«ሁላችንም ከኅይማኖትም ከእውነትም ወጥተን ውሸታሞች ሆነናል!»


 ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ

( ጮራ ዘ አራዳ )

(ደራሲ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሀያሲ)

« በአሁኑ ጊዜ ሰው  ሁሉ ማለት ይቻላል ሌላ ሰው  ነው።ውጪው ሌላ ውስጡ  ሌላ ፤ኑሮ ሌላ ህልሙ  ሌላ፤ልቡ ሌላ፤አፉ ሌላ ሁላችንም  ሌላ ሰው ሆነናል ። ከኅይማኖትም  ከእውነት ወጥተናል። »አባ ሳሙኤል  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክራቲያን  የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድ ኦ ኮሚሽን  ሊቀ ጳጳስ

አቡነ ሳሙ ኤል የተናገሩት ይህ አባባል  በአሁኑ ወቅት የሰው ልጅ ከእውነታውና ከኅይማኖቱ እርቆ  እየኖረ  መሆኑን ያሳያል።

ሰዎች  ለምን ከእውነት   ሊርቁ  እንደቻሉ፣ውሸታምን  ሰው  እንዴት መለየት እንደሚቻል ወዘተ. ሳይንስ የደረሰበትን የምርምር ደረጃ ‘ የሚያስቃኝ  በሰፊው  ለዕትመት ካበቃዋቸው  መጽሐፍቶቼ መካከል አንዱ  በሆነው  « ውሸትና ጥንቁልና » በሚለው  መጽሐፌ  ላይ በሰፊው  አትቸዋለው።

በዚህ መጣጥፌ  ግን ስለ እውነት እንጨዋወታለን።

 አንድ  ገበሬ  ያደለበውን በግ  ገብያ ለመሸጥ  አንገቱን አስሮ ወደ ገቢያ እየጎተተ ይዞ ይጓዛል ። እንደምታውቁት ሌባ ብቻውን አይሰርቅም።ወይንም  ማጅራት ሲመታም  ብቸውን ሆኖ አይደለም

 በተለይም  የዘንድሮ ሌባ እንደ በፊቱ የተሰጣ  ልብስ፣በኪስ ውስጥ  የተገኘ ቦርሳና ገንዘብ  ወዘተ. ሳይሆን  አሁን እረቀቅ ያለ  ሆኗል  ሞባይል  ብቻ ነው  የሚፈልገው ።ታዲያ ሲሰርቁም  ሆነ ሲቀሙ  መሐል ላይ ሰውየውን  አስገብተው  ነው።

የነዚህኛዎቹ  የማጭበርበር  ሌብነት ነው። ልክ  ከሜክሲኮ አደባባይ እስከ መስቀል አደባባይ እንደምናየው ፤ አንዱ  ሲሸጥ  ሌሎቹ  ገዢ  መስለው  በጋራ  ሆነው  እንደ ሚ ይጨ ናብሩት   ቁጭ  በሉዎች   እንደሚባሉት  አይነቶች  ናቸው።

እነዚህ  በአካባቢው  የታወቁ ሦስት ቁጭ  በሉ  የሆኑ ጓደኛማቾች   አንድ  ገበሬ  ያደለበውን በግ ለመሸጥ  በጉን እየጎተተ  በመንገድ  ላይ ሲሄድ  ያዩታል።

እነዚህ ሦስት ጓደኛ የሆኑ ሌቦች «ይህን በግ ከዚህ ሰውዬ ላይ እንዴት ብለን ነው  መውሰድ የምንችለው?»በማለት መመካከር ይጀምራሉ።

ከመካከላቸው አንዱ «ለምንድን ነው  ሰውየውን እየጎተትክ ያለኸው  ውሻ ነው

..ምን ልታደርገው  ፈለክ  ?ብለን  በየተራ  አወናብደን ለምን አንጠይቀውም ? ምናልባት   ሰውየውን በምንነግረው  ውሸት አምኖ !.. ይህን ሙ ክት በግ ውሻ መስሎት ሊለቀው  ይችላል» በማለት ይህን  ሀሳብ ያቀርባል።መጀመሪያ ላይ በሀሳቡ መስማማት አልቻሉም ነበር።«በግን የመሰለ ነገር እንዴት ውሻ ነው  ብለን ሰውየውን  ይቀበላል?» ብለው  ትንሽ ከተከራከሩ በኋላ በሀሳቡ ሁለቱ  ጓደኛሞች  « እንሞክር ! »  በሚለው  ሀሳቡ  ይስማማሉ።

ሀሳቡን ያቀረበው  የመጀመሪያው  ሌባ  ወደ ሰውየው  ጠጋ ብሎ « እንዴት ነክ  ጌታው !… የሚ ገርም  ነው ..! እንደ ፈረንጆቹ መሆኑ ነው።እዚህ ገጠር ውስጥ  ውሻ በገመድ እየጎተትክ  የምትሄደው …የጊቢህን ውሻ  እያናፈስከው  ነው  ?…የታደለ ውሻ..የእኛ ሰፈር ውሾች  አቧራ ሲሉ  የአንተ ውሻ ..» በማለት ይነግረውና ወደ ሰውዬው  ሲመለከት ።

በጉን  እየነዳው  የሚሄደው  ሰውዬ  ደንገጥ  ብሎ  « እንዴ!.. ምን ማለት ነው ? ..የምን ውሻ ነው  የምትለው ?… ዓይን አያይም  …ይህን  የመሰለ  ሙክት በግ ..!  ውሻ  ነው  የምትለው  …ይልቅ ዓይንክን ብትመረመር ጥሩ  ነው »  ብሎት በሰውየው  ድርጊት  ተናዶ  ይጓዛል።

 ሌባውም   «ድንቄም  ሙክት በግ…ተሳስታሀል.. ጌታው  !..ይሄ ሙ ክት በግ ሳይሆን ውሻ ነው !.. ዓይንክ  በደንብ  የማያየው  የአንተ ነው  ..ስለዚህ ተመርመረው …»በማለት እያስካካ  ጥሎት  ይሄዳል።

በሰውየው  ሁኔታ  የተበሳጨው ባለበጉ ሰውዬ  ትንሽ  እንደተጓዘ  ሁለተኛውም  ሌባም  በተራው  በግ ወደ ሚጎትተው  ግለሰብ  ቀረብ  ብሎ   ጓደኛው  ያለውን የማጨናበሪያ  አባባል ይደግመዋል « የባሰ መጣ … በዚህ  ገጠር  ያውም  ኢትዮጵያ ውስጥ  ውሻ እረኛ ሆኖ ያገለግላል እንጂ …  ውሻ የሚናፈስበት  …ጊዜ ተጀመረ  እንዴ ? ጌታው  መቼም  ይሄ ውሻ የአንተ አይደለም  አይደል ?   መቼም ፈረንጅ  ቤት   ይሆናል  የምትሰራው?  …!በገመድ እየጎተትክ  ያለውን ውሻ …  ፈረንጆቹ አናፍስ …ብለውክ  ነው ያወጣከው? » በማለት ይጠይቁታል።

ሰውየው  ትንሽ  እንደ መጠራጠር ብሎ  የያዘውን 

ሙ ክት መልከት ካደረገ  በኋላ «እንዴት ነው .…ነገሩ !..ወቸው  ጉድ! …ሰዉ  ሁሉ ጤነኛ አይደለም  ማለት ነው?…ይሄኮ ውሻ ሳይሆን ያሳደኩትና የቀለብኩት ሙክት በጌ ነው! እንዴት ውሻ ነው  ይሉኛል?…  በማለት በመገረም  እያጉረመረመ  መንገዱን ሊቀጥል ሲል። 

 ሌባውም  ቀበል አድርጎ «ጌታው ..ዓይንህን በደንብ  አድርገ ተመርመር !..በግ ሳይሆን እየጎተትክ ያለኸው ውሻ ነው!»ብሎት እሱም  እንደጓደኛው  ከትከት  ብሎ  እየሳቀ ጥሎት ይሄዳል።

ሰውየውም  በሁኔታው  ተገርሞና ተጠራጥሮ  በጉን ያዝ  አድርጎ ከቆመ  በኋላ በደንብ  ዓይኑን አሽቶ  የያዘውን በግ  መመልከት ይጀምራል «ሰዉ  ሁሉ አብዷል ማለት ነው? … ውሻ በየት በኩል ነው  ቀንድ ያለው ? … ውሻ እንዴት ባህ ባህ.. ይላል ?  እነሱ  ናቸው  የተሳሳቱት!.. ውሻ ሳይሆን ያሳደኩት በጌ እራሱ ነው » በማለት በጉን

እየጎተተ  ይዞ ይሄዳል።

አሁንም  ትንሽ  በጉን ይዞ እየጎተተ … እንደ ተጓዘ ሦስተኛው  ሌባ  ይጠብቀውና «ምነው  ጃል!…ውሻ እንደ በግ እየጎተትክ መሄድ ጀመርክ  እንዴ ?…  » ይለዋል።

«አረ ውሻ ሳይሆን በግ ነው »በማለት ይመልሳል።

ሌባውም «ሰውየው  ጤነኛ አይደለም  እንዴ?  የምን በግ ነው!.. ውሻ ነው  እንጂ!.. ከፈለክ ሌላሰው  ጠይቅ ይለዋል?» ሰውየውም  ተገርሞ ከዚህ በፊት ሌሎች ሁለት ሰዎችም  ተመሳሳይ ነገር ነው ያሉኝ በማለት ።አፍዝ አደንግዝ አድርገውብኝ ለውጠውብኝ ይሆን ? ይልና ያሳደገውን በግ  ገበያ ይዞ ሄዶ አረጋግጦ  መሸጥ  እየቻለ የዋህ የሆነው የገጠር ሰው  ይህን ሳያደርግ  በጉን 

ውሻ ነው!.. ብሎ ፈቶት ለቀቀው።ሌቦቹም  ያቀየሱት ዘዴ ተሳክቶላቸው  በጉን ቀልበው  ይዘው  ሄዱ።

  «ውሽት ሲደጋገም  እውነት ይሆናል» የሚባለው  ለዚህ ነው።

 ብዙ ጊዜ  ልክ ከላይ እንደቀረበው  ተረት አይነት

በተለያዩ ወቅት የምንሰማቸው የማደናገሪያና የማወናበጃ የውሸት ወሬዎች ተደጋገመው  እውነት የሚሆንበት ጊዜ  ያጋጠመን ወይም ያስተዋልን በርካታዎች  ነን ። 

  በተለይም  በማህበራዊ

ሚዲያዎች ላይ የምንመለከታቸው  አንዳንድ ወሬዎች፤ እንዲሁም

በፖለቲካና በንግድ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የሚያቀርቧቸው ንግግሮች በየሰፋራችንና በየአካባቢያችን እከሌ ጉንፋን ያዘው  ሲባል ሆስፒታል ኮማ ውስጥ ገባ  የሚሉን ወዘተ በዚህ በኩል ግንባር ቀደም  ተጠቃሾች  እየሆኑ መጥተዋል ። 

እያነሳን  ያለነው  ነጥብ ስለውሸት  አይደል? በዓለም  ላይ ያሉ አብዛኛው  ፖለቲከኞች  ሌላው  ኃያል  የተባሉ  የአሜሪካውን ጆ ባ ይደንን ጨ ምሮ  ካልወሹ ሕዝባቸውን መምራት የማይችሉ የሚመስላቸው የአፍሪካዎችን  መሪዎች  ጨምሮ  በርካታዎች  ናቸው።ዛሬ የተናገሩትን የማይደገሙ ፖለቲካኞችም  በየጊዜው እየተበራከቱ መሄድ ብቻ አይደለም  ሌላው  ቢቀር የሚያወሩት ውሸት እውነት እንዲመስል በማድረጉ በኩል

በኢኮኖሚ  ካደጉት ሀገሮች የአፍሪካ ፖለቲከኞች ብዙ አለመማራቸው  ጉድ የሚያሰኝ ነው። ምንም እንኳን የውሸት ጥሩ ነገር  ባይኖርም  ስንዋሽ ሰውን ይጎዳል ይሆን ወይ ብለንም መጠየቅ አንድ ነገር ነበር ግን ይህ አልሆነም።  ነገዴው   ካልዋሸ ንግድ መነገድ አይችልም።ቀኑን ሙሉ ሲዋሽ ይውልና በዱአ ማታ ላይ ውሸቱን ያወራርድና ተኝቶ ሲነጋ ተመልሶ ወደ ውሸት ይገባል።ሕይወት እንዲህ እያለ ይቀጥላል።  ውሸት በአሁኑ ወቅት ማግባቢያ ቋንቋ እየመሰለ የመጣበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። 

  አንድ ነጋዴ ያሉኝ አባባል ይህንኑ የሚያመለክት ነው።«እኛ ነጋዴዎችና ፖለቲከኞች አንድ ነን ! » አሉኝ።« እንዴት አልኳቸው?» « ካልዋሸን ሥራችንን መስራት አንችልም »ብለውኝ ነበር።

 ነጋዴው  ፖለቲከኞችን ውሸታሞች  ናቸው  ይሉናል። ነጋዴው በየአመቱ ሱር ታክስና ቫት ትክክለኛውን ለመንግስት ከመክፈል ይልቅ አጭበርባሪ ኦዲተር ፈልገው  ጎምደው  ጎምደው  ከፎርጅት ማስረጃዎች ጋር አያይዞ ለመንግስት ትክክለኛውን  ቀረጥ  ከመክፈል ይልቅ የተሳሳተ ክፍያ ይፈፅማል።ያ የሚከፍለው ክፍያ ተመልሶ እሱንና ቤተሰቡን እንደሚጠቅም ግን አይረዳም።አሁን አሁንም ነጋዴው  ሲሸጥ  ብቻ አይደለም  የመንግሥት ግብርና ቫት ወይንም ታክስ  እንዲከፍሉ ሲጠየቁ ማጭበርበርና ማታለል 

ወይም  መዋሸት የተለመደ ትውፊታዊ  ባህል  እየሆነ መጥቷል።«ጫማ  አለኝ ብለህ እሾህ አትርገጥ።አፍ  አለኝ ብለህ በሰው  አታላግጥ።»እንደሚባለው  የአባቶች ብሂል መሆኑ ነው። 

 ሁላችንም  በአሁኑ ወቅት ውሸታሞች  ሆነናል።አባ ሳሙኤል  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክራቲያን  የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድ ኦ ኮሚሽን  ሊቀ ጳጳስ « በአሁኑ ጊዜ ሰው ሁሉ ማለት ይቻላል ሌላ ሰው ነው።ውጪው  ሌላ ውስጡ  ሌላ ፤ኑሮ ሌላ ህልሙ  ሌላ፤ልቡ ሌላ፤አፉ ሌላ ሁላችንም ሌላ ሰው  ሆነናል ። ከኅይማኖትም ከእውነት ወጥተናል። » እንዳሉት ከኅይማኖታችን ከእውነትም  ወጥተናል።

 መጽሐፍ ቅዱሳችን  በመጽ ሐፈ ምሳሌ 12 ፦ 22 « ውሸተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አጸያፊ ነው፤እውነትን የሚያደርጉ ግን በእርሱ ዘንድ የተወደዱ ናቸው » 

ይል የለ።

እውነትን የሚያደርጉ ፤በእውነት መንገድ የሚጓዙ በእግዚአብሔር ዘንድ  የተወደዱ  ናቸው  ካለ፤ እውነታውን ይዘን የምንጓዝ ስንቶቻችን እንሆን?እውነት ስንልስ ምንድን ነው?

 የዐለቃ  ኪዳነ ወልደ ክፍሌ መዝገበ ቃላት  እውነት የሚለውን ቃል ትርጉም  ከገጽ 226-227  አማን ፥

የታመነ ፥እውነት ፥

በውነት ጻዲቅ መጽደት ፥

እውነተኛ መሆን ፤መርታት በፍርድ ከሐሰት ከበደል መንጻት ፤መጥራት፤

መብለጥ፤መሻል(መዝ 16 እና 50ሣራ 1፥22።25፥29፤ዘፍ 30፥26) ጻድቅ እውነተኛ፤ቅን፤መልካም ፤ደግ፤በጎ፤ንጽሕ፤ጥሩ፤ኪዳነ ወልደ በማለት ይተነትነዋል።

 እውነት የሚለው ቃል በግእዝ «ጽድቅ» ወይም «አማን»በግሪክ «አሌቴያ» ሲባል

ብሉይ ኪዳን በተጻፈበት በዕብራይስጥኛ ቋንቋ «አሜት» ከሚል ቃል የተገኘ ነው።

 ጽድቅ ሲባል እውነተኛ ሆነ ስሕተት የለበትም  ማለት ነው።

ደስታ ተክለ ወልድ  በመዝገበ ቃላታቸው  ጽድቅ የሚለውን ቃል ሲተረጉም «ረታ» እውነተኛ ሆነ፤ከሐሰት ከኅጢአት ተለየ፤ከዚህ የተነሳ መንግሥተ ሰማያት ገባ፤ከኩነኔ ራቀ፤በነፍስ ተጠቀመ በመንፈሳዊ ክብር ከበረ» በማለት ይገልጹታል።

እውነት ማለት ትክክል ማለት ነው።በሌላ አነጋገር እውነት የውሸት ተቃራኒ ነው።በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥም «ከእናንተ ማንም  ከእውነት ቢስት አንዱም  ቢመልሰው»(ያዕ.5፥19)

ውሸት ከእውነት መሳት ወይንም ማፈንገጥ  እንደሆነ ያስረዳናል።ከእግዚአብሔር ባሕርይ ጋር የማይስማማ ሕይወትና  ከእግዚአብሔር ጋር የሚቃረን ንግግር ሁሉ ከእውነት የራቀ ነው።

 ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ  መል እክቱ ላይ ምዕራፍ 2 ቁጥር 8 ላይ «ለዐመፃ በሚታዘዙ እንጂ ለእውነት በማይታዘዙትና በአድመኞች ላይ ቁጣና መቅሠፍት ይሆንባቸዋል»

በማለት እንደገለፀው  በአንድ ጊዜ ለእውነትና ለሐሰት መታዘዝ እንደማንችል ፤አንደኛውን መምረጥ እንዳለብን ፤ለእውነት የማንታዘዝ ሰ ዎች ዐመፀኞች፣አድመኞችና ሐሰተኞች እንደምንባል፤

በውሸት መንገድ የምንሄድ ሰዎች ፍጻሜያችን የእግዚአብሔር ቁጣና መቅሠፍት እንደሆነ ያስረዳናል። 

 እውነተኛነት ፍጹምነት ነው፤እግዚአብሔር የእውነተኛ አምላክ እንደሆነ ሁሉ ፤ቃሉም እውነት ስለሆነ ፤እውነትም እግዚአብሔር ስለሆነ ፤የሰው ልጅም  በባህሪውና በአምሳሉ የፈጠረን ስለሆነ እኛም እውነተኞች መሆን የግድ ይኖርብናል ።

  ዋናው  ቁምነገር መረዳት ያለብን ነገር እውነት ሰዎች የሚፈጥሯት ወይም  የሚያኖሯት አይደለችም።ስለ እውነት ልናውቀው  የሚገባን ነገር ከእውነት ጋር አብረን ልንቆምና በእውነት መንገድ ልንሄድ ይገባናል።ይህ ማለት በእኛ አስተሳሰብና በእኛ ውሳኔ እውነትን እናገራለው ብለን ብቻ  በማውራት የሚተገበር አለመሆኑን ማወቅና መረዳት ይኖርብናል።

  አንዳንዴ  እውነትን እንናገራለን ብለን ውሸት የምንናገር ሰዎች አንኖርም ? ከዚህ አንፃር እውነት በራሷ ዛቢያ ላይ ቆማ ያለች፣የምትኖርና ልትለወጥም የማትችል እንደሆነች መረዳት አለብን።በመሆኑም ፈለግንም አልፈለግንም  በእውነት ላይ አንዳችም  ነገር ማድረግ አንችልም ።ይህ ማለት እውነት ውሸት እንዲሆን ማድረግ አንችልም።

 በእርግጥ  ሰዎች  እውነት የሆነውን ነገር ዐውቀው እውነትን ሊናገሩ በእውነትም ሊኖሩ ይችላሉ።ይህን ለማድረግ ግን አስቀድሞ  እውነትን ማወቅ ያስፈልጋል።እውነትን ሳያውቁ  በእውነት እኖራለው ብሎ  መደስኮር የሚያስኬድ አይደለም።ብዙን ጊዜ  በርካታ ሰዎች እውነት እንደሚያወሩ ይነግሩናል ይሁንና እውነትን እያወቁ ውሸትን የሚናገሩና በውሸት ውስጥ የሚመላለሱ በርካታዎች ናቸው።እየዋሹ አውቀውም  ሆነ ሳያውቁ መኖር ይቻላል።ዳሩ ግን እውነትን አወቁም  አላወቁም ፤

ዋሹም  አልዋሹም፤ሰዎች እውነትን ከእውነታው ሊቀይሯት ውሸትን እውነት ወይም እውነትን ውሸት ማድረግ አይችሉም።ምክንያቱም እውነት አትለዋወጥምና ነው።

ብዙዎቻችን ከእውነት ጋር ብንስማማ  ማለትም እውነትን ዐውቀን የምንኖር ከሆነ እውነተኞች  እንባላለን ፤

ይህ ብቻ አይደለም  ከፈጠረን 

አምላክንም  እንስማማለን።

እውነተኛነት በየትኛውም ኅይማኖት ተፈላጊ ነገር ነው።በክርስቲያኑ ብቻ ሳይሆን፣በቡዲዝሙ፣በሽንቶይዝሙ፣በሂንዶይዝሙ፣በሙስሊሙ ወዘተ.አንድ ሰው  መዋሸት በጭራሽ እንደሌለበትና ንግግራችን እራሱ በእውነትኛነት ላይ የተመሠረተ ከመሆኑም ባሻገር ስናስረዳ እንኳን የምናወራው ነገር ተአማኒነት እንዲኖረው ከፈለግን በማስረጃ የተደገፈ መሆን እንዳለበት በኅይማኖታቸው  ተምህሮ  ላይ ያብራራሉ።

ስለሆነም  የሰው ልጅ እውነትን ዐውቆት በእውነት ይኖራል እንጂ ሰዎች የራሳቸው እውነት የላቸውም።ይህ ማለት ሰዎች እውነትን ራሳቸው የሚፈጥሯት ወይም  በሰዎች ላይ የተመሰረተች አይደለችም። ምክንያቱም  እውነት አንድ እንጂ ብዙ እውነቶች አይኖሩምና።በክርስቲያን ኅይማኖት ትምህርት እውነት እግዚአብሔር ነው፤የእግዚአብሔር ባሕርይ ነው።ብዙ እግዚአብሔር እንደሌለ ሁሉ ብዙ እውነቶች የሉም።በመሆኑም እውነተኛ ሆንን ማለት፤እግዚአብሔርን እናውቃለን፤እግዚአብሔርን እንመስላለን፤ስለ እውነት እናወራለን በእውነትም  መኖር እንጀምራለን።በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 8 ቁጥር 32 ላይ እንዲህ ይላል።«እውነትን ስናውቅ በእውነትም ስንኖር እውነት አርነት ታወጣናለች።በእውነት የማይኖር የሐሰት ባሪያ ነው» በማለት የሚናገረው ለዚህ ነው።

 «በልብ ከሸሸጉት እውነት በግል የተቀበሉት እሳት ሳይበልጥ  ይቀራል? » ብላችሁ ነው ? 

 ከላይ ለማንሳት እንደሞከርኩት እውነት

 የእግዚአብሔር ባህርይ እንደሆነ፤የውሸት ተቃራኒ(አንታይ)መሆኑን፤እውነት የማይለዋወጥ  ዘላለማዊ ከመሆኑም  ባሻገር የሰው ልጅ ምንም  ሊያደርግ  እንደማይቻል  በጥቂቱ ለመመልከት ችለናል።

 በተረፈ  በርካቶቻችን የምናስባቸውና  የምናቅዳቸው በርካቶች  ነገሮች ይኖሩናል። ታዋቂ  ሰው  መሆን፣ባለጠጋ መሆን፣ባለሥልጣን መሆን፣

በትምህርታችን ውጤታማ  መሆን ወዘተ .ለማሳከት እንጥራለን።

እነዚህን ምኞታችንን ለማሳከት አታለንም  ሆነ አጭበርብረን አሊያም  ዋሽተን  ወይንም  ጉቦ ሰጥተን ስኬታማ  ልንሆን እንችላለን።ይሁንና ስኬታችን ጣፋጭ  የሚሆነው  ከላይ ከተነሳው  ነጥብ  በተቃራኒ መልኩ ሆኖን ስንገኝና ጥረታችን በእውነት ላይ የተመሰረተ ቢሆን ነው የሚመረጠው።ከዚህ ሌላ ወንድማቸውን እየበደሉና እያሳዘኑ ፤በጥላቻና በክፋት በተሞላ ኑሮ ውስጥ ተዘፍቀው አካሄዳቸውን ያበላሹ ወገኖች እራሳቸውን መፈተሽ እንደሚኖርባቸው  ከወዲሁ ሳላሳስብ  አላልፍም።

  በእርግጥ  ቃየን ወንድሙን አቤልን ቡክርናውን ለመውሰድ ገደለው  እያልን ታሪኩን

 ማውራት ብቻ ሳይሆን ራሳችንንም  ፊታችንን በመስታወት ፊት ቆመን እንደምንመለከተው ሁሉ  የራሳችንን ሰብዕናና ሕይወትንም  በእውነት መንገድ እየሄድን ነው  ወይ ብለን መመልከት  ያስፈልጋል።

በክፋትና በምቀኝነት ተሞልተን ፤እየዋሸንና እየቀጠፍን፤

የተጣላናቸውንና የበደሉንን ይቅር ሳንል ለእግዚብሔር የምናቀርበው  መስዋዕት ሁሉ ከንቱና የቃየን አይነት መሥዋዕት ነው  የሚሆነው።

በተለይም  በዚሁ በሀገራችን

ወንድሙን የሚጠላና ወንድሙን የሚያሳድድ ምእመንና የቤተክርስቲያን አባቶችና ወንድሞች  በርካቶች  ናቸው።

እነዚህ የቃየን ልጆች ናቸው።

ዛሬ በዘመናችን የአቤልና የቃየን ልጆች በአገራችን ውስጥ  በርካቶች አሉ።ቃየን አቤልን እንዳሳደደውና እንደ ገደለው እንዲሁ በጥለቻ ፥በቅናትና በክፋት ልባቸውን ሞልተው፤በእግዚአብሔር ፊት ቅዱስ ስሙን እየጠሩ መሥዋዕታቸውን ይዘው የሚያቀርቡ ነፍሰ ገዳዮች የሆኑ መተተኞች የሆኑ ካህናቶች፣ደብተራዎች፣ዲያቆኖች አሉ።እንደ አቤል ደም በግፍ የተገደሉ፣ንብረታቸውን የተዘረፉ፥ከሥራ የተፈናቀሉ ከቤተክርስቲያንና ከአገር የተሰደዱ፤በእግዚአብሔር ፊት የሚጮኹ  የየዋሃን ምእመናን(ናት)ብቻ ሳይሆን በግፍ የተገደሉ የበርካታ ኢትዮጵያውያን ነፍሳት ምድራችንን ሞልተውታል።

በእርግጥ  ይህን የሚያደርጉ ኢአማንያን ቢሆኑ ኖሮ አያደንቅም ነበር።ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ፊት የሚጸልዩ ፣ቁርባን ይዘው  የሚያቆርቡና የሚቆርቡ፤በክርስቲያንነታቸው የሚማጻደቁና ስለ ሃይማኖታቸው  የሚቆረቆሩ የሚመስሉ  ሰዎች መሆናቸው ግን ነገሩን ይበልጥ  አሳዛኝ ያደርገዋል።

 የቃያን መንገድ የክፉው መንገድ ነው።የጥላቻ ፥የቅናት ፥የመግደል መንገድ ነው።ሰውን በድንጋይ ወርውረን  ፤በዱላ ደብደብን ወይም  በጥየት ተኩሰን ላንገድለው እንችላለን።ማንም  ወንድሙን የሚጠላ ሰው  ሁሉ እርሱ ነፍሰ ገዳይ ነው  እንዳለው ሐዋርያው  ዮሐንስ  ነፍሰ ገዳይ መሆን አይኖርብንም ምክንያቱም  ነፍሰ ገዳይ ወንጀለኛ ነው ፤ወንጀለኛ ደግሞ  ኅጢአተኛ ነው።

ስለዚህ  ኅጢአተኛ ደግሞ በሞት ውስጥ  ያለ ነው።ውሸት ከኅጢያት መንገዶች አንዱ ነው።በአሁኑ ወቅት በአገራችን በብዛት የሚስተዋለው  ደግሞ ውሸትና የውሸት ካባ ደርበው የሚንቀሳቀሱ ወገኖች ናቸው።እንዲያውም  «ውሽት ሲደጋገም  እውነት ይሆናል» እንደሚባለው ውሸታቸው ተደራርቦ ተደራርቦ እውነት እየሆነ በመምጣት ላይ ይገኛል። 

እነዚህ የቃየን መንገድ ዛሬም አለ።የቃያን መንገድ የሚከተሉ በልባቸው የክፉ፣የጥላቻ ፣የቅናት  ፥የመግደል መንገድ ነው።ሰውን በድንጋይ ወርውረን  ፤በዱላ ደብደብን ወይም በጥየት ተኩሰን ላንገድለው እንችላለን።ይሁንና በክፋትና በተንኮል ተነስተን በሰው ልጅ ላይ የምንወረውረው  ቀስት ምንም  እንኳ  ትንሽ ጊዜ ሰውየውን ቢጎዳውም  መልሶ ግን  ጊዜውን ጠብቆ እራሳችንን መውጋቱ አይቀሬ ነው።ምክንያቱም  እውነት ምንግዜም  እውነት ነው።እውነትን የያዘ ሰው ምንም  እንኳ ችግርና መከራ ቢደራረበትም  የእውነት አምላክ የወረወረውን የክፋትና የተንኮል ቀስት መልሶ ወደ ወረወረው  ግለሰብ ላይ ይተክለዋል።ፆመ  ነነዌን ዛሬ ጀምረናል።አብይ ጾምን ደግሞ ከ15 ቀን በኋላ እንጀምራለን።በእነዚህ የጾማት ቀን የምንጾመው  እራሳችንን ከምግብ ብቻ መለየት አይደለም ከእውሸት፣ከሀሚት፣ከጥላቻ፣ከክፋትና ከተንኮል ጭምር  በመራቅ መሆን ይኖርበታል።በተለይም