ኢትዮጵያችንን ያቆሸሸው ዘረኝነትና የእርስ በእርስ ጦርነት !


ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ (ጮራ ዘአራዳ)

(ደራሲ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሀያሲ)

 ኢትዮጵያ ለጥቁሮች ፈር ቀዳጅ የሆነው  የዓደዋ በዓል ለ128ኛ ጊዜ  እንደ በፊቱ መላውን የአዲስ አበባ ህዝብ  ባያካትትም አድዋን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች በሀገራችን ተከብሮ ውሏል።ይህ የድል ቀን ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለበርካታ አፍሪካውያን የቅኝ ግዛት ተጋድሎ  ያደረገነውን  አስተዋጾ ከፍተኛ መሆኑን ለዓለም ያሳየንበት በመሆኑ ልዩ ስፍራ ይሰጠዋል።በአድዋ ጦርነት ዘር ፣ኅይማኖት ፥ብሄር ሳይለያዩ ቀፎው  እንደተነካበት ንብ  በአንድነት በመቆም ለሀገራቸው  አባቶቻችን የቆሙብት ነበር።ዛሬ ግን በብሄርና በጎሳ እየተቧደንን እርስ በእርስ  እየተፋለምን የጥቁር ህዝቦች ድል የሆነውን አድዋን ጥላሸት እየቀባነው  ነው  የምንገኘው።   

  በየጥቂት ቀናቶች ውስጥ  የእልቂት  ወሬዎችን በአማራና  በኦሮሚያ ክልል እየሰማን ነው ።  መንግስት የራሱን ህዝብ ለመቆጣጠር  በሚል ምክንያት አማፂ ኃይሎችን ለመምታት ሰው  አልባ አውሮፕላኖችንና ጄቶችን ጭምር እየተጠቀመ  ነው።  በአሁኑ ወቅት ሁለቱ ክልሎች   የሰው  እርድ  የሚታይበት እየሆ ነ እያየን  ነው።

 ይህ የእርስ በእርስ ጦርነት እያየን ያለነው አዲስ ነገር አይደለም።  የኢትዮጵያ መንግሥት የተገነባው በኦሮሚያና በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች በተፈጠረው  የብልፅግና ፓርቲ ነው።  ዛሬ፣ ይህ ገሃነመናዊ የሕይወት ጥፋትን ለማቆም  የኢትዮጵያ መንግሥትም ሆኑ አማፂያን በሀገራችን ላይ ሰላም ለማምጣት እንደ ሰለጠነ ሰው ችግሮቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ ለምስጊኗና ሁሌ ከጦርነትና  ከድህነት ለማትወጣው  ሀገራቭንና ለህዝቧ ሰላምና አንድነት መወያየት  ቅድሚያ ሊሰጡት የሚገባ ጉዳይ ነው። 

  በሀገሪቱ ውስጥ እየታየው ያለው የእርስ በእርስ ጦርነት እስከአልተቋጨ ድረስ በኢትዮጵያ ሰላም ይፈጠራል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው።  ዓለም ያልተረዳው ነገር ቢኖር ይህ ያለፈው የአሁኑና ምናልባትም በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የወደፊትም ጭምር የታሪክ ጠባሳ ሆኖ የሚቀር አስከፊ ድርጊት እያየን ነው። የሀገራችን መሪዎች ዛሬ ብቻ ሳይሆን ከጥንት ጀምሮ  ለአንዳንዶች የያዙት ስልጣን  እንደ  ታሪካዊ መብታቸውና መለኮታዊ እጣ ፈንታቸው  አድርገው  ሲመለከቱ ነው  የሚታየው።ይህ ደግሞ ከውይይት ይልቅ ወደ ማናቆር ከዛም ወደ ጦርነት እንድንገባ አደርጎናል። ለዚህ ነው  ጦርነት ለአንዳንዶች በፊልም የምናየው የግላዲያተሮች ጀብዱ የሚታይበት ለሌሎች ደግሞ  እንደ ታሪካዊ ቁስላቸውና ከዛም  አልፎ  ገዳይና ክልሎቹን  ገሀነም  አድርገው  እንዲመለከቱና ለምን በዚህ ክልል ተወለድኩ  እስከ ማለት የሚደርሱበት ደረጃ ላይ ነው የደረስነው።

 ለኢትዮጵያ የሚያስቡ ወገኖች ሁሉ ይህንን ያልተቀበረ የእርስ በእርስ ጦርነት ታሪክ በማውገዝ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ ውይይትና ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲመጣ  መጮህ አለባቸው።  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ንፁሀን ዜጎች በተለይ ሴቶች፣ ህጻናትና አረጋውያን ወገኖቻችን አሁንም  ለአደጋ  ከመጋለጥ አልፈው በሰቀቀን የሚኖርበት ክልሎች  እየሆኑ እያየን ነው።

 ያለፈው  ታሪክ አልቆመ’ም 

 የታሪክ ምሁር ሃሮልድ ማርከስ የኢትዮጵያ መንግሥት በዚህ መንግሥታዊ አመራር ዓመፅ እንዴት እንደተገነባ በ1975 “የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ሕይወትና ዘመን” በተሰኘው መጽሐፉ ላይ እንዲህ አስፍሮት ነበር።  ከዛሬ 130 ዓመት በፊት ስለ ኢትዮጵያ የሚናገረውን የደረቀ፣ ተራ መጽሃፍ ማንበብ በጣም ያማል ምክንያቱም ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ኦሮሚያ፣አማራ፣ ሌሎች ቦታዎች ያለው የእርስ በእርስ ጦርነት እሱ  ከጻፈው  ጋር ነገስታቶቹና ባላባቶቹ ለስልጣን ያደርጉት የነበረውን የእርስ በእርስ ጦርነት ስለሚመስል ነው።  ከዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች አውዳሚ ኃይል በቀር ምንም የተለወጠ ታሪክ ከበፊቱ ጋር ያለ አይመስልም።  በአሁኑ ወቅት  የፋኖ አማፂ ኃይልና ኦነግ ሽኔ ከመንግሥትን ጦር ኃይል ጋር የሚያደርጉትን ውጊያ በአንክሮ እንድንመለከትና ግንባር ቀደም ሆነው እንዴት እየተዋጉት እንደነበረ በፊት ከጻፈው ጋር የሚመሳሰል ታሪክ ነው  ያለው። 

«ጊዜያዊ ተዋጊዎች የሆኑት  የንጉሱ አፈንጋጭ የሆኑ አማራዎች ሙሉ በሙሉ ከመሬት ርቀው  ይኖሩ ነበር። በእነሱ ጥበብ። ጦር፣ ጎራዴ እና ጋሻ ታጥቀው  ከዋናው [ንጉሠ ነገሥት] ጦር ቀድመው መረጃ አቅርበው ከንጉሥ ጦር አፈንግጠው ጠላት ሚዛኑን እንዲጠብቅ አድርገዋል።  ድንገተኛ ጥቃት ፈፀሙ  እነዚህ ተዋጊዎች የንጉሱን ጦር ወደራሳቸው ጨምረዋል… አንድ ጊዜ በጠላት ግዛት ውስጥ አማራዎች ከዋናው ጦር ግንባር ቀደም ብለው የአንድ ወይም ሁለት ቀን ጉዞ በማድረግ በረሃውን ገጠራማ አካባቢ አወደሙ…  ይሁንና ተደብቀው ስለነበር ወድያውኑ በጥይት ተመቱ።’» ይለናል።

 በትግራይ ክልል ያየነው አስከፊው  ጦርነት  ዛሬ  ደግሞ  በአማራና በኦሮሚያ ክልል እያየን ያለነው የእርስ በርስ ጦርነት ይህንን የሚያሳይ ነው።  የምኒሊክ  የሸዋ ጦር የአማራን ሽብር እንዴት እንደሚከተል በግልጽ እንዲህ ሲል ጽፏል።

 «[ወታደሮች] ሴቶችንና ልጆችን ይዘው ወደ ካምፕ ይመለሱ ነበር።  በምርኮ የተያዙ ወንዶችና አረጋውያን ተገድለዋል።  የዘመቻው (ዘመቻ) ከባድነት ሁሉንም  ተቃውሚዎች  ለማጥፋት ያለመ  ነበር…’» ብለዋል።

 ሠራዊቱ ወደ ፊት በተጓዘ ቁጥር ከፍተኛ ውድመት ያጋጥመው ነበር። ቤቶች ተቃጥለዋል፣ ሰብሎች ወድመዋል ፣ሰዎች ተገድለዋል።  ካምፑ በምርኮና በእስረኞች እስኪሞላ ድረስ ሁለት ወይም ሶስት የኃይል ጥቃቶች በየትኛውም ዘመቻ ተከስተዋል።  የቀሩት የጠላት ባለስልጣናት እጅ ለመስጠት ሲወስኑ ብቻ ነበር ዋና አዛዦቹ ጥቃቱን ያስቆሙት።

 ከመደበኛው  የመገዛት ተግባር በኋላ፣ አሁን የምኒልክ ተገዢ  በሆነው  ሕዝብ ላይ መዝረፍና ማቃጠል ተከልክሏል።  ከዚያም ንጉሱ ወይም ተተኪው የሸዋን ባላባት ከአገልጋዮቹና ከአንዳንድ ቅኝ ገዥዎች ጋር በማደራጀት የተበላሸውን መሬት እንዲያስተዳድሩ መድበው  ዋናው ጦር ወደ ቤቱ ተመለሰ።  ደህንነቱ በተጠበቀ ክልል ውስጥ ከገባ በኋላ ምርኮውን ተከፋፈሉ፣ ንጉሱም  ከጠቅላላው  ጦር ከግማሽ እስከ ሁለት ሶስተኛውን ተቀብለዋል… ምኒልክ ይህን ትርፋማ  የጦር ድል  በተቻለ መጠን ወደ ሸዋ ለመቀየር ቢፈልጉም፣ የመስፋፋቱ ግፍ የነበራቸው  ወገኖች ግን ሁኔታውን  አስፈራርተው  ነበር። »

ዛሬ የምናየው  ምሳሌ ይህ ነው፡ ኦነግ ሽኒናፋኖ እንዲሁም  ሌሎች የማንነት ታጣቂዎች ድንበር ተሻግረው በኃይል ሲያጠቁ።የኅይማኖት አባቶችንና መምህራኖችን ሲገድሉ(ፋኖም ሆነ ኦነግ ሸኔ በየፊናቸው ይህን አስተባብለዋል።እኛ አይደለንም መንግሥት ከዚህ በፊት  ያሰለጠናቸው ሚሊሻዎች ናቸው ይላሉ።)  የፌዴራል መንግሥት ይህንን እልቂት ለጥቅሙ መጠቀሚያ ማድረግና በሰው ህይወት ላይ ከፍተኛ ውድመትና የአካባቢ ኢኮኖሚ ውድመት እስኪሆን ድረስ መጠበቅ የለበትም። እነዚህን አሳማሚ  የሆኑ እውነታዎችን ደግሞ  መካድ  የለብንም ።

 ብዙ ሰዎች፣ በተለይም  እንደ ፋኖና ኦነግ ሽኔ  ባሉ ቡድኖች፣ መንግሥት እንደ ጠላት አድርገው  ማየት የለባቸውም  ።  ስለዚህ  ፋኖም ሆነ ኦነግ ሽኔ  ጦርነት ማድረግ እንደ መብትና ያላለቀ እጣ  ፈንታቸው አድርገው  ማየትም  ተገቢ  አይደለም።የአንድ ተራ  ግጭት ብቻ አድርጎም  መንግሥት ማየት የለበትም ።  ለዚህም ነው  እነዚህ አሰቃቂ እልቂቶች በየክልሎቹ የምናየው በአጋጣሚ  የተከሰቱ ናቸው ብሎ ለመቀበል የሚከብድ  ሁኔታ ላይ ነው  ያለነው። ለምን ቢሉ የሰዎችን እልቂትና ከመንግሥት ጋር እየተደረገ ያለውን ጦርነት  በስማርት ፎኖችንና በላፕቶፓችን ላይ  ማህበራዊ ሚዲያዎች ባሉበት በአሁኑ ወቅት በብዛት  ለማየት መቻላችን አንዱ  ለእውነታው  ማሳያ  ነው።

 ጠ/ቅላይ ሚኒስትር አብይ በትግራዩ ጦርነት ፋኖ ለእሳቸው ወሳኝ ኃይል በነበረበት ወቅት በተለይም በትግራይ ላይ ባደረጉት የጦርነት ዘመቻ መላውን ሰላማዊ ህዝብ በማታገል ከፍተኛ አስተዋጾ አድሮጋላቸው ነበር።አሁን ደግሞ በተቃራኒ ሆኖ እሳቸው  ከሚመሩት ጦር ጋር ቀርቧል።ዶክተር  ዐቢይ እያወቁ ያንን አጠቃላይ የጦርነት አስተሳሰብ ከ130 ዓመታት በፊት ጀምሮ የነበረውን የንጉሠ ነገሥታዊ መንግሥት ግንባታ ፕሮጀክት እንደገና እንዲሠራ  ያደረጉ ይመስላል።

 ለዚህም ነው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን «ከኢትዮጵያ» ጋር ምንም ግንኙነት መፍጠር የማይፈልጉት።  «ኢትዮጵያዊ» ማለት የኢትዮጵያ ግዛት አካል መሆን ማለት ከሆነ ምን እንደሚመስልና የት እንደሚሄድ ያውቃሉ  የሚባለው።  ለዚህ ነው  ያንን  የቅዠት  ያለፈ ታሪክ መደጋገም  እንደማይፈልጉ መረዳት ይቻላል።

 በመሆኑም የዛሬው የኢትዮጵያ መሪዎች ወሳኝ ተግባር በአሸባሪነት የተፈረጁትን አካሎችና ሚሊሻዎች  በጦርነት ማሸነፍ አለመቻላቸው ነው። በፌዴራል መንግሥት የበላይነትና በፌዴራል እንዲሁም  የክልል  ኢኮኖሚዎች ላይ ዘረፋ የድህነት ጅምላ ጭፍጨፋ ስንመለከት የቀድሞ  የንጉሠ ነገሥቱን ታሪክ እንደገና በትውስታ እንድንመለከተውና  የወደፊት ዕጣ ፈንታ ከወዲሁ መግለጽ አለመቻሉን ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል የተባለውም  ለዚህ ነው ።  

ለዚያ ራዕይ ማሰብ የሚችሉና የሚሟገቱ መሪዎች ሀገሪቱ እንደ ቀድሞው የሩሲያ ግዛት እራሷን እንዳታፈራርስ የመከላከል ኃላፊነትና ግዴታ እንዳለባቸው  መገንዘብ  ግን አለባቸው ።

ኦነግ ሸኔና ኦሮሚያ ?

ኦነግ ሽኔ የኢትዮጵያው  ጠቅላይ ሚንስትር የትውልድ ሀገራቸው  በሆነው በኦሮሚያ ችግኙ ተተክሎ ና ተፈጥሮ  በራሳቸው  ጓሮ ውስጥ  ያደገ አማፂ ድርጅት  ነው።

 ኢትዮጵያችን  ውስጥ ከፍተኛ ቀውስ ተከስቷል።በተለይም  በአማራና በኦሮሚያ ክልል። በሰፊው የኦሮሚያ ክልል አንድን ብሄር ተኮር ያደረገው ጭፍጨፋ ቀጥሏል። በተለይም የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እምብርት የሆነችው ኦሮሚያ  የፖለቲካና የጎሳ ውዝግቦችና  ግጭቶች  እየተባባሱ ነው።

 የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ታጣቂዎች በአንድ ወቅት ሊደርሱባቸው የማይችሉትን ከተሞች ሲዘዋውሩና በአዲስ ምልምሎች ለማጠናከር ሲፈልግ የቢቢሲ ጋዜጠኛ  «የምረቃ ስነ ስርዓቱን» ሲያካሂዱ  በቦታው ተገኝተው  ተመልክታለች።መንግስት ግን ንግግሮች እንዲቋረጡ ባለመፍቀዱ በወታደሮች ማጠናከሪያ ዕለት ሰው አልባ አውሮፕላኖች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን  መመልከቷን ጋዜጠኛዋ  ገልጻለች ።  

 ከአደገኛው ኮክቴል ጋር ተያይዞ ብዙ የሚፈሩት የአማራ ብሄር ተወላጆች ታጣቂዎች ወደ ኦሮሚያ ዘልቀው በመግባት አማፅያኑን ለመፋለም እንደደረሱ በስፋት ይታመናል።  ኦኤልኤ (OLA) ራሳቸውን የኦሮሞ ብሔርተኝነት አቀንቃኞች አድርገው በመግለጽ፣ ከጥቂት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እንደ ገዳይ የሚታዩ እንዳልነበሩ ዛሬ ደግሞ  የተቃዋሚዎች መገናኛ ብዙኃን ሳይቀር ተወዳጅነትን  እያተረፉ  ነው።

 በኦሮሚያ ክልል ባለፉት አምስት ወራት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። ሲል በመንግስት የተሾመው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ሲናገር ቆይቷል።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ደግሞ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ብሏል።  .

 በግጭቱ ውስጥ ያሉ ሁሉም ወገኖች የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል መባሉን አይቀበሉም።

 ባለፈው  አመት ህዳር ወር የታየው  ጥቃት የኦኤልኤ(OLA) ጥንካሬን በግልፅ ያሳየ ሲሆን ተዋጊዎቹ ነቀምትን በወረሩበት ወቅት ጠቅላይ ሚ/ር አብይ የትውልድ መንደር ዋና ከተማ  ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ የሚወስዱ መንገዶች በመቁረጥ ወደ አዲስ ወደ ተገነባው ግዙፍ ግድብ ለማምራት የሚያስችል ቆረጣ አማፂው ኃይል አድርገው  ሁሉ ነበር።እየገፋ የመጣውን የአማፂ ኃይሉንን ለመግታት መንግሥት የራሱን እርምጃ በመውሰድ አብዛኛውን አካባቢዎች ከአማፂው አይል ለማፅዳት የቻለ ቢሆንም አሁን ግጭቱና ግድያው  በክልሉ እንደ ቀጠለ ነው።

ድሮኖች

 የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት የኦነግ ሽኔንና የፋኖን  ግስጋሴ ለማስቆም ወታደራዊ ኃይሉ በትግራይ ተጠቅሞ የነበረውን አይነት ስልት እየተጠቀመ ነው የሚል  ሁኔታ  በሰፊው  እየተነገረ ነው  የሚገኘው ።  መንግስትና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)

 «በትግራይ ጦርነት ምንም እንኳን የሲቪል ኢላማዎችን ቢመታም ሰው አልባ አውሮፕላኖች ለከባድ መሳሪያዎችና ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ብዙ ጊዜ ይገለገሉ ነበር። ነገር ግን በኦሮሚያ ክልል አማፅያን ከተሞችን ከያዙ በኋላ በኦነግ ሽኔ የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ተደርገዋል።  » ሲል የኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ የኢትዮጵያ ተንታኝ ዊልያም  ዴቪሰን ተናግረው  ነበር።

 በአማራና በኦሮሚያ ክልል አማፂያኑን ለመምታት የአየር ድብደባዎች መፈፀማቸው  ተገልጿል።

 የመንግሥት ወታደሮች ፋኖንና  ኦኤልኤን(OLA) ይደግፋሉ በሚል ጥርጣሬ ሰዎችን በጥይት ተተኩሰው  ተገድሏል ተብሎም  በየሚዲያው እየተገለፀ ነው የሚገኘው።  በተጨማሪም   ከፋኖና ከኦኤልኤ(OLA) አማፂ ኃይሎች ጋር የተቀላቀሉትን የወጣቶችን ዘመዶችን ጨምሮ የአካባቢው ሰዎችን ያለፍርድ ለረጅም ጊዜ መንግስት  አስሯል በማለትም  በየፊናቸው  እየከሰሱ  ይገኛሉ።በእርግጥ  ፋኖ  እንደ ኦነግ ሸኔ በአንድ እዝ የሚታዘዝ አይደለም።መሪዎቻቸው  ብዙ  ናቸው።ስለዚህ እንደ ኦነግ ሸኔ በጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ  ብሎ  ለመነጋገር አስቸጋሪ መሆኑን አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በአንድ ወቅት መግለፃቸው  አይዘነጋም።

 ማፈናቀል

 መቀመጫውን በእንግሊዝ ያደረገው የኢትዮጵያ ተንታኝ መብራቱ ከለቻ በአንድ ወቅት እንደገለፀው  በ2018 እ.ኤ.አ ጠ/ቅላይ ሚኒስትር አብይን ስልጣን እንዲይዙ ባደረገው ትልቁ የኢትዮጵያ ብሄረሰብ በሆነው የኦሮሞ ተወላጆች ልብና አእምሮ ላይ በሚደረገው  ጦርነት በመንግስት ላይ የሚፈጸመው ግፍ መንግስት አጸፋዊ እርምጃ  ሊወስድ እንደሚችል አስጠንቅቋል።

«ኦኤልኤ (OLA) ይህን እንደ ፕሮፓጋንዳ ስልት ብቻ ሳይሆን ታጣቂዎችን ለመመልመል ሊጠቀምበት ይችላል። ነገር ግን በአካባቢው ህዝብ ድጋፍ ለማግኘትና ደካማ አቅርቦታቸውን [መሠረታዊ ፍላጎቶችን] ለማስፋት ሊጠቀምበት ይችላል።» በማለት ስጋቱን ገልፆ ነበር ።

 በዋናነት በምእራብ ኦሮሚያ ከሚገኙት የደን መሸሸጊያ ቦታዎች በሚካሄደው የሽምቅ ውጊያ ላይ ያተኮረው  የ ኦኤልኤ (OLA) አመጽ በኢትዮጵያ ማህበረሰብ ውስጥ ያለውን ጥልቅ ቁርጠኝነት ያሳያል ።ከ111 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖርባትና በአፍሪካ  በህዝብ ብዛት ሁለተኛዋ ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያ  እልፍ አእላፍ ብሄረሰቦች  ያለባት ያለማቋረጥ የሚፎካከሩ ህዝብ ያላት  ሀገር ነች ።  

ለመሬትና ለስልጣን

 እያንዳንዳቸው  ኢትዮጵያውያን በማንነታቸው 

አጥብቀው የሚኮሩ፣ ባህላቸውንና ቋንቋቸውን አጥብቀው ይይዛሉ።  አማርኛ  ቋንቋ  ደግሞ  ብሔራዊ  ቋንቋ ሆኖ  በአብዛኛው ቦታ እየገላገለ ነው።

 ጠ//ሚ//ር አብይ ብሄራዊ ማንነትን ለማስፈንና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጎሳ አጋርነታቸውን እንዲተው ለማድረግ ሞክረዋል።ነገር ግን ጥረቱን ለኦሮሚያ “ራስን በራስ ማስተዳደር” በሚለዉ ኦኤልኤ(OLA)  ሳይቀር ከፍተኛ ተቃውሞ  ገጥሟቸዋል።

 ይህ ምን ማለት እንደሆነ አማፂ ኃይሉ በግልፅ አስቀምጦ ባያውቅም ተቺዎቹ ኦሮሚያ እንድትገነጠል በማድረግ ኢትዮጵያን ለመበታተን እፈልጋለው የሚል አማፂ  ኃይል  ኦኤልኤ(OLA)  እንደሆነ  ይናገራሉ ።እንደ ምክንያት የሚያደርጉት በቅርቡ በፌድራል መንግሥትና በአማፂ ኃይሉ ተደርጎ ውይይት ያለስምምነት መበተኑ እንደ ዋንኛ ምክንያት አድርገው  ያቀርባሉ።

 ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ  ወቅት ሥራ አጥነት በከፋ ሁኔታ በሀገሪቱ በዝቶ እየታየ ይገኛል። ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ጋዜጠኞች ታፍነዋል ።ይህ መቆም እንዳለበት ሁሉም ወገኖች ይስማማሉ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአብዛኛው  የኢትዮጵያ  ህዝብ ተቀባይነት ያላቸው ቢሆንም ተቀባይነታቸው በፊት ስልጣኑን እንደያዙበት ጊዜ ግን አይደለም ።ሰው ከዚህ በፊት በመንግሥት የተገባው ቃል ተግባራዊ ባለመሆኑ የተነሳ ከእሳቸው  ድጋፍ ሸርተት እንዳለ ሲናገሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደግሞ  አንድ የአርሴናል ወይም የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊ ቡድኑ ሲሸነፍ ድጋፉን እንደማይቀይር ሁሉ ችግር በሚኖርበት ወቅትም ከጎናቸቅው ሊሆን እንደሚገባም ይናገራሉ።የኢትዮጵያ ህዝብ ከሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች ጋር ተፈቃቅሮና ተከባብሮ መኖርን  ከዚህ በፊት  የለመደ ህዝብ ነው።ሀገሩን ከማንም  በላይ የሚወድ ህዝብ  ለመሆኑ እማኝ መቁጠር አያስፈልግም ።ሁሉም ባንዲራውን ይወዳል።ግን አሁንም ልብ ለልብ አንድ አይደለም።የእርስ በእርስ ጦርነቱም  መንስሄ ይኸው  ነው።

ጥንካሬውን መገመት

 «ባለፉት ጥቂት አመታት መንግስት በህጋዊ የኦሮሞ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ እያደረሰ ባለው ጭቆና ምክንያት የእንቅስቃሴውንና የተፋላሚውን ቁጥር ማስፋት ኦነግ ሽኔ ችሏል።» ብለዋል ሚስተር ማርክስ ዴቪሰን ይናገራሉ።  አሁንም ንቅናቄው የፌደራል መንግስት ይቅርና ለክልሉ መንግስት ስልጣን ስጋት ሊሆን የሚችልበት ደረጃ ላይ ግን አልደረሰም  ባይ ናቸው።

 የኦኤልኤ (OLA ) ተዋጊዎች ቁጥር ግልጽ ባይሆንም አቶ መብራቱ የገለጹትን «ፈጣን ፍጥነት ያላቸው ጥቃቅን እንቅስቃሴዎችን በተራዘመ ና ዝቅተኛ ግጭቶችን በመቃወም የመንግስትን ኃይል ለማዳከም” የሚሠራ በመሆኑ ከፍተኛ ሊሆን አይችልም። ‘»ሲል  ይገልጻል።በፋኖም በኩል ተመሳሳይ ነው።

የሚሊሻ ጦርነት

 ቀውሱን ለማባባስ አማፂያኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሀን ዜጎችን ገድለዋል።አብዛኞቹ ገበሬዎችን የአማራ ብሄር ተወላጆች ይገኙበታል።ፋኖም በተመሳሳይ ሁኔታ በኦሮሚያ ክልል አጸፋዊ እርምጃ ይወስዳል። በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ  ተወላጆች በአማራ ካምፖች ውስጥ  እየኖሩ ነው።

 የአማራ ታጣቂዎች – ፋኖ እየተባለ የሚጠራው – ወደ ኦሮሚያ የሚገባው  የአማራ ተወላጆችን ለመከላከል ነው  በማለት ይገልጻል።  በምዕራብ ኦሮሚያ በተለያዩ ወረዳዎች በሚገኙ አምስት ከተሞች ላይ ወረራዎችን ጨምሮ ወንጀሎችን ተፈጽመዋል በሚል ሁኔታ ፋኖ  መንግሥት  ላይ ክስ   ያቀርባል።ወደ ትጥቅ ትግልም  የገባው በተለያዩ ጊዜያት በአማራ ብሄር ላይ በኦሮሚያ ክልል እየተፈፀመ  ያለው  ዘርን ያተኮረ ጭፍጨፋ  ዋንኛው  ነው።

 ‘

እ.ኤ.አ ህዳር 2020 የፋኖ ሚሊሻዎች ከትግራይ ሃይሎች ጋር ሲፋለሙ የቆዩበትና የአማራ ክልል መንግስት በግብርና የበለፀገውን ምዕራብ ትግራይን እንዲይዝ የረዱበት ሁኔታ አሁንም ከትግራይ ጋር ተመሳሳይነት  ያለው ነው ብለው  ይጨነቃሉ።

 አማሮች ግን ፋኖዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ  ይገባል የሚለውን ሁኔታ የሚክዱ ሲሆን « ሚሊሻዎቻቸው በኦሮሚያ መንግስት ሰልጥነው ማህበረሰባቸውን ከዋናው ከኦኤልኤ(OLA)  ጥቃት እንዲከላከሉ ከአራት አመት በፊት  በመንግሥት ስልጠና የወሰዱ  ናቸው   እንጂ እኛ አይደለንም  »  ባዮች ናቸው።

 ብዙ አማሮች፣ እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይን የሚደግፉ ኦሮሞዎች በኦነግ ሽኔና በህወሓት ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬ እንዳላቸው በመግለጽ ሁለቱ ተባብረው ስልጣን ለመያዝ ባለፈው አመት ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን ጠቁመዋል።

 ከዚያም የትግራይ ተዋጊዎች ወደ መሀል ሀገራቸው በማፈግፈግ ከፌዴራል ወታደሮች ጋር ከፍተኛ ጦርነት የገጠሙ ሲሆን  ሁለቱ ወገኖች በህብረቱ  ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጫና እስከሚደርስባቸውና በፌድራል ጦር ሽንፈትን በቀመሱበት ወቅት በኦሮሚያ ከተከሰቱት ግጭቶች የበለጠ አውዳሚ የሆነ ጦርነት አድርገው  እንደነበር አይዘነጋም።

 ኦኤልኤን(OLA) ከዶክተር ዐብይ መንግስት ጋር  ውይይት  ያደረገ ቢሆንም ስምምነቱ እንዳይሳካ  መንግሥት ፈቃደኛ አይደለም በማለት ይገልጻል። ጦርነቱ አሁንም  እየተባባሰ ነው ።

መንግስት ፋኖንም  ሆነ  ኦነግ ሽኔን « የጠራ የዕዝ ሰንሰለትና የፖለቲካ አጀንዳ የሌላቸው።አሸባሪዎች »  ሲል  ይገልጻቸዋል።

 የኢትዮጵያን “የተረሳ ጦርነት” የሚሉትን በኦሮሚያና በአማራ ክልል ያለውን  ጦርነት ለማስቆም የአለም ማህበረሰብ  መንግሥት እንደ ትግራዩ ጦርነት እንዳስቆሙት ሁሉ ይህንንም  እንዲያቆሙ    ተማጽነዋል።

 ለሦስት አስርት አመታት የዘለቀው  መንግስታዊ ጭቆና  ወደ ሰላምና ዲሞክራሲ ማምራት እንጀምራለን ብለው  የተናገሩት ጠቅላይ ሚ/ር አብይ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሹመት ካገኙበት ጊዜ  ጀምሮ  ቃል ቢገቡም  እጅግ ብዙ  ችግሮች  እየታዩና  እንደታሰበው  እንዳልሆነ እየታየ ነው።

 ይልቁንም የፖለቲካና የጎሳ ቡድኖች አሮጌ ነጥቦችን በማውጣት የወደፊቷ ኢትዮጵያ ምን መምሰል እንዳለባት የተለያዩ አመለካከቶችን በማሳየታቸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመቆጣጠር የታገሉትን አንድነትና  ሰላም  ከመፍጠር  ይልቅ  ጭራሽ በሀገሪቱ  ላይ ውጥረቶች  ተፈጥረው  ታይተዋል። ኢትዮጵያችን ከዚህ ከቆሻሸው   የእርስ በእርስ  ጦርነትና ዘረኝነት በዚህ አድዋ የድል በዓል ሰሞን ሁሉም  ወገኖች ለማስወገድ ቃል በመግባት ሁላችንም ለሀገራችን ሰላም ማምጣት የየበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይገባናል ባይ ነኝ። ለሀገራችን እግዚአብሔር ሰላሙን ያምጣልን።አበቃው !