Crisis in Ethiopia: በኢትዮጵያ ያለው ቀውስና የነፍስ አባታችን የአሜሪካ ውደሳ !


 

ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ ( ጮራ ዘ አራዳ) 

(ደራሲ  ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሃያሲ )

ኢትዮጵችን በአንድ በኩል  በሰብአዊ ቀውሶች ብትናወጥም  በሌላ በኩል ከ27 ሀገሮች ወደ ሀገራችን የሚገቡ ስደተኞችን በአግባቡ  በማስተናገድ ከአሜሪካ መንግስት አድናቆት ተችሯታል።

ሀገራችንን  ድርቅ፣ ጎርፍና የእርስ በእርስ ጦርነት በትንሹ  21.4 ሚሊዮን ዜጎቻችን ለእርዳታ ፈላጋ እንዲዳረጉ አድርጓል  ። ከ21.4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች እንደ ምግብ ፣ንፁህ ውሃ የመሳሰሉ መሰረታዊ የሆኑ አስፈላጊ ነገሮች በአስቸኳይ አሁን ድረስ  ያስፈልጋቸዋል። በርካታ ኢትዮጵያዊ ለቤተሰቦቻቸውና ለከብቶቻቸው  ምግብና መጠጥ  ለማግኘት ሲሉ ብዙዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው  ተሰደዋል።ይህም በቁጥር ሲሰላ ወደ 4.4 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ከቀያቸው  ተፈናቅለዋል። 

የሰብአዊ እርዳታ በኦሮሚያ ክልል፣ ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል በአሁኑ ጊዜ እስከ 1.5 ሚሊዮን የሚደርሱ ተፈናቃዮች በካምፖች ውስጥ ወይም ከተቀባይ ማህበረሰቦች ጋር ተጠግተው ይኖራሉ ተብሎ  ይገመታል።

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም የተሻለ ሁኔታ አገኛለሁ በሚል ተስፋ ሰንቀው አካባቢውን ለቀው  የነበሩ ከ300,000 በላይ ሰዎች አሁን ግን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።ይሁንና የዓለም አቀፍ  እርዳታ  ድርጅቶች  እንደሚሉት ከሆነ እነዚህ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ፣ የመጠለያ፣ የውሃ፣ የንፅህና አጠባበቅ (እርዳታ እንዲሁም  የጤና ተደራሽነት ያስፈልጋቸዋል በማለት ይናገራሉ። 

ነገር ግን በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ታጣቂዎች መካከል የተቀሰቀሰው  የእርስ በእርስ ግጭት ከእነዚህ ማህበረሰቦች መካከል ጥቂቶቹን ለማድረስ እጅግ አስቸጋሪ  መሆኑን  ሳይገልጹ አላለፉም።

ይህንኑ በተመለከተ በቅርቡ  ኦቻ OCHA እንዳስታወቀው 'በ2023 እ. ኤ . አ ከታቀደው 800,000 ሰዎች ውስጥ ከ100,000 የሚበልጡት ሰዎች የአደጋ ጊዜ መጠለያና ምግብ ነክ ያልሆኑ እርዳታዎች በመላው [ኦሮሚያ ክልል] እንዲያገኙ  ተደርገዋል። ወደ አካባቢው  የተመለሱት ሰዎች ካጋጠሟቸው አበይት ፍላጎቶች መካከል ኑሯቸውን መልሶ ለመገንባት የሚደረገው ድጋፍ አንዱ  መሆኑን ኦቻ ይገልጻል።

የጎርፍ  ማስጠንቀቂያ 

ይህ ሁሉ ችግር በኢትዮጵያእያለ 

በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግስት በ2024 ከመጋቢት-ግንቦት ወር ኃይለኛ  ዝናብ እንደሚዘንብ ማስጠንቀቂያ የሰጠ  ሲሆን  ህዝቡ ይከሰታል ተብሎ  በሚጠበቀው የጎርፍ  አደጋ  ከወዲሁ እንዲዘጋጅ ጥሪ አቅርቧል። በቅድመ ማስጠንቀቂያው  የህብረተሰቡን ህይወት ለመታደግና አርሶ አደሮች በሰብል እና በንብረታቸው ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችንና የመንግሥትን ድጋፍ ለማግኘት ተስፋ ያደርጋሉ። ነገርግን በዚሁ የጎርፍ አደጋ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ሊጎዱ እንደሚችሉና ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ የአካባቢው ነዋሪዎች  ከቀያቸው ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ይጠበቃል። 

 በሌላ በኩል ከነፍስ አባታችን ከአሜሪካ ጋር ያለን ወዳጅነት የጠነከረ ይመስላል።በተለይም ኢትዮጵያ በእርስ በእርስ ጦርነት ወይም  በፖለቲካ ከሀገራቸው ሸሽተው ወደ  ኢትዮጵያ ለሚገቡ ስደተኞች የምታደርገው  አቀባበል  አድናቆት አስችሯታል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት አገልግሎት ሰሞኑን እንደገለፀው  በምስራቅ አፍሪካ እያደገ ባሉ የሰብአዊና የስደት ተግዳሮቶች ላይ በተለይም ከኢትዮጵያ እና ከቻድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ እንዲሁም የሰብአዊ እርዳታ መሪዎችና ስደተኞች ጋር መነጋገራቸውን ገልፀዋል።በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የህዝብ፣ የስደተኞች እና የፍልሰት ቢሮ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጁልዬታ ቫልስ ኖይስ እንዳሉት « በጉዞዬ ወቅት ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣የሰብአዊ እርዳታ መሪዎች እና አጋሮች እንዲሁም በሁለቱም ሀገራት ከሚገኙ ስደተኞች ጋር ተገናኝቻለው። በመካከለኛውና በምስራቅ አፍሪካ እያደጉ ባሉ የሰብአዊና የስደት ፈተናዎች ላይ አተኩሬ ነበር። በዚህም መሰረት ከቻድ ጠቅላይ ሚንስትር ማሳራ ጋር ባደረኩት ቆይታ ከ47 ሚሊዮን በላይ በሱዳን እና በአጎራባች ሀገራት ቻድን ጨምሮ  ደቡብ ሱዳን ላይ  ለደረሰው የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ የሰብአዊ ዕርዳታ በማሳወቄ ኩራት ተሰምቶኛል።» ብለዋል።« ይህ የገንዘብ መጠን ካለፈው በጀት ዓመት ጀምሮ በሱዳንና በአጎራባች ሀገራት ላሉ ሰዎች አጠቃላይ የአሜሪካ ሰብአዊ እርዳታ ከ968 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከፍ በማድረግ ለመለገስ ታስቧል። የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ለሱዳን አስቸኳይ ምላሽ የሰብአዊ እርዳታ መለገስ ቀዳሚ ተግባር ነው ። አሁን በጉብኝቴ እንዳየሁት ከ1 ሚሊዮን በላይ ስደተኞች በየእለቱ ወደ ቻድ እየገቡ ነው።ሱዳን ውስጥ ባለው ጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ስደተኞችን ስቃይ ለመቅረፍ ከሌሎች የአለም ማህበረሰብ አባላት ጋር ተባብረን ለመስራት ቆርጠን ተነስተናል። » ሲሉ ገልጸዋል።« ኢትዮጵያም ሆነች ቻድ በሱዳን ውስጥ ባለው ጦርነት በሰፊ የሰብአዊ ዕርዳታ ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ ሀገራት  ናቸው። ከ2023 መጀመሪያ ጀምሮ ኢትዮጵያ ወደ 50,000 የሚጠጉ የሱዳን ስደተኞችን ተቀብላለች። በአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ አለመረጋጋት ባለበት ወቅት፣ ኢትዮጵያ ለተፈናቀሉ ዜጎች የምትሰጠው ድጋፍ አሁንም በጣም ወሳኝ ነው።» ብለዋል።

«ኢትዮጵያ እያለሁ ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሱዳን ለተፈጠረው ሰብዓዊ ቀውስን በተመለከተ ምን መደረግ እንዳለበት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ተወያይቻለሁ። የኢትዮጵያ መንግስት ከሰብአዊ እርዳታ አካላት ጋር በቅርበት በመስራት አዳዲስ የስደተኛ ቦታዎችን ለመመስረትና በአስር ሺዎች ለሚቆጠሩት አዲስ ስደተኞች አስፈላጊ የሆነ የህይወት አድን እርዳታ ለመስጠት ችሏል። የሱዳን ህዝብ በአገራቸው ከሚደርስባቸው ጥቃት እንዲያመልጡ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚያደርገው ድጋፍ እጅግ ጠቃሚ ነው። በጉብኝቴ ወቅት፣ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የከተማ የስደተኞች ማዕከል ጎበኝቻለው።።በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የህዝብ፣ የስደተኞችና የፍልሰት ቢሮ ፓርተነር ከሆነው ጀሱት የስደተኞች አገልግሎት ጋር በትብብር የሚሰራ ነው።በማዕከሉ የመማሪያ ክፍሎችና የመዝናኛ ስፍራዎች ውስጥ ካሉ ስደተኞች ጋር ተነጋግሬአለው። እንደዚያ ያሉት ጣቢያዎች በተለይ ለወጣት ስደተኞች እንግሊዘኛ እንዲማሩ፣ የሙያ ክህሎት እንዲያገኙና በጥበብ እና በሙዚቃ ሀሳባቸውን እንዲገልጹ እድሎችን የሚፈጥር መሆኑን ለመረዳት ችያለው። ይህ ድጋፍ በዩኤስ እና በሌሎች አለምአቀፍ ለጋሽ አማካኝነት የስደተኞችን የመቋቋም አቅም ያሳድጋል ። አዲስ መጤዎች ከአዲሶቹ ማህበረሰቦቻቸው ጋር እንዲዋሃዱ ይረዳል። » ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሕዝብ፣ የስደተኞች እና የፍልሰት ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጁልዬታ ቫልስ ኖይስ ገልፀዋል።

 ቻድ ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን የመቀበል ታላቅ ፈተና ከፊቷ ተደቅኖባታል ።

በቻድ ውስጥ ያሉ አቅመ ደካሞችን በተለይም ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችን እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለመደገፍ ቁርጠኝነት መኖሩን ነው ኃላፊው የገለፁት። በዩናይትድ ስቴትስ የሚደገፉ ፕሮግራሞች፣ እንዳሉና ከ47 ሚሊዮን ዶላር በላይ የተገኘ ሲሆን እስከ 18 ሚሊዮን ዶላር በቻድ ውስጥ ላሉ ፕሮግራሞች የሚውል ነው  ብለዋል።- ይህ ገንዘብ  ጥበቃን፣ መጠለያን፣ ውሃንና ንፅህናን ፣ ትምህርትን እንዲሁም ሌሎችንም ይደግፋሉ። 

የአሜሪካ  መንግሥት በዚሁ መግለጫው በኃላፊው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሕዝብ፣ የስደተኞች እና የፍልሰት ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጁልዬታ ቫልስ ኖይስ  በኩል እንደገለፀው «የኢትዮጵያ መንግስታትና ህዝብ በሱዳን እና ከሌሎች ሀገሮች የሚሰደዱ ስደተኞችን ተቀብለው በማስተናገድ ላደረጉት አስተዋጾ ምስጋናችንን በአሜሪካ መንግሥት ስም ደግሜ አቀርባለሁ። » ብለዋል። ለሱዳን ድንገተኛ አደጋ ልዩ የሆነ፣ ረሃብን እና የረዥም ጊዜ ጥፋትን መከላከል ሁለቱንም የተኩስ ማቆምና ያልተደናቀፈ ሰብአዊ ድጋፍን ማቅረብ ይጠይቃል። እኛ አሜሪካ የምንገኝ በሱዳን አስከፊ ግጭት ለተጎዱ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት አድን ድጋፍ ለማድረግ ከኢትዮጵያና ከቻድ መንግስታት እንዲሁም ከአለም አቀፍና ከሀገር ውስጥ አጋሮች ጋር በጋራ ለመስራት ቁርጠኞች ነንም። » በማለት ተናግረዋል።  እያደገ ያለው የሰብአዊና የስደት ተግዳሮቶች በመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ ምን እንደሚመስል ። የደቡብ ሱዳን ፍሪላንሰር ጋዜጠኛ ሚስተር ሪቻርድ ሱልጣን  የቀረበው  የመጀመሪያ ጥያቄ ሲሆን ሚስተር ሱልጣን « በቻድ ያሉ ስደተኞች በኢትዮጵያ ካሉት ስደተኞች ያላቸው ፍላጎትና ያለው ልዩነት ምንድነው?»  ሲል  ለቀረበው  ጥያቄ  የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሕዝብ፣ የስደተኞች እና የፍልሰት ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጁልዬታ ቫልስ ኖይስ  ሲመልሱ፡ «አመሰግናለሁ። ለጥያቄው አቶ ሱልጣን እናመሰግናለን። ደህና፣ ሁለቱም አገሮች እጅግ በጣም ብዙ ለጋሽ ሀገሮች  ነበሩ ።የሁለቱም አገሮች ህዝቦች ለረጅም ጊዜ ስደተኞችን በመቀበልና በመደገፍ እጅግ ለጋስ የነበሩ ናቸው። ግን ምላሾቹ የተለያዩ ናቸው ።የሁለቱም ሀገራት ሁኔታ የተለየ ነው. ኢትዮጵያ ለዓመታት ከተለያዩ ሀገራት - ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ የመን፣ ሶሪያ ስደተኞችን አስተናግዳለች። ኢትዮጵያ በነበርኩበት ጊዜ ከሁሉም ሀገራት የመጡ ስደተኞችን አግኝቻለሁ። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ወደ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ስደተኞችና 4 ሚሊዮን ተፈናቃዮችን ታስተናግዳለች። የኢትዮጵያ መንግሥት  ይህን ሁሉ ስደተኞች  ተቀብሏል - ወይም ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ወደ 50,000 የሚጠጉ የሱዳን ስደተኞችን ተቀብላለች።በአገሪቱ ውስጥ ካሉት ስደተኞች ጋር ዳግመኛ ተጨምሯል።. ኢትዮጵያ ለእነዚህ ስደተኞች የምታውለው የራሷ የሆነ ከፍተኛ ሀብት ያላት አገር ነች።» ካሉ በኋላ በመቀጠል።

 «ይህ በእንዲህ እንዳለ ቻድ ድሀ አገር ነች - ከሶስት ሰዎች አንዱ ለራሱ ህልውና ድጋፍ የሚፈልግበት ሀገር ነው።ይሁንና ያ የቻድ ዜጎች ጥሩዎች ናቸው። ቀደም ሲል እንደገለጽኩት ባለፈው አመት ወደ 560,000 የሚጠጉ ስደተኞችን ዘንድሮ ከ100,000 በላይ ስደተኞችን ተቀብለዋል። ይህ በከፍተኛ የውስጥ ድህነት ባለች በት ሀገር ውስጥ ነው  እየተደረገ ያለው። እንዲያውም  ከጠቅላይ ሚንስትር ማሳራ ጋር ባደረኩት ውይይት፣ ለእኔ የምወስደውን አንድ ሀሳብ ነገሩኝ።ስደተኞች በቻድ ሀገር የጋራ ድህነትን እያስተናገዱና እየተካፈሉ ነው የሚኖሩት - ፍቀዱልኝና - ይህን አባባላቸውን ጻፍኩኝ፣ አሁን እኔ እያወራው ያለሁት ስለመልካምነት ነው። ነገር ግን የጋራ ድህነት አላቸው ፤ለማንኛውም ግን ይቅርታ። ቻድ በሚያስደንቅ ሁኔታ ለጋስ ሀገር ነች ናትም - ግን ትልቅ ድህነት ቢኖርባትም ትልቅ ስደተኛን የመርዳት ፍላጎት ያላት ሀገር ናት ፣ የዚህ ቃለምልልስ ምላሼ በዋነኝነት ያተኮረው ባለፈው ዓመት በሱዳን ውስጥ እየሆነ ባለው ነገር ላይ ነው። የሱዳን ሁኔታ ጉዳይ ቀውሱና ግጭቱ በቀጠለ ቁጥር ብዙ ስደተኞች ቻድ እንደሚደርሱ ሁሉም ሰው ይጠብቃል። ስለዚህ ፍላጎቶች - በሁለቱም አገሮች ውስጥ እውነተኛ ስደተኛን የመቀበል ፍላጎቶች አሉ.።በሁለቱም ሀገራት እንግዳ ተቀባይ መንግስታትና ህዝቦች ናቸው ። ነገር ግን የሁለቱም ሀገራት የስደተኞች ቁጥር የተለያየ ነው፣ ስደተኞችን የሚያስተናግዱበትም መንገዶችም የተለያዩ ናቸው። ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ተናገሩት ለመመለስ ማስታወሻዬን ለማየት እሞክራለሁ። ኦህ…አግኝቻለሁ. የጋራ ድህነት እና ሰብአዊነትን ከስደተኞች ጋር  እየተጋራን ነው ።ነበር. ያሉት፤ እናም …ቻድም ሆነች ኢትዮጵያ ለየራሳቸው የስደተኛ ሁኔታን በአግባቡ እንዴት በማስተናገድ ላይ እያሉ  እንደሆነ የሚገልፅበት ጥሩ መንገድ ነው ብዬ አስቤአለው። . » በማለት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሕዝብ፣ የስደተኞች እና የፍልሰት ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጁልዬታ ቫልስ ኖይስ ተናግረዋል።

ከኤንፒአር ሬድዮ ነፃ ጋዜጠኛ አማኑኤል ኢጉንዛ  ኢትዮጵያን በተመለከተ ያነሳው ጥያቄ የሚከተለው ነበር።ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ባላችሁ ግንኙነት በኦሮሚያና በአማራ ክልል በተፈጠሩ ግጭቶች ሳቢያ በአገር ውስጥ ስለተፈናቀሉ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ጉዳይ ለኢትዮጵያ መንግሥት ምን እያደረገ እንደሆነ ይህንን በተመለከተ አንስታችኋል ወይ ? ምክንያቱም በተለይ በአሜሪካ ላይ ከሚቀርቡት ትችቶች መካከል እነዚህን ጉዳዮች ለመፍታት ከመንግስት ጋር ለመነጋገር መሞከር በጣም ጠንካራ አይደለም የሚል ስሞታዎች የሚቀርብበት ሁኔታ አለ የሚል ነው። 

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሕዝብ፣ የስደተኞች እና የፍልሰት ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጁልዬታ ቫልስ ኖይስ  ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በተለያዩ የሰብአዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት  ማድረጋቸውን ገልፀው።  የጉዟዬ ዋና አላማ በሰፊው ያተኮረው በሱዳን ስደተኞች አቀባበል ላይ ያተኮረ ነበር፣ የውይይታችን ዋና ትኩረት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ያ ነው። ነገር ግን ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈናቀሉ ዜጎችን ጨምሮ ለተለያዩ ህዝቦች ትልቅ የሰብአዊ እርዳታ ለጋሽ ሆና እንደምትቀጥልም ተነጋግረናል። እንዲያውም ባለፈው የበጀት አመት ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይና እስከዚህ በጀት አመት 89 ​​ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ ሰጥተናል ለስደተኞች፣ ጥገኝነት ጠያቂ ለሆኑ፣ በአገር ውስጥ ለሚፈናቀሉ ተፈናቃዮችና ለሌሎችም በግጭት፣ በድርቅ፣ በምግብ እጦት የተጎዱ ወገኖች የሚውል የገንዘብ እርዳታ ነው።ስለዚህ ለጥያቄዎ መልስ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ። » ብለዋል።በኬንያ የምስራቅ አፍሪካ ባልደረባ ከሚስተር አግሬይ ሙታምቦ የቀረበው ሌላ  ጥያቄ «የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ያሉ ሀገራት የሰራተኛ ፍልሰትን በተለይም ወደ አረብ ሀገራት ወይም ባህረ ሰላጤ ሀገራት እንዴት እየተመለከተችው  እንደሆነ በአጠቃላይ መናገር ይችላል ወይ?» የሚል ነበር።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሕዝብ፣ የስደተኞችና የፍልሰት ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጁልዬታ ቫልስ ኖይስ ፡ሲመልሱ « በእርግጥ በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው። ብዙ የተነጋገርንበት ነገር ነበር፡  የአሜሪካ ፖሊሲ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ስርአት ያለው ና ሰብአዊ ስደትን እና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን እድሎች መደገፍ ነው። አለም አቀፋዊ አቋማችን ነው። በአፍሪካ በተለይም እኔ የምመራው ።በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የህዝብ፣ የስደተኞች እና የፍልሰት ቢሮ PRM ለአፍሪካ ክልላዊ የፍልሰት ፕሮግራም የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል፣ እኛም ለአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት እና ለክልላዊ ፍልሰት ምላሽ እቅድ እንረዳለን። ለሠራተኛ ፍልሰት የሚረዳው የገንዘብ ድጋፍ - ህጋዊ ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ፣ ሰብአዊ የሠራተኛ ፍልሰት - ከስደት ጋር በተያያዙ አገሮች መካከል ውይይቶችን እናመቻቻለን ፤ከኖሩበት ሀገር ወደ አገራቸው መመለስ ለሚፈልጉ ስደተኞች ውይይት እናደርጋለን። በተለይም ከየመን ወይም ከጅቡቲ ወደ አገራቸው መመለስ ለሚፈልጉ ስደተኞች ያንን ስናደርግ ቆይተናል።

ስለዚህ እኛ የምንሳተፍበት አካባቢ ነው, ፡በዚህ በአረብ ክልል ውስጥ ለሥራ ለመስራት የሚወጡ  ስደተኞች  በየጊዜው እየጨመረ የሚሄድ የስደተኝነት ፍላጎት ነው  ያለው ነገር ግን እርግጠኛ ነኝ ይህንን ሁላችሁም በዓለም ዙሪያ ያላችሁ ለሥራ የሚኬድ ስደትን እንደምትደግፉት እርግጠኛ ነኝ እነዚህ በመላው ዓለም ትኩረት የሚስቡ ጉዳዮች ናቸው. » ብለዋል።ኃላፍው ይህን ያሉት አሜሪካ በአሁኑ ወቅት በሜክሲኮ ድንበር በየቀኑ በብዙ ሺህ የሚገመት ስድተኞች እየገቡባት ነው።ይህን የስደተኞች በየቀኑ ወደ አሜሪካ መግባት በተመለከተ የቴክሳስን ቦርደር በተመለከተ SB 4 የተባለ የቴክሳስ ገቨርነር ህግ አውጥቶ እንደነበር CBS ዘግቦ ነበር።ይህ ህግ ቦርደሩን አልፈው የሚገቡ ስደተኞች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱና እስከ 20 አመት የሚደርስ እስራት የሚያስፈርድ ህግ ነበር ቴክሳሶች ያጸደቁት ።የቴክሳስ ገቨርነር ግሬግ ጋቢን ህጉ ተፈፃሚ ይሆናል በማለት ደስተኛ ነበር።ማክሰኞ ቀን ይህ ህግ ከወጣ በኋላ ማታ ላይ ግን የፌድራል የአሜሪካ መንግሥት ህጉን ውድቅ የሚያደርግ ሀሳብ አቅርቦ ጉዳዩ እንደገና እንዲታይ ጥያቄ በማቅረብ ጉዳዩ ተፈፀሚ እንዳይሆን ተደርጓል ።የሜክሲኮ መንግስትም ይህ የሰበአዊ መብት እረገጣ ከመሆኑም ባሻገር አሜሪካ ወደ ሜክሲኮ አልቀበልም ብላ የምትልካቸውን ሰዎች እኛም አንቀበልም የሚል አቋም እስከመያዝ ችለዋል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስልጣን ላይ ከተቀመጡበት ጊዜ አንስቶ በአጠቃላይ 7.2 ሚሊዮን ኢሌጋል የሆኑ ስደተኞች ወደ አሜሪካ የገቡ ሲሆን ወደፊትም አሜሪካን እየናፈቀ ወደ አሜሪካ የሚገባው የስደተኛው ቁጥር በእጥፍ እየጨመረ እንደሚሄድና በክልሉ ያለው የሥራ አጥ ቁጥር እየጨመረ ስለሚሄድ ቴክሳስን ከአቅሟ በላይ እንድትኖር ያደርጋታል የሚል ፍራቻ አለ።በዚህም የተነሳ የቴክሳስ ገቨርነር በቀጣዩ ምርጫ ይህን የስደተኞች ወደ አሜሪካ የሚጎርፈውን ለማስቆም በግንብ እንዲታጠር ገንዘብ ለማሰባሰብ ያሰቡትን አከራካሪውን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ትራምፕን በግዛቱ እንደሚያስመርጥ ተጠቁሟል።የአሜሪካ መንግሥት ይህን ያህል በህዝቦቿ ዘንድ ወደ ሀገሯ የሚገቡ ስደተኞችን በተመለከተ ጫና እየተደረገባት ቢገኝም።ስደተኛው በሀገሯ ውስጥ እንደ ቻድና ኢትዮጵያ ህዝብ ያለውን ተካፍሎ እየበሉ እንዲኖሩ ባታደርግም።እራሳቸውን ችለው እንዲኖሩ አስፈላጊውን ሁሉ ጥረት እያደረገች ነው የምትገኘው።ከዚህ አንፃር አሜሪካ ከድሀ ሀገሮች ወደ አሜሪካ የሚጎርፉ ስደተኞች ለመቀነስ ሥራ ወደ አለበት አረብ ሀገሮች የሚሄዱ ስደተኞችን አሜሪካ እያበረታታች የምትገኘው።

 በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ በኬንያ የሚገኘው የኢኤፍኢ የስፔን የዜና ወኪል ወ/ሮ ሉቺያ ብላንኮ ያቀረቡት ጥያቄ «ጦርነቱ ሱዳን ውስጥ ከጀመረ ከአንድ አመት በኋላ ቻድ የደረሱት ስደተኞች ሁኔታ ምን ይመስላል? እንዲሁም ኢትዮጵያን በተመለከተ ከኦሮሞ እና ከአማራ ግጭት ጋር በተያያዘ በአገሪቱ ያለው የመፈናቀል ሁኔታ ምን ይመስላል? እና ባለስልጣናት ስለ እነዚያ ግጭቶች ምን ነገሩዎት? » የሚል ነበር ።የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሕዝብ፣ የስደተኞች እና የፍልሰት ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጁልዬታ ቫልስ ኖይስ ሲመልሱ፡ «እሺ፣  ከቻድ ልጀምር። ወደ ቻድ የሚደርሱ ስደተኞች ሁኔታ በጣም አስከፊ ነው። ከለበሱት ልብስ በቀር ምንም ማለት ይቻላል ይዘው እየመጡ  አይደለም። እየደረሱ ያሉት በመንገድ ላይ ተጎጂ ከሆኑ በኋላ ነው። እጅግ በጣም ብዙ ፍላጎቶችና ከፍተኛ የስሜት ቀውስ ይዘው እየመጡ ነው; ብዙዎቹ በፆታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት፣ ወሲባዊ ጥቃት ያተረፉ ናቸው። ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት 90 በመቶ የሚሆኑት ሴቶችና  ህጻናት ጥልቅ ፍላጎት ያላቸው  ሲሆን በጣም ጥቂት የራሳቸው ሀብቶች  የያዙም  አሉ ። ከዚህም በላይ በ2004 ከዳርፉር ያለውን ሁኔታ በመሸሽ ቻድ የገቡ ስደተኞች  አግኝቻቸዋለሁ፤ የኖሩበት ሁኔታ አስከፊ ቢሆንም ዛሬ የሚደርሱት ስደተኞች ሁኔታ እጅግ የከፋ መሆኑን በአንድ ድምፅ ተናግረዋል። ስለዚህ ከባድ ፈተና ነው። በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ትልቁ የሰብአዊ ቀውስ ነው፣ እናም ይህን ግዙፍ ፈተና በከፍተኛ ሁኔታ ለመቋቋም ሲሞክሩ የቻድ ህዝብና መንግስትን ለመርዳት ይቻል ዘንድ የበርካታ ሀገራት ምላሽ የሚያስፈልገው ቀውስ ነው የተከሰተው። »

«ኢትዮጵያ ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት የተለያዩ ጉዳዮች አሏት። በእኔ እምነት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ 27 አገሮች ስደተኞች አሏት፤ ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ሌሎች በርካታ ስደተኞች አሉ። የሱዳን ስደተኞችንም ተቀብለዋል ነገርግን የትም ቦታ ይሁን ወደ ቻድ እየደረሱ ካሉት ሰዎች ቁጥር ጋር አይቀራረብም።»

«ኢትዮጵያ ውስጥ ግን የተለያዩ ችግሮች አሁንም አለ - ትልቁ የሰብአዊ ችግር - የአማራ እና የኦሮሞ ተወላጆችን ጨምሮ የተፈናቀሉ ዜጎች ጉዳይ ነው። እኔ እዚያ በነበርኩበት ጊዜ ስለነዚያ ሁኔታዎች ተነጋገርናል። የአሜሪካ ድጋፍ ለሁሉም ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ማዳረስ ነው። በቻድ ውስጥ ካሉት በተለየ ግን በኢትዮጵያ ውስጥ በምናቀርበው የሰብአዊ ፍላጎቶች የገንዘብ ድጋፍ በማድረጋችን ኩራት ተሰምቶኛል። ስደተኞች በተገቢው ሁኔታ ነው  የተያዙት።ዩናይትድ ስቴትስ ይህንን በመደገፍ ኩራት ይሰማታል ።ልክ እንደ ቻድ ሁኔታ ከሌሎች መንግስታት ፣ ሌሎች ድርጅቶች ፣ በዚህ የሰላም ልማት ትስስር ቦታ ላይ በመስራት ፣ የዓለም ባንክን ተሳትፎን በማግኘት  አዳዲስ መፍትሄዎችንና ድጋፍ ማድረግ  ይጠይቃል። የግሉ ዘርፍ. ስለዚህ በሁለቱም ሀገራት ያሉትን ሁሉንም ፍላጎቶች ለማሟላት ከበቂ በላይ ስራዎች አሉም ነበሩም - ሁለቱንም ሀገራት ለመጎብኘት እና ምላሹን ለማየት እድል በማግኘቴ የሁለቱንም ሀገራት መንግስታት አመሰግናለሁ። ነገር ግን እዚያ በነበርኩበት ወቅት ባየሁት ስቃይ ራሴን አዝኜ ተመለስኩኝ፣  የበለጠ ለመስራት እና በሌሎች ሀገራት ያሉ አጋሮቼን የበለጠ በጠንካራ ወይም በከፍተኛ ሁኔታ ምላሽ እንዲሰጡ ለማድረግና ለማሳመን ተስፋ አለኝ። የፍላጎቶቻቸውን  መጠን ለማሟላት እጥራለው  » ብለዋል።በመጨረሻም የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሕዝብ፣ የስደተኞች እና የፍልሰት ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጁልዬታ ቫልስ ኖይስ ።  ሁሉም ሰው ትኩረት ስለሰጡኝ ማመስገን እፈልጋለሁ። እነዚህን (የማይሰሙትን) ለሕዝብ ለማድረስ ለምታደርጉት ነገር ሁሉ ላመሰግናችሁ እፈልጋለሁ  » በማለት ከጋዜጠኞች የቀረበላቸው ጥያቄዎች  አጠናቀዋል።

በሌላ በኩል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሃፊ አሚና መሀመድ በኢትዮጵያ የተሰበረውን ተስፋ አስቆራጭ ነገር  መልሶ ለመገንባት ድጋፍ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሃፊ ይህንን የገለፁት ለአምስት ቀናት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ በትግራይ፣ በአማራ፣ በሶማሌና በአፋር ጉብኝታቸው  ማጠቃለያ  ላይ ነው።

«ኢትዮጵያ ውስጥ መተማመን ፈርሷል፣ እናም ያንን እምነት መልሶ ለመገንባት ለህዝቦቻቸው ሰላምን መልሶ ለመገንባት አገሪቱን፣ አመራሩንና ህዝቡን የምንደግፍበትን መንገድ መፈለግ አለብን።» ሲሉ አሚና ተናግረዋል።

ጣት መቀሰር አለመኖሩን የሚናገሩት አሚና «ይህም ማለት ለተፈጸመው ግፍ ተጠያቂው ሁሉም ሰው ነው ማለት ነው። አሸናፊነት አስፈላጊ ባልሆነበት አስከፊ ግጭትና አሳዛኝ ሁኔታ ባለበት ሀገር  ሰላም  ወሳኝ ነበር።»ብለዋል።

አሚና በልጆቻቸው ፊት የተደፈሩና በቡድን የተደፈሩ ሴቶችና ልጃገረዶች ላይ የሚደርሰውን ስቃይ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ጦርነት አፋጣኝ ማቆም እንዳለበት ጠይቀዋል።

«ኢትዮጵያውያን ሴቶች ሊታሰብ በማይቻል ሁኔታ ተጎድተዋል። በጣም በከፋ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ሴቶች ላይ ምን እንደተፈጠረ መገመት አይችሉም። ይህ ደግሞ በክልል ሳይሆን በክልሎች ነው።» ሲሉ ተናግረዋል።

«እኔ እንደማስበው ያለ ጥርጥር ፍትህና ተጠያቂነት መሰማት ያለበት ነገር ይመስለኛል። እኔ እንደማስበው ይህ የብሔራዊ ውይይቶች የመጀመሪያ ማዕከል አካል ነው። በመላ ሀገሪቱ ለደረሰው ግፍ ሳይታረቁና ጥፋተኛ የሆነው ወገን  ካልተጠየቁ ዘላቂ ሰላም ማምጣት አይችሉም። እናም በዛ ክልል ጣት መቀሰር የለም እያልኩ ያለሁት ለዚህ ነው።ጥፋተኛ ብትፈልግ ሁሉም ተጠያቂ ነው። ድንበሮችና ክልሎች ተሻግረው ነበር ጥፋትም የተፈጸሙት። ተጠያቂነትም መሰማት አለበት። » ብለዋል።

ይሁንና የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ በሀገሪቱ ያለውን ግጭት ለማስቆም የተቀናጀ ጥረት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።  አበቃው ።ቸር እንሰንብት !