«የተጠለፈ ትግል» መጽሐፍ እንዳየሁት!


 
 ከጋዜጠኛ ወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ
ይህን ጽሑፍ የኢትዮጵያ መንግስትን በመፍራት ጋዜጦችም ሆኑ መጽሔቶች ማውጣት አልፈለጉም ምክንያቱም በዚህ መጽሐፍ አዘጋጁን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ታስረዋል።ከዚህ በፊት እስርን የማይፈሩት ሁሉ ለእውነት መታሰርን መፍራታቸው ከማሳዘን አልፎ የፕሬስ ነፃነት አለመኖሩን የሚያሳይ ነው።
  ውጭ ያለውም ሆነ ሀገር ውስጥ ያለው ህብረተሰብ ስለመጽሐፉ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ በማለት በድህረ ገጼ ላይና በብሎጌ ላይ እንካችሁ ብያለው መልካም ንባብ።
እንደምን ሰንበታችሁልኝ ውድ ወዳጆቼ ለዛሬው ልጫጭር የፈለኩት በአንድ መነጋገሪያ በሆነ መጽሐፍ ዙሪያ ነው።
አሁን እንደ በፊት  ብዙ መጽሐፍ አንባቢ እንኳን አይደለሁም በፊት ሌላ ነገር ከምገዛ መጽሐፍ እያደንኩ እየገዛው ወይንም ከገዙ ሰዎች ተወሼ የወጡትን ሁሉ መጸሐፍቶች አነብ ነበር። አዲስ አለማየሁ፣ባህሉ ግርማ፣ ብርሃኑ ዘሪሁን፣ማሞ ውድነህ፣ሲሳይ ወርቁ ወዘተ. የመሳሰሉ የምንወዳቸውና የምናከብራቸው ጸሐፍቶች የት አሉና? ሃያሲያንንም ስናይ፤ የምወዳቸውና የማከብራቸው ዛሬ በሕይወት የሌሉት ጋሽ መስፍን ሀብተማርያም ፣ ጋሽ እሸቱ(ዘለሌ ዘግንፍሌ )፣ጋሽ ስብሀት ፤ ጋሽ ሙልጌታ ሉሌ  በሕይወት ካሉት መካከል ዳንዴው ሰርቤሎ ከ6ኪሎ ፣
ጋሽ ጌታቸው (ዳግላስ ጴጥሮስ)፣አሸንፊ  ዘ ደቡቡ፣በስደት የሚኖረው ጋሽ ስንሻው፣ፕሮፌሰር ጌታቸው  ወዘተ. ያህል ጸሀፍቶች የት አሉንና?   በጫት ፈረስ በአብዛኛው ስለሚጻፍ እየመረጥኩ ካልሆነ በስተቀር ብዙም ለማንበብ ፍላጎቱ የለኝም።
 አንዱ ወዳጄ «የተጠለፈ ትግል » የሚለውን መጽሐፍ አነበብከው ወይ አለኝ? ይህን ያለኝ ያለምክንያት አይደለም ?ከጋዜጠኞች የመብት ተከራካሪዎች ጋር አልፎ አልፎ ስለምሰራ በዚህ መጽሐፍ ዙሪያ አንድ እንድልላቸው ስለፈለገ ይመስለኛል።
  ስለ መጽሐፉ አንዳንድ ነገሮችን ነገረኝ
 
  መጽሐፉ እየተፈለገ እንደሚቃጠል፤መጽሐፉን ያከፋፈለውና የመጽሐፉ አዘጋጅ እና ወንድሙ እንደተያዙ እንዲያውም ጊዮርጊስ የሚገኘው አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከሳሾቹ አብረው እየቀረቡ መሆኑን ሰማውና ጸሐፊው ምን ቢጽፍ ነው መጽሐፉን ያከፋፈለውና ወንድሙ ን ጨምሮ እንደዚህ ሊታሰሩ የቻሉት? የሚሉት ጥያቄዎች በአዕይምሮዬ ውስጥ ተመላለሰብኝ። እናም በዚህ ዙሪያ አንድ ለማለት ፈለኩ።
በመጽሐፍት አከፋፋዮች ዙሪያ
ዙሪያ ካለኝ ልምድ አንፃር የእኔንም ስድስት መጽሐፍቶች ስለ አከፋፈሉልኝና እየሸጡልኝ ስለሆነ ነው።
የመጽሐፍት አከፋፋዮች
ሁለት አይነቶች ናቸው ። አንደኛው አከፋፋዩ የሚፈልገውን ርዕስና አሳብ መርጦ ለምሳሌ የእንግሊዘኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሐፍቶች ወይንም የትርጉም ስራዎች አሊያም ሌሎችም መጽሀፍቶች ከሆነ የሚወጡት
ወጪውን ችሎ ከጸሐፊው ጋር እኩል የሚከፋፈልበት ሁኔታ አለ። ሌላው ጸሐፊው በገዛ ገንዘቡ አሳትሞ ለመጽሐፍ አከፋፋዩ ከሽያጩ ከ5እስከ 7 በመቶ በማሰብ እሱ ደግሞ ለመጽሐፍ ሻጮች መደብርጋር

መጽሐፉን ያከፋፈለውና በእስር የሚገኘው መጽሐፍት ቤት
ከ37-40 በመቶ በኮንሳይመንት ወይንም መጽሐፉን ሸጦ ከሽያጩ እስከ 40 በመቶ ወስዶ በየሶስት ወሩ ወይንም ከዛም በላይ ባሉት ወራት የተሸጡትን መጽሐፍ የሚያስረክቡበት ሁኔታ አለ። ከዚህ አንጻር መፅሐፍ አሳታሚዎች ከጥቅም አንፃር ነው መጽሐፍቶችን የሚሰሩት ማለት ይከብዳል።
በስኬታማ ቤተሰብና በሌሎች ማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሚያተኩረው ይህ የእኔ መጽሐፍም እንዳይሸጥ ተከልክሏል ግን ለምን? 
የንባብ ባህል በሌለበት ሀገር ውስጥ ገንዘብ ተፈልጎ
የሰውን ወቅታዊ ፍላጎት ተጠቅሞ መጽሐፍ መጻፍ ዋጋ የሚያስከፍልበት ሁኔታአሁን አሁንመኖሩን እያየን ነው።
 አንባብያኖቼ ይህን ያህል
ስለመጸሐፍት ሽያጭ
ግንዛቤ ከወሰዳችሁልኝ ወደ ተነሳሁበት አንኳር ነጥብ ልመለስ ። ከላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ይህ ብዙ ዋጋ አስከፈለ የተባለውን መጽሐፍ እንዲቃጠሉ፣እንዲቀሙ፤ግለሰቦቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ እርምጃ እየተወሰደ ነው ያለው  ይህ ለምን ይሆናል ? ብዬ
ሕግ አስከባሪውን  ወገን ላይ ከመደፍደፌ  በፊት መጽሐፉን ማንበብ እንዳለብኝ ስለተረዳው አንዱን ወዳጄን መጽሐፉን እንዲፈልግልኝ  ጠየኩት። እሱም እሺታውን ገልጾልኝ ከሰዎች ጋር አፈላልጎ በእጄ እንዲገባ ስላደረገልኝ
በአንባብያኖቼ ስም ከልብ አመሰግናለው ።

የመጽሐፉ ርዕስ
«የተጠለፈ ትግል » ይባላል።
ደራሲ መድህን ሲራጅ
መጽሐፉ የታተመው ሐምሌ 2011 ዓ.ም   ይላል። መጽሐፉን ማንበብ ስጀምር «መታሰቢያ » የሚለው ላይ የሰፈረው አርፍተ ነገር ገና ከጅምሩ ያዘኝ ።
«መታሰቢያነቱ ከሁለት ሶስት አመታት በፊት በነበረው ህዝባዊ ትግል ላይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነት ብለው ለተሰው አገር ወዳድ ዜጎቻችን በመሉ ይሁንልኝ » የሚል ቃል ሰፍሮ ይገኛል።
መጽሐፉ የታተመው ሐምሌ 2011 ዓ.ም  ነው።
ምንም እንኳን ውጪ ብኖርም ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር የጀመርኩት ሁለት አመት አካባቢ በመሆኑ እስካለው ድረስ በዚህ ሁለትና ሶስት አመታት በርካታ ሰዎች የሞቱት «ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነት ብለው የሞቱ » የተባለው ሁኔታ
በተለይም
ከባዕድ ወራሪ ጋር ሲፋለሙ የተሰዉ  ሰዎችንስላላየው
ጥያቄ ምልክት አድርጌ ንባቤን ቀጠልኩ።
ምክንያቱም አብዛኛዎቹ የወያኔ መንግስት የዛራው የዘረኝነት ፖለቲካ አድጎ በርካቶችን ከቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉና እንዲሞቱ ማድረጉን ነው የማውቀው።እዚህ ላይ ትዝብቴን አቆየውና ወደ ሌላኛው ፍሬ ነገር ማምራቴን ቀጠልኩ ።
በነገራችን ላይ በመጽሐፉ
ውስጥ የተጠቀሱትን የሰዎችን ስም የጋዜጠኝነቱ ኢቲክስ ስለሚገድበኝ ክፍት አድርጌ በማለፍ በተነሱት አላስፈላጊ ባልኳቸው ነጥቦች ላይ ብቻ
አተኩሪያለው።በዚህ ላይ ደግሞ
የሰው ስምን ያለአግባብና ያለ ማስረጃ መጥቀስ አይደለም በኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃም ያስጠይቃል። ፈረንጆቹ ይህን Defamation ወይንም የስም ማጥፋት ዘመቻ ይሉታል።ስለዚህ የሶዎቹን ስም ማንሳቱን አልፈለኩትም።ከዚህ ሌላ በሩቅ ምሥራቅ ፍልስፍናና አስተምሮት ላይ በመመርኮዝ ዝም ብዬ በጨበጣ አስተያየቴን
መስጠት ሳይሆን ፋክትን፣ሪያሊቲንና ሎጅክን ተመርኩዤ ነው ትንተናውን ለመስጠት የሞከርኩት።ይህ ማለት የማንም ወገንተኛ ስልሆን በተቻለኝ አቅም
 አስተያየቱን ሚዛናዊ ለማድረግ ሞክሬያለው።
በእርግጥ በሕዝብ ዓይንና ጆሮ የሚሰሙና የሚታዩ በርካታ የተነሱ ነጥቦች አሉ ፤ የተወሩ ሁሉ እውነት ናቸው ብሎ መደምደም ባይቻልም ጽሐፊው የጻፈበት የራሱ ምክንያት ሊኖረው ስለሚቻል በርካታ መነሳት ሊኖርባቸው ይችላሉ ያልኳቸውን ነጥቦችና ጥያቄዎች
ለጊዜው አልፌአቸዋለሁ።
በመጽሐፉ ውስጥ የተገለጹ አብዛኛዎቹ በማስረጃ የተደገፉ ባለመሆናቸው ተአማኒነት ይጎላቸዋል።
እስቲ አንዳንዶቹን ለአብነት
እናንሳ
በተራ ቁጥር 2 ገፅ 11 ላይ የሰፈረውን ስንመለከት
«…የመግቢያ ውጤት ማማጣት … አቶ እከሌ (የኦሮሚያ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበረና በኋላ በእሳቸው ሚስጥር ያወጣብኛል በሚል ሰበብ ሆን ተብሎ በመኪና አደጋ ሕይወቱእንዲያልፍ የተደረገ ።
ማትሪክ ተፈትኖላቸው ሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲ ገብተው ሀግ እንዲማሩ… » እያለ ይቀጥላል። መቼም ማትሪክን የወሰድን ሰዎች ልክ እንደ
Identical Twice ከአንድ የሴት እንቁላል ለሁለት ተከፍሎ ከተወለዱ መንትያ  ወንድማማቾች ወይንም አህትማማቾች ካልሆንን በስተቀር ተፈታኝ ያልሆነ ሰው የመፈተኛ ወረቀት ሳይዝ ወይንም ይዞ በሰው ስም ይፈተናል ማለት ይከብዳል ። ይህ በእኔ እምነት ተአማኒነት ያንሰዋልባይ ነኝ። ሌላው  «..በዋሽንገተን ዲሲ የብዙ ቤቶች ባለቤት..
»እንዲሁም በተራ ቁጥር 2 ገፅ 15  ላይ «…በአሜሪካና ካናዳ ቤት ገዝተዋል…» ጸሐፊው ይሉናል። መቼም ውጪ የምንኖር ሰዎች ቤት ለመግዛት አይደለም ለመከራየት እንኳን እንዴት እንደምንቸገር ስለምናውቅ አይደለም ብዙ ቤት አንድ ቤትም የአሜሪካና የካናዳ ዜግነት ሳይኖረው መግዛት በውጭ
አይደለም መኖር ለአንድ የኢትዮጵያ ባለስልጣን ያውም የኢትዮጵያ ዜግነት ላለው ሰው ይከብዳል። የኮርዲፕሎማንት ሰው እንኳን ቢሆን ቪዛው በኢምባሲው በኩልነው
ለመኖር የግድ ማሳደስ ግለሰቡ ግዴታ አለበት።
ከዚህ አንፃር ጽሑፉ ተአማኒነት ይጎለዋል።
በተራ ቁጥር 4 ከገፅ 19-20 ባለው ውስጥ
«...የዘውዳዊ ዘመን አስተዳደርን በማጉላት የፌድራሊዝም ስርዓቱን አስተዳደር ደግሞ በማንኳሰስ በሰፊው ለመዳሰስ ሞክሯል። በዚህም አሃዳዊ ስርዓት ለመመለስ ከሚዳክሩ አካላት አድናቆትን ብቻ ሳይሆን ክብርና እውቅናን ለማግኘት ችለዋል።...» በአሁኑ ወቅት የአደጉ ሀገሮች ከአረብ ሀገሮች በስተቀር የንጉሳዊ አስተዳደሮች ለሲምቦል ይህል አስቀምጠው ሌብራል፣ሪፓብሊካንና ዲሞክራት ወዘተ. ፓርቲዎች እየተባሉና እየተፎካከሩ ነው ሀገር ሲመሩ የሚታዩት ።ለምሳሌ ጃፓንን ማንሳት ይቻላል።
በንጉሥ የመመራቱ ሁኔታ በአብዛኛው መንግስታት ዘንድ
የቀረ ነው። ኢትዮጵያም ከደርግ ውድቀት በኋላ የንጉስ አስተዳደራዊ መንግስትን በተለይም በውጪና በጫካ ኢዲዮ በማለት ይንቀሳቀሱ የነበሩ የንጉሥ ናፋቂዎች ብለው! ብለው ! ያልቻሉትን ነገር
አንድ ተራ ግለሰብ ብቻውን እንደተባለው ፍላጎት እንኳን ቢኖረው ጸሐፊው እንዳሉት ለመተግበር እሞክራለሁ ቢል
ግለስቡ "ቁልቁለቱ ዳገት ነው የሚሆንበት"
«…ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት እንደመጣ 30 ሚሊዮን ብር ከማህበረ ቅዱሳን ሰብስበው በመስጠቱ ምን ያክል አቅም እንዳለውና ተፅዕኖ ፈጠሪ መሆኑን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አስመስክረዋል።በዚህም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ትኩረት መሳብ በመቻሉ አማካሪው ሆኖ ለመመረጥ ችለዋል።...»ይለናል ጸሀፊው ! ማህበረ ቅዱሳን የሚመራው የራሱ የሆነ ቦርድ አለው ከዛም አልፎ የበላይ ጠባቂ አለው።የባላይ ጠባቂው ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው። ከዚህም ሌላ ገንዘብ ከካዝና አሊያም ከባንክ ሲወጣ የራሱ የሆነ አሰራር አለው ፤አይደለም በሚሊዮን የሚቆጠር ብር በሺህ የሚቆጠር ብር ከአካውንታችን ስናወጣ የባንክ ደፍተር ወይንም መታወቂያ ካልያዝንና ፊርማችን መጀመሪያ ከፈረምነው ጋር ካልተመሳሰለ በስተቀር ብር ማውጣት አንችልም። ከዚህ አንፃር ያን ያህል ብር አንድ ግለሰብ እንዲሰጥ አደረገ ብሎ መጻፍ የባንክ ሂሳብ አሰራርን ለምናውቀው  ብቻ ሳይሆን ለማያውቁትም ሰዎች ጽሑፉ ተአማኒነት ስለሌለው ለማመን  ይከብዳል። «…ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጉብኝት ወደ ፈረንሳይ ሀገር ባመሩበት ጊዜ አንድ የግብረሰዶማዊያን ማህበር አባላቶች ኢትዮጵያን መጎብኘት እንደሚፈልጉ ገልጸፆውላቸው እርሳቸውም ፈቅደውላቸው ነበር።ይህንን ሚስጥር የሚያውቀው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የቅርብ ወዳጅና አማካሪ የሆነው...(እከሌ የተባለው ሰው ) ብቻ ነበር ።እርሱም ይህንን ሚስጥር አሳልፎ ለኦርቶዶክስ ሃይማኖት ማህበራት በመስጠቱ ማህበራቱ የግብረሰዶማውያንን  ጉዞ በመቃወም ሊያስቀሯቸው ችለዋል።...» ይሄ አባባል እውነት ከሆነ ግለሰቡን እንዲመሰገን ያደርገዋል እንጂ የሚያስወቅሰው አይደለም።እንዲያውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእርግጥ ፈቅደው ከሆነ ትልቅ ስእተት ነው የሰሩት። ማንም ግብረሰዶማውያን ሀገር ጎብኚ ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ ከየትም ሀገር ይገባል። እንደ አሜሪካ ባለች ሀገር ደግሞ ጋብቻ ሁሉ እስከመፍቀድ የደረሰችበት
ሁኔታ አለ።  በሀገራችንም ውስጥ በርካቶች እራሳቸውን ሸፍነው ከዚህ በፊት ገብተዋልም የሚገቡም አሉ።ይፋ አይሁን እንጂ ሀገራችን ውስጥም ግብረሰዶማውያን አለ።
ሆኖም. በግሩፕ ሆኖ ወደ ሀገር ውስጥ ይፋ አድርጎ መግባት ግን ካለን ባህልና ታሪክ አንፃር ሲታይ ግንድርጊቱ በዓለም አደባባይ እርቃናችንን ነው የሚያስቀረን ።
ጸሐፊው እንዳሉት ግለሰቡ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሚስጥር አሳልፈው በመስጠት ተቃውሞ አስነስቶ በአባቶች አማካይነት
እንዲቀር መደረጉ የሚደገፍ እንጂ የሚያስነቅፍ አይደለም።  በበኩሌ በአባባሉ በኢትዮጵያውነቴጭምርነው
እንዳፍርያደረገኝ።   የወያኔ መንግስት " አሳብን በነፃነት የመስጠት መብትመግለጽ ሰጥቻለው" ብሎ አሳባችንን በመግለጻችን ለእስር በተዳረግንበት በአንድ ወቅት በእስር ቤቶች አካባቢ ግብረሰዶማውያን ሌላውን እንዳይበክሉ ተብለው ተለይተው እንዲተኙ ይደረጉ እንደነበር አስታውሳለው። አሁን ማህበሩ ካልመጣ ብሎ መደስኮር ምን ይባላል።
  በተራ ቁጥር 4ገፅ 19-20 ባለው ላይ ጸሐፊው ስለአንድ ተዋቂ ሰው ሲጽፍ «…የኢህ አፓ ታጋይ ሆነው እያሉ ፓርቲውን በግልፅ ነቅፈዋል በሚል ክስ ለወራት ከታሰሩ በኋላ ወደ ሱዳን አመሩ…የሸገር ወጣቶችን በገንዘብ ገዝተው የግጭቱን መንሻ የኦነግ ደጋፊዎችን ለመተናኮል አደረጉ።ቀጥለውም በቄሮና በሸገር ወጣት መካከል የተፈጠረውን ግጭት እንደ ክፍተት ተጠቅመው ፤የሸገር ወጣቶችን በገንዘብ ገዝተውና  የጦር መሳሪያ አስታጥቀው በቡራዩ የሚኖሩ የጋሞ ሕዝብ እንዲፈናቀሉ አደረጉ።...» የሚል አለ። በመጀመሪያእንደተባለው ሰውየው ኢህአፓ ሳይሆኑ መኢሶን እንደነበሩ ነው ሲወራ የሰማሁት! ከዚህ ሌላ በጉራጌ ክልል ከጉራጌ ቤተሰብ እንደተወለዱ ነው የማውቀው። በተጨማሪ እሳቸው የሸገር ወጣቶችን ስለቀሰቀሱ አይደለም በቄሮ ላይ የአዲስ አበባ ሕዝብ የተነሳው ።
ለምሳሌ እኔ ያየሁትን ላንሳ የምኒልክን ሀውልት እናፈርሳለን ብለው የተነሱ ከወደ ሱሉልታ እየጨፈሩ የመጡ የኦሮሞ ወጣቶች (ቄሮ)
ሐውልቱን አልፈው ሲሄዱ የአዲስ አበባ ወጣቶች ዝም ብሎ ነበር ።በኋላ ላይ ግን ሐውልቱን ከበው አይሆኑ ነገሮችን እናደርጋለን ያሉትን እነዚህን የኦሮሞ ወገኖች ፖሊስ ዝምታን ሲመርጥ የአዲስ አበባ ወጣቶች አረንጓዴ፣ቢጫና ቀይ ባንዲራውን ይዞ በመውጣት «ምኒልክ የሞቱት ለዚች ለተቀደሰች ባንዲራ ነው » በማለት እንዳመጣጡ መለሱት ። በጣም የሚያሳዝነው ብጥብጥ ያስነሱት ሳይሆን «ሐውልቱ ታሪካዊ ነው ማንም ሊያፈርሰው አይገባም » በማለት የታገሉት የአዲስ አበባ ወጣቶች ነበር ለእስር የተዳረጉት። እናም ጽሐፊው የቄሮ ወጣቶችን ከደሙ ንጹ የአዲስ አበባ ወጣቶችን በአንድ ግለሰብ ተመርተው ለብጥብጥ መነሳታቸውን መግለጹ። በቦታው ተገኝተን በዓይናችን ላየነው ኢትዮጵያዊ  አሳዛኝ ሆኖ
ነው ያገኘሁት ።ሌላው ቀርቶ ተዋቂውን ድምጻዊ ቴዲ አፍሮን «... (በጉራጌነቱ የተመረጠ)አጫፋሪነት…» ብሎታል ጸሐፊው ። ቴዲ ጉራጌ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምን የልጅ አዋቂ የወገኑን ብሶትና ችግር በሙዚቃው የሚያቀነቅን ኩሩ ኢትዮጵያዊ እንጂ አጫፋሪ አይደለም። «..በአዲስ አበባ ጎዳናዎችም የዶክተር..መንግስት የሚቃወም ትልቅ ሰልፍ ተካሄደ...» የሚልም ሀሳብ አይቻለው። እኛ ያየነው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚደግፍ እንጂ የሚቃወም ሰልፍ እስካሁን አዲስ አበባ ውስጥ አላየንም «...የኢሳት ጋዜጠኞች ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ ትዕዛዝ ወስደው ያስባረሯቸው…»ጸሀፊው በማለትም አስቂኝ ሀሳብ አስፍሯል።
 እንደሚታወቀው ግንቦት 7 ኢሳት የኔነበር ብሎ ፓርቲው ከመክሰሙ በፊት ይፋ አድርጎ ነበር። እሱ እኔ እስከ ማውቀው አይደለም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርቲው  እራሱ ማንንም አላባረረም።እንዲያውም አብዛኛዎቹ በሁኔታው ተናደው እራሳቸውን ሲያገሉ ከፊሎቹ ደግሞ ለመቀጠል መስማማታቸውን ነው የማውቀው ።
 ከገፅ 29-31ካለው ውስጥ የገረመኝ ነገር ፀሐፊው በአንድ በኩል ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ ሆነው ይቀርባሉ። በሌላ በኩል ዘረኝነት የተጠናወታቸው ሆነው የቀረቡበትን ጽሑፍ እናገኛለን።  «...
በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ከኦህዲድ ይልቅ የሕዝብ ተወዳጅነት የነበረውን ኦነግን ለመወንጀልና ስሙን ጥላሸት ለመቀባት ታስቦ ነው…በእናትም በአባትም ኦሮሞ የሆኑትን ካድሬዎች በኦነግ አሳበው እንዲባረሩ አድርጓል። በምትካቸውም ከዚህ በተቃራኒ የኦሮሞ ሕዝብ ፍላጎት ደንታ የማይሰጣቸውንና  በደም ኦሮሞ ያልሆኑ ነገር ግን አፋን ኦሮሞን በሚችሉ ግለሰቦች ተክቶአቸዋል።...የኦህዲድ  ካድሬ ሆኖ ለማገልገልም ሆነ ለመሾም በደም ሙሉበሙሉ  ኦሮሞ አለመሆንና ብሔርተኛ (Nationalist)አለመሆን ዋንኛው መስፈርቶች ነበሩ። በነዚህ መስፈርቶች የዛኔ የመለመላቸው ወጠቶችም አሁን ተመሳሳይ ሁኔታ በመፈጣሩ የኦህዲድ/ኦዲፒን ስራአስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ እያጥለቀለቁ ይገኛሉ።…በ..ዘመንም በደም በሁለቱም በእናታቸውና በአባታቸው በኩል ኦሮሞ የሆኑና ብሔርተኛ ናቸው ተብለው የታመነባቸው የኦህዲድ/ኦዲፒ ከፍተኛ አመራር ከኃላፊነት ቦታቸው እየተገፈተሩ ይገኛሉ።…»ይሉናል። በእኔ እመነት ውጭ ወጥተው የሚኖሩ ጥምር ዜግነት ያላቸው ሰዎች "ሀገራችንን እንድናገለግል የኢትዮጵያዊነት ዜግነት ይሰጠን" እያሉ ጥያቄ በሚያቀርቡበት ወቅት በሌላ በኩል በሀገራችን ውስጥ የብሄር ፖለቲካ እንዲሰራፋ ጸሐፊው መጻፉ የሚያሳዝን ነው።
  ይህ ብቻ አይደልም ጸሐፊው በገፅ 36 ላይ
ባለፉት 28 አመታት ለእስር የተዳረጉት የኦሮሞ ተወላጆች ብቻ እንደሆኑና ሌሎች ለእስር እንዳልተዳረጉ እንዲህ በማለት ይገልጻል«...
 የእስር ቤቱ ወይም ተጋራፊዎች ቋንቋ አፋን ኦሮሞ የነበረው በህውሃት ፀጥታ ዘርፍ አመራር ጊዜ ነው።... » ይለናል።
የመጽሀፉ ጸሐፊ እሱ የሚያውቀው እኛ የማናውቀው የዛፍ ይሁን የጥንቁልና ኅይማኖትን  እንደሆነ ለማናውቀው አንባቢያኖቹ እንደ ትልቅ ኅይማኖት አድርጎም ያቀረበልን ሁኔታ አለ በገፅ 37 ላይ እንዲህ ብሎ ያውጋናል። «..የዋቄፋናና የፕሮቴስታንት ሀይማኖት መሪዎችና አባላቶች...»
  ጠቅላይ ሚኒስትሮቻን ከእቶ መለስ በስተቀር የፕሮቴስታንት ኅይማኖት ተከታዮች ናቸው። በዚህ ላይ ቤተክርስቲያን ሲቃጠል ፣የኅይማኖት አባቶች የተሰዉት በሱማሌ፣በኦሮሚያና በድቡብ ክልል የሰማነው የኦርቶዶክስ ኅይማኖት እንጂ ፀሀፊው እንዳለው የዋቄፋናና የፕሮቴስታንት ሀይማኖት መሪዎችና አባላቶች አይደለም ። እናም በማር ለውሶ እውነቱን ሸሽጎ ሀሰቱን እውነት አስመስሎ በመጸሀፉ ያቀረበበት ትራጀዲ ተእይንት ነው ማለት ይቻላል። በዚሁ መጽሐፍ ላይ በገፅ 37 ላይ «..ወንድሙ የተገደለበትና እህተቹ የተደፈሩት በቀድሞ...ነበር ..»የኦሮሞ ተወላጆች እንደሆኑ ይገልጻል። እኛ እስከምናውቀው በኦሮሞ ክልልና በደቡብ ክልል እንዲሁም በሱማሌና በአማራ ክልል ይህ አይነት ድርጊት የተፈፀመባቸው ጸሐፊው እንዳሉት ሳይሆን በመገናኛ ብዙሐን ባለፉት ሁለት አመታት እንደሰማነው የሌላው ብሔር ተወላጆች ናቸው።ጸሐፊው የራሱ ብሔር በአሁኑ ወቅት ስልጣኑን እየመራ እያለ በሌላ በኩል ጉዳት እየደረሰበት ነው ብሎ መደስኮሩ ሀገር ወዳድ ሳይሆን ብሔርተኝነት የተፀናወተው መሆኑን ያሳያል።
  ሌላው የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ላይ የተገለጸውን ጉዳይ እንዲሁም በፍርድሂደት እየታየ ያለን ጉዳይ በተመለከተ በተለይም
የቦምብ ፍንዳታውን
የገለጸበት ሁኔታ የተኅማኒነት ጉዳይ አለው ወይ ?ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል።
«…የሰኔ 16 የቦምብ ፍንዳታ በዋናነት ያቀነባበረና በብሔራዊ መረጃና ደህንነት ጽሕፈት ቤት የጸረ ሽብር ዳይሬክቶሬት የነበረው...እና የፌድራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነርና የብሔራዊ መረጃና ደሕንነት ጽሕፈት ቤት ምክትል ዳይሪክተር የነበረውን ቀድሞ ያጋለጡ እራሳቸው አብሯአቸው ሲገድሉ ሲያስሩ የነበሩ የእነሱ የሥራ ባልደረቦች የቅርብ ወዳጆቻቸው ጭምር የነበሩት ናቸው።...»ይለናል።
  ሌላው ፀሀፊው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት ፅሕፈት ቢሮን እንደሚመሩም ከገፅ 39-ገፅ 40 ሰፍሮ እናያለን «..የአሁኑ  የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት ፅሕፈት ቤት ከቀድሞው በህወአት ከሚመራው ተቋም ጋር በሁሉም ነገር ተመሳሳይ ነው። ልዩነቱ የአሁኑን በበላይነት የሚያዘው ኦህድድ መሆኑ ነው።ኦህድድ ለማለትም አይስደፍርም ፤በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ማለት ትክክለኛ ገለፃ ይሆናል።...»
«...በፓርቲ ሳይሆን እንደ ዘውዳዊው ዘመን በአንድ ግለሰብ ማለትም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የስልጣን ኃይል ብቻ መደራጀቱ ነው።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የፀጥታ ዘርፍ እራሳቸው እንደግለሰብ በራሳቸው ፍላጎት ሲያደራጁ ሲያራምዱ የሚፈልጉትን ስውር የፖለቲካ ፍላጎት መሰረት በማድረግ ነው። ይህ ስውር የፖለቲካ ፍላጎታቸውም የሚመነጨው ከሚያምኑበትና ከሚያራምዱት የዳግማዊ አፄ ሚኒልክ የፖለቲካ አካሄድ ነው።...»
አንድ መሪ ስልጣን ከያዘ ገና ሁለት አመት እንኳንሳይሞላው ሁሉም ጋር እጁን ከቶ ይዳክራል ብሎ መናገር  በእኔ እመነት የሚያስኬድ አይመስለኝም።
 ፀሐፊው የመገናኛ ብዙሐን በዶክተሩ ላይ እንደዘመቱና የቲም ለማ አባላቶች እንደታደጓቸው ከገፅ 46-47 የሰፈረው ሀሳብ ደግሞ ትንሽ ብልጣ ብልጥነት የታየበት አካሄድ እንደሆነ ያሳያል
«..እነዚህ በመንግስት መዋቅር ውስጥም ሆነ በውጪ ያሉ አካላት በአንድነት በእጃቸው የሚገኘውን መገናኛ ብዙኃንና ሁሉንም መንገድ ተጠቅመው ዶ/ር አብይ አህመድ ላይ ዘመቱ ።በዚህን ጊዜም ምንም የሚዲያ የበላይነት ባይኖራቸውም  ግን መላው የኦሮሞ ታጋዮች በአንድነት ቆመው እነዚህን ጠላቶች ሁሉ በቻሉት ሁሉ መከቱላቸው ።ጠቅላዩም  በዚህ ጫና ውስጥ ከቲም  ለማ ጋር በመሆን የተከመሩ በርካታ የፖለቲካ ችግሮችን ለመፍታት ቻሉ። ምንም የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄዎችና ፖለቲካዊ ፍላጎቶች አንዳቸውም ምላሽ ባያገኙ እንኳ።…» ይለናል።
እኔ እስከማውቀው ሚዲያው እንዳለ ለውጡን የሚደግፍና
ከዶክተር አብይ ጋር የቆመ መሆኑን ነው ያማውቀው ።ሌላው ነገር  የእሳቸውን አካሄድ የሚደግፈው እኔ እስከማውቀው የኦሮሞ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በዋንኛነት የአማራና የደቡብ ሕዝቦች ጭምሮ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም እኮ ስልጣኑን ያለደም ማፋሰስ ያስረከቡት ኦሮሞ ስለሆኑ አይደለም ። ምንም እንኳ ገዢው ፓርቲ ኢህአዲግ እና የመከላከያ ሰራዊት ስልጣኑን እንዲለቁ ቢፈልጉ እንኳን እሳቸው ፍቃደኛ ካልሆኑና «አለቅም ቢሉ!»ወደ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ድርጊቱ ስለሚሄድ በዓለም አቀፍ መድረክ በሀገሪቱ ላይ የሚመጣው ጫና ምን እንደሚሆን ከወዲሁ መገመት ይቻላል።
በዚህ ላይ ደግሞ የመከላከያ ኃይል በሰላማዊ መንገድ ስልጣኑ እንዲተላለፍ አድርጓል።በዚህ ላይ
አብዛኛው የሚመራው በትግሬ ብሔር በመሆኑ ህዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይም ለውጡን እነሱም ስለሚፈልጉ እንጂ በኃይል ስልጣኑን መቆናጠጥ አቅቷቸው አይደለም።እየተባለ ያለው ሁኔታ ወያኔ ስልጣኑን ለቋል ፤ከእንግዲህ ወዲያ አያንሰራራም ምናምንትሴ እየተባለ የሚነዛው ወሬ የፖለቲካ ቁማር ጨዋታ እንጂ ሌላ አይደለም።ምክንያቱም ከላይ ያለውን ቦታ አይያዙ እንጂ ቁልፍ ቦታዎችን አሁንም የያዙት እነሱ ናቸው።
  እኛ ሚዲያ ላይ የሰማነው ሌላ ጸሀፊው በሚዲያ ሰማውት ያሉት ደግሞ ሌላ ሆኖ ነው ያገኘሁት አንድ ምሳሌ ልጥቀስ በገፅ 52 ላይ የሰፈረውን እንመልከት
«..በለገ ጣፎ ዘርን መሰረት ያደረገ ማፈናቅል እየተፈፀመ ነው» በማለት የግል መገናኛ ብዙሃንን በማጥለቅለቁ ጉዳዩ በጣም ተራገበ። ...የተወሰኑት ሚዲያዎች የኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ..አንጋግሩ ህገወጥ ግንባታ ላይ እርምጃ መውሰድ የመንግስት አቋም በመሆኑ ዘመቻው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናገሩ።...ሁኔታዎችን እያዩ የሚገለባብጡ ጀማሪ ካድሬ ቢሆኑም።... »ብለውናል። ቤቶቹ የተሰሩት ከ12 አመት በፊት እንደነበረ የተሰራበት መሬትና ካርታ የሌላ አካል እንደሆነ ነው በሚዲያ ላይ የተገለፀው።ዋናው ነገር ቦታው የመንግስት ከሆነ ሰዉን ከቤቱ በማፍረስ ማፈናቀል ሳይሆን አስፈላጊውን ፎርማሊቲ አሟልተው በእዛው እንዲቀጥሉ ቢደረግ ይመረጣል ቢባል ያስኬዳል። ምክንያቱም መንግስት ለሕዝብ እስከ ቆመ ድረስ እራሱ ተጎጂ ሆኖ ባሉበት አካባቢ እንዲኖሩ ቢደረግ የመረጥ ነበር። ከአንድ መንግስት ሕዝብን ማንገለታት፤
ያለመኖሪያ አንድ
ቤተሰብን መበተን ፤አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን እርምጃው ኢፍታዊ መሆኑን ያሳያል። በተለይም በዚህ ቦታ የተጎዱት የሁሉም ብሔረሰብ ወገኖቻችን ናቸው ። እንጂ ፀሐፊው እንዳሉት የአንድ ብሔረሰብ አካል ብቻ አይደሉም።
ፀሀፊው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩን በአንድ በኩል ይክባል በሌላ በኩል ይኮንናል እኔ እንደመሰለኝ ጸሀፊው በጫት ፈረስ የጻፈው ይሆንወይ
? ብዬ እንድጠይቅ አድርጎኛል። በገፅ 53 ላይ የሚያመለክተውም ይህንኑ ነው «…ጠቅላይ ሚኒስትሩም...በመርዝ የተለወሰ ምላሽ  ሰጥተዋል።…»ሲል ይገልጻል።
የኮዬ ፊጬ የጋራ መኖሪያ ቤት በተመለከተና ...«…የለገጣፎ ቤቶችን ማፍረስ ዘመቻ እኛ ነን ያስቆምነው እያሉ ሲፎክሩ የነበሩት የግንቦት 7 ኢዘማ አመራርም  ጉዳዩን አረገቡ አቶ...እንዲወገዙ ዘመቻውን አጠናከሩ ። ...» ገፅ 57 ላይ የሰፈረው ይህ ዐርፍተ ነገር ብቻ ሳይሆን በርካታ ቦታዎች ላይ እንዳየሁት ጸሐፊው የግንቦት 7 / ኢዘማ አመራሮች ላይ ጥላቻ እንዳለበትና ከሌሎች ክልሎችና ፓርቲዎች በአሉባልታ ፈረስ ፓርቲውና አመራሮቹን  እንዲጋጩ በአጻጻፉ እንደሚፈልግ ለመመልከት ችያለው።
  ከዚህ ሌላ በአብዛኛው ጽሑፍ ላይ እንደተመለከትኩት አሉባልታና ሰውን ከሰው በማጋጨት ላይ ያተኮረ ነው። ለምሳሌ የመከላከያ ሚኒስትሩን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እንዲሁም ከባለቤታቸው ጋር ቁርሾ እንዳላቸው በተለያዩ ገጾች ላይ ጠቅሶ አንብቢአለው  ።ለአብነት ያህል በገፅ 58 እና 67 የሰፈረውን በዋቢነት መግለጹ በቂ ይመስለኛል።
  ይህን ስል ጸሐፊው አንዳንድ የጻፏቸው ነገሮች እውነታነት የለውም ማለቴ አይደለም ለምሳሌ ከገፅ 68 እስከ ገፅ 70 ባለው ውስጥ የተጻፉት አጠቃላይ ሀሳቦች  ባለፉት 27 አመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ስለነበረው ሙስናና ብልሹ አሰራር በተመለከተ የፃፋቸው አለ።
ዓለም አቀፉ የፀረ- ሙስና ጥምረት ትራንስፓረሲ ኢንተርናሽናል የተባለው ድርጅት እ.ኤ.አ በ2018 ባወጣው ከሙስና የፀዱ ሀገራት በሚለው ሪፖርቱ ላይ ኢትዮጵያን ከ180 ሀገራት 107ኛ ማስቀመጡን ጸሀፊው የገለጸበት ሁኔታ በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው። እንዲያውም ትግራይ ውስጥ በሙስና የተሰሩ በርካታ ቪላ የሆኑ አፓርታማዎች ስላሉ ይህ  ሰፈር «ሙስና ሰፈር » እንደሚባልና የታክሲ ወያሎች ሳይቀር «ሙስና ሰፈር የሚሄድ» እያሉ ሲጮሁ ማዳመጡንና አካባቢውንም ማየቱንም አንዱ ወዳጄ አጫውቶኛል። ከዚህ አንፃር ሙስና በሀገራችን ውስጥ ተንሰራፍቶ እንደነበር መመልከት ይቻላል።
 ይሁንና ከገፅ 71 ጀምሮ እስከ ገፅ 77 ላይ በሙስና ዙሪያ የተገለጹት ሀሳቦች የሰዎች ማንነት የተገለጸበት በመሆኑ ማስረጃ ሳይኖር እውነት ነው ወይንም አይደለም ብሎ ለመደምደም የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ በእጁ ማስረጃ ስለሌለው እንዲህ ነው ብሎ አስተያየት ለመስጠት ይከብደዋል።
  በሌላ በኩል ጸሐፊው ጽንፈኛ የኦሮሞ ተወላጅ እንደሆነ ከሚያሰፍራቸው ሀሳቦች መረዳት ይቻላል። ለምሳሌ አንድ እንደሱ ጽንፈኛ የኦሮሞ አክቲቪስትን ጠቅሶ  ከገፅ 79 ጀምሮ እያንቆለጳጰሰ የጻፈበት ሁኔታን ተመልክቻለው። «በተዕፅኖ ፈጣሪነቱንና በፖለቲካዊ ስትራተጂው ፈርጥ የሆነው አቶ...ይገኝበታል።አቶ...የኦሮሚያ ወጣቶችን አስተባብሮ በማታገል የህወአትን የጭቆና አራንቋ ከላያችን ላይ ያነሳ ከኦሮሞ ሕዝብ የተገኘ ብርቅዬ ልጅ ነው ማለት ይቻላል።...» እያለ ይቀጥላል።
  ከዚህ ሌላ ጸሐፊው የሚፈልጋቸውን ሰዎች በአሁኑ ወቅት ብዙ በደል እየደረሰባቸው እንደሆነ።
የማይፈልጋቸውን ሰዎች ደግሞ በጥላቻ በትር ሲመታም በጽሑፉ ላይ ተመልክቻለው።
  እከሌ የሚባለው ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን ነበረበት፣ እነከሌ ሀገር ጥለው እንዲሄዱ ግፊት እየተደረገባቸው ነው፤ የእከሌ ፓርቲን ደገፉ ተብለው በኦሮሚያ ክልል እየተያዙ ነው። በተለያዩ የሶሻል ሚዲያዎች ለምሳሌ በፌስቡክ ላይ የሀሰት የስም ማጥፋት እርምጃ እየተካሄደባቸው ነው ።ብላ ብላ ...የሚሉ ሀሳቦችን በአብዛኛው ገጾች ላይ ተመልክቻለው።  ለምሳሌ ከገፅ 78 ጀምሮ እስከ ገፅ 80 ያለውን መመልከት ይቻላል።
  ጸሐፊው ስለሶሻል ሚዲያ በተመለከተ የጻፈው ሁኔታ እርስ በርሱ የተጋጨና ተሀማኒነት የጎደለው ሆኖ አግኝቸዋለሁ። በገፅ 82 ላይ 2210 የፌስቡክ ተጠቃሚ የሆኑ ግለሰቦችን ጠቅላይ ሚኒስትራችን ቀጥረው እያሰሩ መሆኑን የገልጻል።ገፅ 84 ላይ ደግሞ 2110 የሚሆኑ ግለሰቦች ናቸው በማለት ቁጥሩን በመቶ ቀንሶ እንመለከታለን ። ከዚህ ሌላ «...የፌስቡክ አከፋፈላቸው አስመልክቶ በውጭ ሀገር የሚገኙት የፌስቡክ ተቀጣሪዎች በሙሉ የሚከፈላቸው በየወሩ 1000 ዶላር ሲሆን ገንዘቡም በየወሩ አንዳንዴ በየሁለት ወሩ ያስመዘገቡት የባንክ የሂሳብ ቁጥራቸው ገቢ ይደረግላቸዋል። በሀገር ውስጥ የሚገኙት ደግሞ ገንዘቡን የሚቀበሉት በዋና አድራሻቸው በኩል በካሽ ነው።በወር ውስጥም እንደግለሰቦቹ ከ10000 ብር እስከ 20000ብር ያገኛሉ።…» ይላል። እዚህ ላይ ጽሐፊውን ለማመን ይከብደኛል።
ምክንያቱም የዶላር እጥረት ኖሮባት 49 በመቶ በብድር ለምትተዳደር ድሀ ሀገር ለአንድ ሰው ያውም ለፌስቡክ 1000 ዶላር
ይከፈላል ፤ ሀገር ውስጥ ላለ ደግሞ እስከ 20000 ብር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይከፍላሉ ብሎ መጻፍ ጽሑፉን ተአማኒነት እንዲጎለው ያደርገዋል ። አንድ የኢትዮጵያ ዶክተር 24ሰዓት ያለ እንቅልፍ እየሰራ በየወሩ ከ13000 ብር በታች  እየተከፈለው በሚኖርባት በዚች ምስጊን  ሀገር ለተራ ነገር አንደ የተማረ መሪ ከኪሱ ይህን ያህል ገንዘብ ያወጣል ብሎ መናገር የሚያስኬድ አይመስለኝም ።
ከገፅ 87-89 ባለው ውስጥ ፀሐፊው ኦነግን ለማሳጣት በመንግስት አካላትና ባለስልጣናት ጭምር የተለያዩ ድርጊቶች እንደተፈፁም ይገልፃል ። ለምሳሌ ከቤኒሻንጉል የተፈናቀሉት ከ200000 በላይ ዜጎች የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ሆን ብለው የፈፀሙት እንደሆነ፤በኦሮሚያ ክልል ጎጂ ዞንና ቡራዮ  የነበረው የዜጎች መፈናቀል ወዘተ ሆን ተብሎ መሆኑንና  ኦነግን በሕዝቡ ዘንድ ለማስጠላት በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ፀሐፊው ገልጿል።
  በዚህ ጽሑፍ ውስጥ የተነሱት ነጥቦች ተአማኒነት ብቻ ሳይሆን በተለይም በቡራዩ የተፈናቀሉት ዜጎቻችን ምንም ይሁን ምንም ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሀንና ሶሻል ሚዲያ ላይ እንዳነበብነው የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው ችግር  እንደፈጠሩ የሰማነው ።
 በእርግጥ የኦነግ ደጋፊ ይሁንወይንም ደግሞ የመንግስት ደጋፊ የሆነው የኦዲፓ/ኦህዲድ ደጋፊዎች ለጊዜው
እኛ የምናውቀው ነገር ባይኖርም ፤ችግሩን ግን የፈጠሩት የኦሮሞ ተወላጆች  ናቸው።አሁንም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ላይ በኦሮሚያ ክልል ችግር የፈጠሩት አሁንም ኦሮሞዎች ናቸው። እኛ እስከ ምናውቀው ከ90 በመቶ በላይ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የመንግስት ደጋፊ እንደሆነ ነው የምናውቀው ። መንግስት በአጥፊዎቹ ላይ እርምጃ እንዲወስድ መገፋፋት ሲገባ እንደ ጲላጦስ ከደሙ ንጹ ነኝ ማለቱ የትም አያደርስም ። እንዲያውም ስልጣን ላይ ያለው መንግስት እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ አብዛኛው የኦሮሞ ተወላጆች ስለሆኑ ለራሳቸው ብሄር አግዘው ዝምታ እንደመረጡ ተደርጎ ነው አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚስማማው ።ከዚህ አንፃር ፀሐፊው መንግስትን ተጠያቂ እሳቸው ኦሮሞ ስለሆኑ (ከጽሑፋቸው ለመረዳት እንደቻልኩት) የኦሮሞ ተወላጆች በኦሮሚያ ክልል እየተፈጠሩ ላሉ ችግሮች ተጠያቂ አይደለም ። ማለታቸው የሚያሳዝን ብቻ ሳይሆን ትዝብት ላይ የሚያስጥል ነው።
  በገፅ 90 ላይ ፀሐፊው «...ባለፉት አመታት በጭቆና ቀንበር ስር ወድቀው የአማርኛን ቋንቋ ተገደው ሲማሩትና ሲገለገሉበት የነበሩት የኢትዮጵያ ሕዝቦች በራሳቸው ቋንቋ የመማር ማስተማርና እንደ የመንግስት የስራ ቋንቋ የመገልገል መብታቸው ተጠብቆ አይተነዋል። ነገር ግን አሁንም አሁንም የብሔር ጭቆና የለም ማለት አይቻልም...»  ይሉናል። እዚህ ላይ ፀሐፊው ጠባብ  ብሄርተኛ ብቻ ሳይሆኑ ስለቋንቋ ያላቸው ግንዛቤ ደካማ መሆኑን የሚያሳይ ነው። በአንድ ወቅት በቀድሞ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ላይ በብዕር ስሜ «በእውነት ቋንቋ ጨቋኝ ነው?» የሚል ፅሑፍ ከ20 አመት በፊት መፃፌን አስታውሳለው። አሁንም ይህ አመለካከት ላለፉት ሁለት አሥርተ አመታት አለመቀየሩ ያሳዝነኛል።በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መንግስት፣በተለይም አሁን ፎነቲክስ ዲፓርትመንት ተብሏል ። በፊት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ተቋም ይባል ነበር ። በዚህ ላይ ብዙ እንዳልሰሩ ያሳያል።ቋንቋ መግባቢያ እንጂ ጨቋኝ አይደለም ። አማርኛን ቋንቋን ለምትጠሉ ወገኖች አንድ ጥያቄ ብቻ ላንሳላችሁ እወዳለሁ። ለምን የኦሮሚፋ ቋንቋን  ቃላቱን  በላቲን ውስጥ ትጠቀማላችሁ?ለምንስ እንግሊዘኛ ቋንቋ ጥሩ ተናጋሪና ጸሐፊ ለመሆን ትፈልጋላችሁ? ምክንያቱም እንግሊዞች ቅኝ ግዛትን ለማስፋፋት  በኅይማኖት ስም ጭምር ሳይቀር ሀገራችን ውስጥ ገብተው ኢትዮጵያውያኖችን ብዙ ነገር ያደረጉ ናቸው። ቴዎድሮስ እ.ኤ.አ በ1868 አራሱን የሰዋው ለዚች ምስጊን ሀገር ሲል ነበር በእንግሊዞች ሲሸነፍ ከመማረክ ብሎ እራሱን ያጠፋው ።«..ማረከን እንዳይሉ ሰው የለ በእጃቸው ፤ገደልን እንዳይሉ ሞተው አገኟቸው፤ ምን አሉ እንጊሊዞች ሲገቡ ሀጋራቸው?...» የተባለላቸው አፄ ቴዎድሮስ አማርኛ ተናጋሪ ስለሆኑ ጨቋኝ ሆነው አይደለም።የኮሱ ሻጭ ልጅ (የድሀ ልጅ)የነበሩ ናቸው። እኛ ግን ከሌሎቹ የተሻለ የራሳችን ፊደልና ቋንቋ እያለን እሱን ሳንጠቀም የሰው ቋንቋ እየቀላወጥን ዶክማ ጭንቅላት ይዘን  «በራሳቸው ቋንቋ የመማር ማስተማርና እንደ የመንግስት የስራ ቋንቋ የመገልገል መብታቸው ተጠብቆ አይተነዋል..»እየተባለ በየጊዜው በየሚዲያው ላይ ነጋሪት ይጎሰምልናል።ማንም ሰው በአፍ መፍቻ ቋንቋው ቢማር ምንም ችግር የለውም ። ይሁንና ሀገሪቷ እንደማንኛውም ሉ አላዊ ሀገር አንድ ብሔራዊ ቋንቋ ያስፈልጋታል።ይህ ደግሞ ከአማርኛ ቋንቋ የተሻለ ካለ ማንኛውም አማርኛ ተናጋሪ የሆንን ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ ነን።ግን ምሉ የሆነ እንድ አማርኛ ቋንቋ የለን
ም።ይህ መታወቅ አለበት።
  ጸሐፊው « ...የቋንቋ እኩልነት ጥያቄን እንደማሳያ የወሰድኩት የኦሮም ሕዝብ ቋንቋን አስመልክተው ያልተመለሱ ጥያቄዎች ስላሉት ነው።እነዚህ ለአመታት ሲጠየቁ የከረሙት ጥያቄዎች፦ አፋን ኦሮሞን የአዲስ አበባ (ፊንፊኔ)ከተማ አስተዳደር እና የፌድራል መንግስት የሥራ ቋንቋ የማድረግ የመብት ጥያቄዎች ናቸው።...» ይለናል። እዚህ ላይ ፀሐፊው ኦሮሚፋ ብሔራዊ ቋንቋ ይሁን ሲሉ ቋንቋው የራሱ ፊደል አለው ወይ? ኦሮሚፋ እኮ ከላቲን ነው ቃላትን እየተወሰ የሚጠቀመው እንጂ የራሱ የሆነ ፊደል የለውም።
  ቋንቋ ይወለዳል ፣ያድጋል ፣ ይሞታል እንደሚባለው ሁሉ ። አንድ የኦሮምኛ ቃል ቢሞት ሌላ የሚተካው ቃላት የሚያገኝበት አለው ወይ?የሚለውን ጥያቄ ምንም እንኳን ማንነቶትን ደብቀው መርዞትን እረጭተው ቢሰወሩም ባሉበት ሆነው ሊመልሱልኝ ይገባል ።
  አማርኛ እኮ የራሱ የሆነ ፊደል ያለው ፤የራሱ የሆነ ስዋስዎ፤አገባብ፤አንቀፅ፤ዘር፤ነባር፤ግስ፤ ቫውል ፤የራሱ የሆነ ቁጥር ያለው፤ የራሱ የሆነ ተነባቢና አናባቢ ፊደል ያለው ወዘተ  ነው። አማርኛ እንደ ኦሮሚፋ ቀላዋጭ ሳይሆን ከአባቱ ግዕዝ መዋስ የሚችል የኢትዮጵያውያኖች ብቻ አይደለም የዓለም ጭምር መኩሪያ ቋንቋ ነው። ዛሬ ጀርመኖች አማርኛ አይደለም ግዕዝ እየተማሩ ነው።ዛሬ እንግሊዞች፣ቻይናዎች፣ጃፓኖች ወዘተ. እኛ የምንፀየፈውን አማርኛ እነሱ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ገብተው ተምረው ለእኛ በቋንቋ ተቧጭቀን ከሀገር ለምንሰደደው ሁሉ እንግሊዘኛን ወይንም  በተሰደድንበት ሀገር ቋንቋ ለማንችለው ወገኖች ማመልከቻዎችን የራሳቸውን ቋንቋ በአማርኛ ቋንቋ እየተረጎሙና እያዘጋጁ ፎርሙን እንድንሞላ እንዲሁም ስንተባተብ የአማርኛ ግስን(ቮካብለሪን) እየተረጎሙልን መጽሐፍ እያነበቡ እያስደመሙን ይገኛሉ። በእርግጥ አብዛኛው ኦሮሞዎች ሌላው ቀርቶ አማርኛ ማውራት አቅቷቸው ሲንተባተቡ እንሰማቸዋለን።ይህ ድግሞ አማርኛ ቋንቋ ጨቋኝ ስለሆነ  አይደለም ኦሮሞዎች አይደለም መጽፍ ማወራት ስለከበዳቸው ነው። ይህ ደግሞ የመጣው በጥላቻ ላይ ስለተመረኮዙ ቋንቋውን የመማርና የማወቅ  ፍላጎት ስለሌላቸው በእራሳቸው ላይ ያመጡት ችግር ነው።
 የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንትን ጽ/ቤት ጨምሮ በርካታ የኦሮሚያ መሥሪያ ቤቶች የሚገኙት አዲስ አበባ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለምን እነዚህ ጽ/ቤቶች አዳማ ወይንም ሌላ የኦሮምያ ክልል ይሁን ብሎ የተከራከረው ወይንም እንደ ቄሮዎች የጫረው ፀብ የለም።
ምክንያቱም የአዲስ አበባ ሕዝብ አብዛኛው ፊደል የቆጠረ ጭምር ከመሆኑም ባሻገር ሁሉም በመፈቃቀርና በመከባበር ላይ በተመሰረተ መልኩ
የሚኖርባት የኢትዮጵያችን ዋና ከተማ መሆኑን ያውቃል።
 አዲስ አበባ አይደለም የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋና መዲና ነች። እናም ፀሐፊ ተብየው ጠባብ አስተሳሰብህን እዛው ቦቲክ ውስጥ ጨምረው።
  «...አንድ ሰው ተወልዶ ባደገበት በአያት ቅድም አያቶቹ ቀዬ በራሱ ቋንቋ ካልተገለገል የብሔር ጭቆና ስር እንደሆነ ከዚህ በላይ ማስረጃ የለም...» ይለናል ፀሐፊው።
 ቁልፍ የሆኑ የመንግስት የስልጣን ቦታዎች ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስቶ እስከ አዲስ አበባ ከንቲባ ድረስ የሚመራው በኦሮሞ ተወላጆች ነው። እናም ውዱ
ፀሐፊ ብሔሮት እንደተጨቆነ ሲያወሩ ትንሽ ለአፎት እንኳን አይከብዶትም?
  እንዲያውም አዲስ አበባንም በቅጡ የሚያውቁትም አይመስለኝም ምክንያቱም አንድም የኦሮሞ መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ውስጥ የለም ብለው ደምድመዋል ።የኦሮሚያ ባንክ፣የኦሮሚያ መሬት አስተዳደር፣የኦሮሚያ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት፣የኦሮሚያ ባህል ማዕከል የኦሮሚያ…ወዘተ.የሚገኘው? የት ነው።ስታዲዮም ፊትለፊት፣ኢሰመኮ ፊትለፊት፣ስድስት ኪሎ ገንዘብ ሚኒስቴር አጠገብ፣ ሳንጆሴፍ ት/ቤት አጠገብ ፣  ብሔራዊ ትያትር ቤት አጠገብ ወደ ኮሜርስ መሄጃና ፊትለፊት ያሉ መስሪያ ቤቶች ወዘተ.የማን ብሔር መሥራያ ቤቶች ናቸው?
  በቋንቋና በአገልግሎት ዙሪያ በርካታ ነጥቦችን በሬ ወለደ የሆነ ጽሁፋቸውን እስከ ገፅ 94 ድረስ ጸሐፊው አቅርበዋል።
ይሁንና አሉባልታን ያራገበ አንድ መጽሐፍ ጸሐፊ በአማራና በኦርቶዶክስ ላይ ያነጣጠረ  የጥላቻ ብዕር የሰፈረበት ስለሆነ ስለ አማርኛ የጻፉት ጽሑፍ በቂ ሕውቀት እንደሌላቸው ያሳያል። እኔ ሳስበው ጸሐፉ እራሱ ገንዘብ ተከፍሎበት  የተጻፈ ነው የመሰለኝ።ምክንያቱም ለአማርኛ ጥላቻ ያለው ሰው በላቲንኛ ይጽፋል እንጂ በአማርኛ ይጽፋል ብዬ አልጠብቅም።
  በአብዛኛው መጽሀፉ ላይ ያየሁት ኦሮሞን በተለይም ኦንግን የማንቆለጳጰስ ሁኔታ ነው ። ብዙ ችግሮች እየደረሰበት እንደሆነ፤የኦሮም ታዋቂ ተወላጆች ችግር እንዳለባቸው፤ ባለፉት ጊዜያት በኦሮሚያ አካባቢ ስለ ተፈጠሩ ችግሮች ፤በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ ፀሐፍትና የታሪክ ተመራማሪ የሆነውን ዳንኤል ክብረትን  ሳይቀር የማንቋሸሽና በሬ ወለደ የሆነ የፈጠራ ጽሑፍ፤ እንዲሁም ቀረቤታ እንዳላቸው የሚነገርላቸውን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትሩን እርስ በርስ እንዲጋጩ በርካታ ተረት ተረት የተባሉ ጽሑፎችን በመጽሐፉ ላይ አቅርቧል።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለጻፉት ሶስት መጽሐፍ፤የኦሮሞ ሕዝብ ዳግመኛ  ለብጥብጥና ለእረብሻ እንዲነሳሳ መገፋፋት፤የኦሮሞ ሕዝብን ከሌላው ብሔር ጋር የማጋጨትና የመቀስቀስ ሁኔታ የታየበት።መጽሐፍ ነው።
 ስለኦሮሞ ወጣቶች ቄሮ(በላቲን Qeerroo)ትግል ሁኔታ አንዳንድ ነጥቦችን ለማንሳት ተሞክሯል።

ስለ መጽሐፉ ይዘት
መጽሐፉ በስነጽሁፍ አጻጻፍ ስለት ሚዛን የሚደፋ አይደለም።
 በሁለተኛ ደረጃ ላይም ሆነ በዩንቨርስቲ እንደተማርነው ሦስት አይነት የሥነ-ጽሑፍ ስልቶች አሉ። አንደኛው ከዝርዝር ወደ ዋናው ሀሳብ የምንመጣበት ፤ ሁለተኛው ከዋናው ወደ ዝርዝር የምንሄድበት፤ ሶስተኛውና የመጨረሻው ከዝርዝር ወደ ዋናው ሀሳብ ከዛም ወደ ዝርዝር ሀሳብ የምንሄድበት የአጻጻፍ ስልቶች አሉ።
  በዚህ መጽሐፍት ውስጥ ግን ያየሁት ለምሳሌ «የቤተ መንግስቱ ዘዋሪዎች  በሚለው » ርዕስ ስር  ጸሁፉ እዛው ርዕሱ ላይ  መቋጨት ሲገባው በሌሎችም  ርዕሶች ላይ ይህንኑ አባባል ሲደጋግመው ይታያል ። ይህ ማለት ከላይ በተነሱት ሶስት የአጻጻፍ ስለት ላይ በመመርኮዝ የጻፈው ነገር ካለመኖሩም ባሻገር የጽሑፉ ፍሬ ሀሳብ ወይንም መልዕክት አሊያም አንኳር ነጥብ ምን እንደሆነ አልገባኝም።
 ተአማኒነት
መጽሐፉ የሚታወቁ የሰዎችን ስም ከተፈጸሙ ድርጊቶችና ክንውኖች ጋር በማያያዝ ተአማኒነት እንዲኖረው ጥሯል።ከዚህም ሌላ በኅብረተሰቡ ውስጥ የሚወሩ ወሬዎችና አሉባልታዎች በመጽሐፉ ውስጡ ስላሉ ተአማኒነት ያለው ይመስለናል።ይሁንና መቼ፣የት፣እንዴት፣ለምንና ማን የሚሉትን ጥያቄዎች እያነሳን በተነሱት ነጥቦች ላይ ጥያቄ ስናነሳ ግን ተአማኒነት በአብዛኛው የሌለው መሆኑን እንረዳለን።
ለምሳሌ የፌስቡክ ሰራዊቶች የሚለው ላይ በውጪ የሚኖሩ አንድ ሺህ ዶላር ሀገር ውስጥ ያሉ ከ10-20 ሺህ ብር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይከፍላሉ ይለናል። መቼ፣የት፣እንዴት፣ለምንና ማን ብለን ስንጠይቅ ግን የተሟላ መልስ አናገኝም። እንደኛ እኔ እንዳየሁት በቢሮ የሚሰሩ የኢህአዲግ አባላቶች ፌስቡክ ሲጠቀሙ አይቻለው ። ይህ እንግዲህ የኦዲፓ ፤የሕወአት የሌላም ፓርቲ አባላቶች ናቸው።ነገር ግን የመንግስት ተቀጣሪዎች እንጂ ዶ/ር አብይ የሚከፍሏቸው አይደሉም።ዶ/ር አብይስ ገንዘቡን ከየት ያመጣሉ?ለምንስ ብለው ይከፍላሉ?ተዋቂ ለመሆን ነው? እናም የፊልም አክተር ናቸው? ወይስ ዘፋኝ?ወይስ ኳስ ተጨዋች?
እንዲህ እንዲህ እያልን ካነሳን ጽሑፉ ተአማኒነት ያንሰዋል።

ስም ላይ ጥንቃቄ አለማድረግ 
 የምንወደውና የምናከብረው ድራሲ ባህሉ ግርማ በደርግ ጊዜ ተከልክሎ በነበረው «ኦሮማይ» መጽሐፉ ላይ የደርግ ባለስልጣኖችን ትክክለኛ ስማቸሁን አልተጠቀመም ይሁንና አንባቢው እንዲመራመርና እንዲያውቅ በአጻጻፍ ስልቱ እያዋዛ ያስቀኘናል።
  በዚህ መጽሕፍ ላይ የሚያመሳስለው በድብቅ መሸጡና ከተገኘ እንዲቃጠል መደረጉ ብቻ ነው።
  የባለስልጣን ስሞችን እየጠቃቀሰ ሲያወራ ልክ እንድ ቆሎ ጓደኛቸው አድርጎ ነው የሚያወራው። አንድ ሰው ጥሩም ይሁን መጥፎ ሀገር መሪ እስከ ሆነ ድረስ መከበር አለበት።ያለ ማስረጃ ደግሞ ስም እየጠሩ ማብጠልጠል በሕግ «በስም አጥፊነት (Defamation) » ያስጠይቃል። 
ምንጭ
 ለአንድ ለጻፍነው መጽሐፍ ለልቦለድና በእውነት ላይ ያተኮረ ኢልቦለድ መጽሐፍ ካልሆነ በስተቀር ምንጭ (Source) ከዛም ባለፈ አስፋላጊ ነገሮች ያልናቸውን ነገሮ ያለበትን ገፅ የምናወጣበት (Index  ) ወዘተ. ሊኖሩት ይገባል። መጽሐፋችን ታአማኒነት እንዲኖረው ከማድረጉም ባሻገር ተጨማሪ ማብራሪያ ለሚፈልግ አንባቢ ተጨማሪ መረጃ እንዲፈልግ በር እንከፍትለታለን።
ማጠቃለያ
ከላይ አንዳንድ በመጽሐፉ ዙሪያ ነጥቦችን ለማንሳት ሞክረናል። በእርግጥ መጽሐፉ ላይ ግለሰቦች፤ባለስልጣኖች የመንግስት መስሪያ ቤቶች ወዘተ. ያለግብራቸውና ያለስራቸው ሰማቸው እየተነሳ የተቦጨቁበት ሁኔታ አለ።እኔ የወያኔ /ኢህአዲግ ደጋፊ ሆኜ አይደለም። ባለስልጣኖች ለምን ይሰደባሉ የምለው። መተቸት ካለባቸው እንደተማረ ሆኖ በማስረጃ በተደገፈ መልኩ Criticize  እናድርግ ነው። ያለ ማስረጃ መስድብ ግን የሰዎችን ሰብእና ከመግፈፉም ባሻገር በሕግ ያስጠይቃል።
አንዳንድ በሰለጠነው ሀገር የውሸት ዜና ተፈብርኮ የሚሰራበት ሁኔታ አለ በተለይም በስፖርቱ መስክ በብዛት ይታያል። ይህም ተጨዋችን ለማሻሸጥ።ተፈላጊነቱ ይበልጥ እንዲጨምር ለማድረግ ወዘተ.ይጠቀሙበታል። በፖለትካ መስኩም ተመሳ&a