክልል በወቅቱ የተፈጠረውን ብጥብጥ ለማርገ
ብ ሲባል  እንደሆነ.... እስካሁን 
የሀገሪቱን የመሪነት ሚና  ተሰጥቶን አያውቅም....   ለእኛ ክልል ሊሰጥ ይገባል » የሚል አመለካከት ይዘው በወቅቱ  መነሳታቸውን
በሶሻል ሚዲያዎች ላይ ማንበቤን አስታውሳለው? ምን ያህል እውነትነት እንዳለው ባላረጋግጥም  ....!
 እንደተባለው የኦሮሚያ ምክትል መስተዳድር በመሆን ኃላፊ የነበሩትና አሁን የመከላከያ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ለማ የምክርቤት ኃላፊ ስላልሆኑ የምክርቤት አባል የሆኑት ዶክተር አብይ የአቶ ኃይለማርያምን ቦታ ሊይዙ በቅተዋል። 
   አቶ ለማ  ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ እንዲመጣ ያደረጉ ከስልጣን ይልቅ በኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ እንዲሰፍን የሚፈልጉ መሆናቸውን  ይህንንም በመንተርስ ስልጣናቸውን ለዶክተር አብይ አሳልፈው በመስጠታቸው በአብዛኛው ኅብረተሰብ ዘንድ የልጅ አዋቂ ተብለው አድናቆት የተቸራቸው  ባለስልጣን  ናቸው  ተብሏል ።እውነትነት ካለው ይበል የሚያሰኝ ነው። የቀብሌ ተመራጭ ለመሆን የማይፈነቀልበት ሀገር ውስጥ በምንኖርበት በዚች ምስጊን ሀገር ውስጥ ትልቅ ስልጣን «አልፈልግም» የሚል ሰው ሲገኝ ደስ አይልም ትላላችሁ? ያውም እኮ በሰው ላይ ክፋትና ተንኮል በሚሰራበት በዚች ሀገር አንደዚህ አይነት ቅን ሰው ሲገኝ ከሰማይ እንደ ወረደ መላዕክት አድርገን ነው የምንቆጥረው!...ምናልባት ከተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ከአቶ ኃይለማርያም ጋር እንደ ጃፓኖቹ አባባል በደም አይነት ይመሳሰሉ ይሆናል?... በአንድ ወቅት የጀፓን የፍትሕ ሚኒስትር የነበሩት ስልጣናቸውን ለቀው ለምን ለቀቁ ሲባሉ «የደም አይነቴ ቢ(B) ስለሆነ ....መስማማት አልቻልኩም ...» በሚል ሁኔታ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን አስታውሳለሁ።
 
  በእርግጥ አቶ ለማ በሚዲያ ቀርበው ሲጠየቁ የሰማውት ነገር አለ.. ይኽውም 
ለውጡን ያመጣው የኦሮሞ ብሔር ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ  እንደሆነ..አዲስ አበባ (ፊንፊኔ) የኦሮሞ ተወላጆች እንደሚሉት የእነሱ ከተማ ብቻ  እንዳልሆነች...
 የመላው ኢትዮጵያዊ  እንደሆነ ..አብዛኛው
  የሚወራው ወሬ ውሸት እንደሆነ የአሉባልታ አመለካከትን የቀለበሱና ያስቀለበሱ !  አዲስ አበባ የመላው ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳትሆን እንዲያውም  የአፍሪካውያን ጭምር ከተማ መሆኗን ሁሉም ተከባብሮና  ተፈቃቅሮ የምንኖርባት  ከተማ እንደሆነች በወቅቱ በመንግስት የመገናኛ ብዙሐን መግለጻቸውን አስታውሳለሁ። ይህ ብቻ አይደለም በተቀዋሚው ኦነግ ጋር በነበረው ድርድር ላይም ትልቁን ሚና የተጫወቱት አቶ ለማ ነበሩ ።በመሆኑም ለአቶ ለማ
ያለኝ አክብሮት ከፍ ያለ ነው!
 ምንም እንኳን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትርና አቶ ለማ የ የወያኔ/ኢሕአዲግ  መንግስት አባል ቢሆኑም አመለካከታቸውና አስተሳሰባቸው ከድርጅታቸው ለየት ያለ  አስተሳሰብ ያላቸው ናቸው። እናም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትርናአቶ ለማ ከወያኔ/ኢሕአዲግ አባልነታቸው  በስተቀር በአብዛኛው ተቀባይነት ያገኙ   ባለስልጣን
ናቸው ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም።በዚህ ላይ
ተመስገን ነው!..እድሜ ለእነሱ !..ይቺንስ የምንተነፍሰው እነሱና የስራ ባልደረቦቻቸው ባመጡት  ለውጥ አይደል?...,
  ..., አንድ ብዙ የታሰረ ...ከወ/ሮ ብሩቱካን ሚዴቅሳ ጋር በደንብ
ቀረቤታ ያለው ጋዜጠኛ  ስለ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን... 
እኔን አግኝቶኝ የተናገረው ነገር እስካሁን ይገርመኛል።
 እኛም ጋዜጠኞች ጋርም ችግር አለ? ለምን አይሉኝም አሁንም ጭምር መስሎ አዳሪ ጋዜጠኞች በመንግስት ሚዲያ ላይ አሉ ፤ አዕይምሮ የተባለችው ጋዜጣ (አዲስ አበባ ኬኔዲ ወይንም ወመዘክር(ቤተመዛግብትና ቤተመጽሐፍት ላይብረሪ ይገኛል) መውጣት ከጀመረችበት ከቀዳማዊ ኃይለስላሴ ጀምሮ  እስካሁን እስካለው የመንግስት ሚዲያዎች ላይ አዲስ ዘመንን ጨምሮ የሚጻፉት ጽሑፎች ለመጣው መሪ ሁሉ የሚሰግድና የሚያንቆለጳጵስ ነው።የአሁኑ የሚለየው የግል የተባሉትም መደመራቸው  ነው።ይህን እንድል ያስገደደኝ...አንድ የፕሬስ ጋዜጠኛ... ወ/ት ብርቱካን ከአሜሪካ ከመምጣታቸው በፊት ነው ....  ስለ ዶክተር አብይ ሲናገር «ሕዝብ ገርፎ ያሳደጋቸው ናቸው» ብሏል።እኔም ከሕዝቡ መካከል አንዱ ነኝ .. ዶክተር አብይን ስልጣን ላይ ከመውጣታቸው በፊት ስለማላውቃቸው ምን አልባት የሕዝብ ቆጠራው አምልጦኝ ስለነበረ ወዳጄን አልተከራከርኩትም   ....ሌላኛው የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኛ 
ደግሞ አቶ መለስ ባንዲራ ዘቅዝቀው የተነሱትን ፎቶ ጋዜጣዬ ላይ በማውጣቴ ጋዜጣ እንዳላሳትም  ተከለከልኩ
 ሲል ከቆየ በኋላ አሁን ደግሞ ዶክተር አብይ ስልጣን ከያዙ በኋላ «እኔ ስለማላጮህ መጽሔት አውጣ ተባልኩኝ» ብሎ ከልቤ በፊትለፊት ሳይሆን በሆዴ እንድስቅ አደረገኝ። በሰለጠነው ዓለም አንድ መሪ
የተዘቀዘቀ ባንዲራ አሲዞ ፎቶ ሞንታጅ አድርጎ አይደለም.... እንደ አሸባሪ ድርጅቶች ያሉ አይሲሲ... ሰውን ሲያርዱ! የሚያሳይ... ፎቶ ብቻ ሳይሆን አስገራሚ ቪዲዮ ሰርተው በዩቲዩብ (YouTube) ላይ
 ማየቴን አስታወሳለሁ። የገረመኝ የእሱ ሳይሆን «ስለማላጮህ » የሚለው አማርኛ አብዛኛው የግል ጋዜጠኛና አከፋፋይ ፕሪስ ውስጥ ገብቶ ሲያተራምሰን እንደቆየ የሚያሳይ ነው ። ማን ጮሆ ያውቃል?...ስለ ማላጮህ ከሆነ ያስኬዳል ።አንዳንዱ ከቨሩ ወይንም ርዕሱ ይጮህና ውስጡ ሲገባ የቀዘቀዘ  ወይም እንደበቀቀን ሌላው ላይ ያየነው ሀሳቦች ሊሆኑ ይችላሉ  … እነሱም እኮ አይፈረድባቸውም ...አንዳንድ አንባቢ ቤቱም ፤ ሥራ ቦታውም …እየጮኸና እየተጮኸበት ስለኖረ ከፍሬ ነገሩ ሳይሆን ከሚጮህ ነገር ነው የለመደው ። የጣራችን  ቆርቆሮ በኃይለኛ ዝናብ ሲመታ ጮክ ብለን ካላወራን ማን ሊሰማን …? ደግሞ ርዕስ እያጮህን ውስጡን  ባዶ አድርገን ያስተማርነው  እኛው
 የነፃው ፕሬስ አባላት አይደለን?
ስለዚህ እኔ ባልስማማበትም ይህን ሀሳብ...አሳታሚው ግን... አለ አይደል… ሀሳቡን ባልጨርሰው ይሻላል !...ታዲያ ጎበዝ አሁን ለዚህ ፕሬስ መስዋትነት የከፈልን 
 ጋዜጠኞች ከእነዚሀ መስሎ
አደሮች ጋር ጥቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት እንዴት በፍቅር እንደመር.? ወቸው ጉድ …!
   ....የኋላ የኋላ ደግሞ እኮ
ችግር በዶክተር አመራር ስር
መጣ እንጂ!
ዶክተር አብይን ምንም እንኳን  የወያኔ/ኢሕአዲግ  መንግስት ታማኝ በመሆናቸው ስልጣኑን እንድይዙ ድርጅቱ ቁልፉን ሚና የተጫወቱላቸው  ቢሆንም ስልጣኑን ከያዙ በኋላ የወሰዷቸው የሪፎርም  እርምጃ  ግን የሚያስሰግናቸው ሆኖ ነው ያገኘሁት። የታሰሩ ፖለቲከኞች፤የታሰሩ ጋዜጠኞች እንዲፈቱ አድርገዋል።የተዘጉ ብሎጎች ፤ድህረ ገጾች፣ጋዜጦች ወዘተ እንዲከፈቱ ማድረጋቸው።( በኋላ ላይ ካሜራ ማን የሆነውንም ጋዜጠኛ አሸባሪ እያሉ ከተቱ እንጂ)
ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ወደ ሀገር ቤት ገብተው ባዶ ስታዲዮም  ውስጥ የሚጫወቱ ቢሆንም የመጫወቻ ኳሱን ለተቃዋሚዎች ጎል አግቡ ብለው
 ሰጥተዋል። ሁለት የተነጣጠሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ኅይማኖት አባቶች አንድ እንዲሆኑአድርዋል፤ከኤርትራ ጋር የነበረው አለመግባባት በሰላማዊ  መንገድ እንዲፈታ አድርገዋል። አድርገዋል…አድርገዋል..ወዘተ.
  ዶክተር አብይ ይህን  ሁሉ እርምጃዎች የወሰዱት ወይንም ለውጥ  እንዲመጣ ያደረገው  በየትምህርት ቤቱና በየከተማው  የገዢውን ፓርቲ የሚቃወም በመብዛቱ ነው።