ኢትዮጵያና ሱማሊያ በየፊናቸው ያደረጉት ስምምነት


ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ ( ጮራ ዘ አራዳ) ደራሲ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሃያሲ ) 

ኢትዮጵያና ሱማሊያ ከሱማሌላንድ ጋር በፈረንጆቹ አዲስ አመት ጥር 1 ቀን በፈረሙት የወደብ የሊዝ ሽያጭ ላይ አተካሮ ከገጠሙ  ያው ሁለተኛውን ወር አጠናቀው ሦስተኛ ወራቸውን ሊይዙ ነው።

ኢትዮጵያ ከሱማሌ ጋር ጦርነት እንደማትፈልግ ገልጻ ብዙ የተወራለትን ጉዳይ ዝምታን ብትመርጥም  ሱማሊያ ግን አሁንም አካኪ ዘራፍ ማለቷን እንደቀጠለች ነው።ሮይተርስ ማከሰኞ ዕለት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ቃለ መጠይቅ አድርጎ ባወጣው መረጃ እንደሚጠቁመው  ከሆነ ኢትዮጵያ ‘ህገ-ወጥ’ የወደብ ስምምነትን ወደ ተግባራዊነት ከለወጠች ሶማሊያ ራሷን ትከላከላለች ሲሉ  በፕሬዝዳንቷ አማካይነት ይፋ አድርጋለች።

የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ኢትዮጵያ በሶማሊላንድ የባህር ኃይል ሰፈር ለመመስረት ስምምነት ላይ ከደረሰች ሀገራቸው ራሷን ለመከላከል የምትችለውን ሁሉ እንደምታደርግ ነው  የተናገሩት።

ተንታኞችና ዲፕሎማቶች የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ከሀገር መውጣታቸው በሶማሊያ መረጋጋት እንዳይኖር ያደርገዋል ሲሉ ቆይተው ነበር። እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ የአልሸባብ ጥቃት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችንና ወታደሮችን የገደለ ሲሆን በርካታ ወታደሮችን ወደ ሱማሊያ በመላክ  የሰላም ማስከበሩን ግዳጅ በብቃት የተወጣችው  ኢትዮጵያ ነበረች።

የአፍሪካ ቀንድ ለድርቅ ተጋላጭ  ከመሆኑም ባሻገር አካባቢው  ከሰብዓዊ ቀውሶች ባሻገር ተደጋጋሚ ግጭቶች አጋጥመውታል። ጎረቤት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በ1977-1978 እና በ1982 በግዛት ይገባኛል  ጥያቄ  ተዋግተዋል።

የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ  በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ለመወያየት ፍቃደኛ የሚሆኑት  የአዲስ አበባ መንግስት “የአገራችንን ክፍል የመውሰድ” ፍላጎቱን ሲያቆም ብቻ ነው ሲሉ ተናግረዋል።የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ የሱማሌው ፕሬዝዳንት በአቀረቡት አስተያየት ላይ እንዲሰጡ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ አይደሉም ሲል ሮይተርስ ገልጿል። ዶክተር አብይ ቀደም ሲል ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር ግጭት የመፍጠር እቅድ እንደሌላትና የባህር ተደራሽነት በተለይም ያለባትን ችግር ለመፍታት ጥረት እያደረገች እንደሆነ ተናግረዋል።

የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ አካል ሆኖ በሶማሊያ የሰፈሩት ወደ 3,000 የሚጠጉ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከአልሸባብ አጋር ከሆነው የአልቃይዳ ታጣቂዎች ጋር እየተዋጋ የሚገኘውን ጦር የማስወጣት የሱማሊያ መንግሥት  እያሰበ እንዳልሆነ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል ።

ተንታኞችና ዲፕሎማቶች የኢትዮጵያ ወታደሮች ከሀገር መውጣታቸው በሶማሊያ መረጋጋት እንዳይኖር ያደርገዋል ሲሉ ስጋታቸውን ከወዲሁ ገልጸዋል። እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ የአልሸባብ ጥቃት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችንና ወታደሮችን  እየገደለ ነው።

በሶማሊያ በሚገኙ ታጣቂዎች ላይ በየጊዜው ጥቃት የምትፈጽመው ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ በርካታ ምዕራባውያን ሀገራት የኢትዮጵያ ከሱማሌ ጋር ያደረገችው የወደብ ስምምነት በሱማሌ የሚገኙ ወጣቶች ወደ አልሸባብ ሊገቡ ይችላሉ የሚል ፍራቻ አላቸው።አልሻባብም ቢሆን ይህንኑ አጋጣሚ በመጠቀም  በሱማሌ ሽብሩን ለማጠናከር የምልመላ ጥረቱን ሊያሳድገው  ይችላል የሚል እሳቤ አላቸው ።

በ2006 እ.ኤ.አ መጨረሻ ላይ የኢትዮጵያ ጦር ሶማሊያን የወረረው አልሸባብ የተባለውን አሸባሪ እስላማዊ ግንባር ለማስወገድና እንቅስቃሴውን ለመግታት ወደ ሱማሌ ገብቶ እየተዋጋ ነው የሚገኘው   ።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ የመንግስታቸው ግምት እንደሚያሳየው አልሸባብ በጥር ወር ብቻ ከሱማሌ ላንድ ጋር ኢትዮጵያ ስምምነት ካደረገች በኋላ ሁኔታውን በመቃወም ከ6,000 እስከ 8,000 የሚደርሱ አዳዲስ ተዋጊዎችን መመልመሉን  ለማወቅ ተችሏል  ይላሉ።

ሮይተርስ ያነጋገራቸው ተንታኞችና ዲፕሎማቶች  ፕሬዝዳንቱ ያቀረቡትን አሀዝ እንደማይቀበሉና በሺዎች ሳይሆን ምናልባት በመቶዎች የሚቆጠሩ አዲስ ምልምሎች ሊቀጠሩ ይችላሉ የሚል ግመት አስቀምጠዋል። 

በፈረንጆቹ አዲስ አመት መጀመሪያ ላይ ጥር 1 ቀን 2024 በተፈረመው የኢትዮጵያ ና የሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ላይ የበቀል እርምጃ በሚመስል መልኩ በኢትዮጵያና በሶማሌ አዋሳኝ ከተማ ባላድ ሀዎ በትንሹ 6 ኢትዮጵያውያን  መገደላቸው  ታውቋል።

በኢትዮጵያና በሶማሌላንድ መካከል በተደረገው የመግባቢያ ስምምነት ሶማሊያ ክፉኛ ተቆጥታለች። የኢትዮጵያ እርምጃ የሶማሊያን ሉዓላዊነት እንደጣሰ ነው የሚያመለከተው በማለትም ትናገራለች። እንዲያውም  የኢትዮጵያና የሱማሌላንድን ጉዳይ እንደ አንድ  ትልቅ ኢሹ  አድርጋ ሱማሊያ  ስምምነቱን በመቃወም ግብፅን እና የአረብ ሊግ አባላትን ለበርካታ ሳምንታት ካሰባሰበች በኋላ ተቃውማለች።በሌላ በኩል  ሶማሊያ ሐሙስ ዕለት ከቱርክ ጋር የባህር መከላከያ ስምምነት ተፈራርማለች ኢትዮጵያ ከእንግሊዝ ጋር ኬንያና ሱማሌ በሌሉበት ሁኔታ በሱማሌና በኬንያ በኩል አልሻባብ የተባለውን አሸባሪ ኃይል አከርካሪውን ለመምታት ስምምነት በዚሁ በያዝነው ሳምንት ተፈራርመዋል። 

ሁለቱ ሀገራቶች ከቱርክና ከእንግሊዝ ጋር ያደረጉት ስምምነት ምን እንደሚመስል እንመልከት።ቱርክ በሶማሊያ ውስጥ ትልቁ የጦር ሰፈር አላት። ከሀሳን ካልዮንኩ ዩኒቨርሲቲ ቱርካዊ ምሁር ሙራት አስላን በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል ያለውን ውጥረት ሲገልጹ ቱርክ ከሶማሊያ ጋር የጀመረችውን የመከላከያ ስምምነት  ይህንኑ ያረጋግጣል በማለት ይገልጹታል።

ሶማሊያ ከቱርክ ጋር የተደረገውን የመከላከያ ስምምነት አወድሳለች ፣ ለ «ለማይነቃነቀው  ድጋፍ» አመስግናለው ።ብለዋል  የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ከስምምነቱ በኋላ በሰጡት መግለጫ።

የሱማሊያው የመከላከያ ሚኒስትሩ አብዱልቃድር መሀመድ ኑር እ.ኤ.አ ከ 2011 ጀምሮ ከአንካራ መንግሥት ጋር ሱማሊያ  ያላት  ግንኙነት እያደገ መምጣቱንና ሀገራቸው ሁለቱ መንግስታት «የማይበጠስ» ግንኙነት እንዳላቸው ተረድቻለው  » ብለዋል ።

የሶማሊያ የመከላከያ ሚኒስትር አብዱልቃድር መሀመድ ኑር ሀገሪቱ ከቱርኩ ጋር የገባችውን አስደናቂ የመከላከያ ስምምነት «የሀገራችንን አስተማማኝና ብሩህ ተስፋ ለማሳደግ አዲስ ምዕራፍ የሚያመጣ የአዎንታዊ ለውጥ  ምልክት ነው።» ሲሉ ገልጸዋል ።

የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለTRT World በሰጡት ቃለ ምልልስ መከላከያ ሚኒስትሩ ኑር እንዳሉት ስምምነቱ ሁሉንም አይነት ህገወጥ ተግባራትን ለማጥፋት የተደረገውን የጋራ ቁርጠኝነት የሚወክል፣ ለሶማሊያ የባህር ላይ መከላከያ የማዕዘን ድንጋይ የሆነ የተዋጣለት የባህር ሃይል መመስረትን ያጠቃለለ  ነው ። .» ብለዋል።

መከላከያ ሚኒስትሩ ኑር «ለወንድማማችነት የቱርክ ሪፐብሊክ መንግሥት ላሳዩት ጽናትና  ፈጣን ድጋፍ እንዲሁም  በክልላችን ሰላምን፣ መረጋጋትን፤ሀብትን ለማፍራት ላሳዩት ቁርጠኝነት ያለንን ጥልቅ አድናቆት እናቀርባለን።» ሲሉ በጉራ ተናግረዋል።

ሰኞ እለት የሶማሊያ ፓርላማ የሁለትዮሽ ከቱርክ ጋር የተደረገውን የመከላከያና የኢኮኖሚ ትብብር ስምምነት ለቱርክ የሶማሊያን የወደብ ውሃን የመጠበቅ ስልጣን የሚሰጥ የ10 አመት ስምምነት አጽድቋል።

የሶማሊያን የመከላከል አቅም  ማጠናከር

ስምምነቱ የሶማሊያን ውሃ መጠበቅ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ቀንድ ሀገርን ደህንነት ለመጠበቅ የባህር ሃይል ለማቋቋም የሚያስችል ሁኔታም አስቀምጧል።

«በተጨማሪም ስምምነቱ እያደገ የመጣውን ሰማያዊ ኢኮኖሚያችንን ለማጠናከር፣ ቁልፍ የኢኮኖሚ  ዘርፎችን ለማነቃቃት እና ለዜጎቻችን እንዲሁም ለሰፊው ክልል አዲስ የብልጽግና መንገዶችን ለመፍጠር ቃል ገብቷል።» ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትሩ ለTRT World ተናግረዋል።

«ለወንድማማችነት የቱርክ ሪፐብሊክ መንግሥት ላሳዩት ጽኑ፣ ፈጣን ድጋፍና በክልላችን ሰላምን፣ መረጋጋትን ሀብትን ለማፍራት ላሳዩት ቁርጠኝነት ያለንን ጥልቅ አድናቆት እናቀርባለን።» ብለዋል።

«በቱርክ የባህር ኃይል ሰራተኞች እውቀትና ድጋፍ ፣የእኛ የባህር ኃይል ሀይሎች አለምአቀፍ ደረጃዎችን ለማሳካት በጠንካራ ስልጠና እንደሚራመዱ ተስፋ እናደርጋለን። በዚህ ረገድ ቱርክ የሰጠችው እርዳታ በእውነት ሊለካ የማይችል ነው።» ሲሉም አክለዋል።

የማይናወጥ ድጋፍ በቱርክ

በቱርክና በሶማሊያ መካከል ያለው ግንኙነት የቱርክ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በአፍሪካ ላይ ከሚገለጽባቸው መንገዶች አንዱ ነው።

እ.ኤ.አ. በ 2011 የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር – አሁን ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ከሁለት አስርት ዓመታት ገደማ በኋላ ሶማሊያን የጎበኙ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ያልሆኑ መሪ ሆነዋል።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ አጋጣሚዎች ሀገሪቱን ጎብኝተው የሶማሊያ አቻዎቻቸውን በቱርክ ብዙ ጊዜ አስተናግደዋል።

የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር እንዳሉት « እንደ ሶማሊያውያን ችግሮች ባጋጠሙን ጊዜ የቱርክ ወንድሞቻችንን ድጋፍ ሰጪ እጃቸውን  ይዘረጉልናል»ብለዋል።

«ይህ እምነት በአንድ ጀምበር የተዝረጋ  አይደለም; ታሪክ የሰጠን ሃላፊነት ነፀብራቅ ነው። በተለይም ከ2011 ጀምሮ የሁለትዮሽ ግንኙነታችን በአዲስ መልክ ሲያድግ ይህ እምነት የማይበጠስ መሆኑን ተገንዝበናል።» ሲሉ ገልፀዋል።

« ከዚያ አመት ጀምሮ ቱርክ የሶማሊያ ህዝብ የተስፋ ብርሃን የሆነችውን የወንድማማችነት እጇን ዘርግታለች። ቱርክ በሚያስደንቅ ወታደራዊ ፣ የተከበረ ህዝብና በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት የሚዘልቅ የመንግስት ባህል ያላት የማያወላውል ድጋፍ ሰጥታናለች። ይህን ስምምነት ተከትሎ የሶማሌ ህዝብ ያስተላለፉት የደስታ መልእክቶች ለዚህ ትስስር ትልቅ ማሳያ ናቸው።» በማለት መከላከያ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

ቱርክ እንደ መከላከያ ኃይል

አዲስ አበባ ከሶማሊያ ተገንጣይ የሶማሌላንድ ግዛት ጋር የቀይ ባህር መዳረሻ ስምምነት ከተፈራረመች በኋላ ሞቃዲሾ «ህጋዊ ያልሆነ»  ስትል በሶማሊያና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ውጥረት ተባብሶ በቀጠለበት በአሁኑ  ወቅት የስምምነቱ ዜና  መሳጭ  ነው።

«ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሶማሊያ የባህር ዳርቻዎቻችንን የመጠበቅና የማስጠበቅ ከባድ ስራና አሳዛኝ ፈተናዎች ገጥሟታል። በዚህ ወቅት ቱርክ ከባህር ሃይሏ ጋር በመሆን በጓደኞቻቸው ላይ እምነት እንዲኖራቸው ያደርጋል እንዲሁም ጠላት ሊሆኑ በሚችሉ ሰዎች ላይ ፍርሃት ይፈጥራል።» ሲሉ የሰማሊያ መከላከያ ሚኒስትር  ኑር ይናገራሉ።

«የቱርክን ሰፊ የመንግስት ስራ ልምድ በተለያዩ ዘርፎች መጠቀሙ ለሶማሊያ መንግስት ብቻ ሳይሆን ለክልላዊና ለአለም አቀፍ ሰላም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል» ብለዋል ።«ለቱርክ ምስጋና ይግባውና በሶማሊያ ወደብ  ውስጥ ያለው የሃይል ክፍተት የሚሞላው ጠንካራ የሶማሊያ የባህር ሃይል በማቋቋም ሲሆን ሁሉም አይነት ህገወጥ ድርጊቶች ክትትልና ቁጥጥር ይደረግባቸዋል።» በማለት የሱማሊያው መከላከያ ሚኒስትር ተናግረዋል።

ኢትዮጵያና ቱርክ የጠበቀ ግንኙነት አላቸው።በኢትዮጵያ ከቻይና ቀጥላ ሁለተኛዋ ትልቅ መዋለ ንዋይ በኢትዮጵያ ያፈሰሰች ሀገር ቱርክ ነች።ሰብዓዊ ዕርዳታዋን ከፍ አድርጋ በእርስ በርስ ግጭት ለተመታችው ሀገር ሰበዓዊ እርዳታም ለኢትዮጵያም ትሰጣለች ።ምርጥ  የተባሉ የጦር መሳሪያዎችም  ድሮኖች ጨምሮ ለኢትዮጵያ ያስታጠቀች ሀገር ብትኖር ቱርክ ነች።

ቱርክ ለኢትዮጵያ የምታደርገው የሰብዓዊ ዕርዳታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ከአንካራ በዓለም አቀፍ ዕርዳታ  በማድረግ በኩል ግንባር ቀደም ሚና ትጫወታለች፤ ከዚህ ውስጥም አገሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቁን ዕርዳታ በመስጠት ትታወቃለች። እ.ኤ.አ. በ 2020 ቱርክ 26 ከመቶ የአለም አቀፍ ሰብአዊ እርዳታ ስትይዝ 8.04 ቢሊዮን ዶላር ወጪ አድርጋለች ሲል በእንግሊዝ መቀመጫውን  ያደረገው የልማት ኢኒሼቲቭስ ገልጾ ነበር።«ያለምንም ማመንታትና ፍርሃት የቱርክ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (NGO) በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በትግራዩ ጦርነት ከሚገባው በላይ እርዳታ  አድርገዋል » ሲሉ የቱርክ የዜና  ምንጮች በወቅቱ ገልፀው ነበር።

«ንቁ ና ገለልተኛነት» 

«ቱርክ በተለያዩ ምክንያቶች በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ትፈልጋለች። አንደኛ ከኢትዮጵያ ጋር ታሪካዊና ወዳጅነት ያላት ሀገር ስትሆን በሁለተኛነት በሀገሪቱ ብዙ ኢንቨስትመንቶች አሉን» ሲል የቱርክ የዜና ምንጭ ተናግሯል። በመላው ኢትዮጵያ ከ150 በላይ የቱርክ ኩባንያዎች ከግንባታ እስከ ጨርቃጨርቅ ድረስ በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት አድርገው   በኢትዮጵያ ውስጥ  ተሳትፈዋል።

ለቱርክ፣ ኢትዮጵያ «ታላቅ የመካከለኛው ምስራቅ ግንባታ የምትካሄድባት ስትራቴጂካዊ ፅንሰ-ሃሳቧን ተግባራዊ ለማድረግ የምትችልባት ሀገር ኢትዮጵያ እንደሆነች የቱርክ የዜና ምንጮች ይናገራሉ  ።

«በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ማንኛውም አለመረጋጋት ወደ ሌሎች ክልሎች ሊዛመት ይችላል፣ ይህም በመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ መዘዝ ያስከትላል።ይህ ደግሞ  ለቱርክ ጥሩ እንዳልሆነ  TRT World ተናግሮ ነበር።ከዚህ አንፃር ቱርክ የኢትዮጵያና የሱማሌላንድን ስምምነት ከራሷ አድቫንቴጅ አንፃር ትደግፋለች እንጂ  ከሱማሌ ጋር የ 10 አመት ስምምነት ማድረጓ በኢትዮጵያና በቱርክ መካከል ያለውን ግንኙነት ያበላሻል ማለት የማይሆን ነገር ነው።እንዲያውም ከዚህ በፊት ኢትዮጵያና ቱርክ ያደረጉትን ወታደራዊ ስምምነት ማዕቀፍን የተከተለ ነው።እንዴት የሚለውን ወደ ኋላ ላይ እመለስበታለው።

የዜና ምንጩ በተጨማሪም እንደሚለው አብዛኛው የቱርክ ኢንቨስትመንቶች ከ2000ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ እስከ 2010ዎቹ መጨረሻ ድረስ የትግራይ ተወላጆች በሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ግንባር ቀደም የፖለቲካ ድርጅት የሀገሪቱን የበላይነት በተቆጣጠሩበት ወቅት የገቡ ናቸው ።ስለዚህ ከትግራይ ጋር የፌድራል መንግሥቱ ስምምነት ስላደረገ በኢትዮጵያ ያለው የሰላም ሁኔታ እንዲቀጥል የቱርክ መንግሥት ይፈልጋል።

በ2018 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣት የሕወሃት አገዛዝ በማብቃቱ የስልጣን ሽኩቻ ፈጠሯል። አብይ የተማከለ ስርአት ጠንካራ ተከታይ ሲሆን ህወሓት ደግሞ የፌዴራሊዝም  አስተዳደር ተከታይ ነው።

ቱርክ በኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉንም ብሄረሰቦች በእኩል መልኩ ትመለከታለች። ይላል የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ።

ባለፈው አመት ኢትዮጵያ ውጥረት ውስጥ በነበረችበት ወቅት አብይ ቱርክን ጎብኝተው  ነበር።በአሁኑ ወቅት ስልጣን የለቀኩትን የቱርኩን ፕሬዝዳንት ሬክ ማቻርን አግኝተው ነበር። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከቱርክ አቻቸው ጋር በተደጋጋሚ  ተነጋግረዋል። 

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 18 ቀን 2021 በአንካራ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ሶስት የተለያዩ ስምምነቶችን በመከላከያ ሚኒስቴሮች ጭምር የተፈራረሙ ሲሆን «የፋይናንስ አስተዋፅዖ ትግባር ፕሮቶኮል ፣ የወታደራዊ ፋይናንሺያል ትብብር ስምምነትና የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት አድርገዋል። ይህን ስምምነትን ለፓርላማ ቸው  አቅረበው. እንዲፀድቅ አድርገዋል።

በስምምነቱ ውስጥ የትብብር መስኮች በወታደራዊ ልምምዶችና ከጦርነት ውጪ በሚደረጉ እንደ ሰላም ማስከበር፣ ሰብአዊ  እርዳታና የባህር ላይ ወንበዴ ተግባራት ላይ በጋራ ለመዋጋት መሳተፍ የሚሉ ተዘርዝረዋል። ስምምነቱ ሁለቱ ሀገራት በመከላከያ ኢንደስትሪ ውስጥ እንዲተባበሩም ያስችላቸዋል።ከዚህ አንፃር ቱርክ ከሱማሌ  ጋር ያደረገችው ስምምነት ሁለቱ ሀገራት የተስማሙትን መሰረት ያደረገ ነው ማለት ይቻላል።

በስምምነቱ አንቀጽ 4(6) መሰረት ተዋዋይ ወገኖች ወታደራዊ መረጃን ለመለዋወጥም ተስማምተዋል። ከዚህም በላይ ተዋዋይ ወገኖች የጋራ ሎጀስቲክስ ድጋፍና የጦር መሳሪያ፣ ቁሳቁስ እንዲሁም አገልግሎት በእርዳታ መልክ ወይም በክፍያ  ለመለዋወጥም  ተስማምተዋል።

ሚስጥራዊ መረጃ ጥበቃ ፤አካላዊና አእምሯዊ ንብረት መብቶች በአጠቃላይ ቱርክ የጦር መሳሪያ ለመሸጥ ካቀዳቸው ሀገራት ጋር በተፈራረመችው በመከላከያ ኢንደስትሪ ውስጥ የትብብር ስምምነቶች ላይ የተካተተው አንቀፅም ከኢትዮጵያ ጋር በሚደረገው የማዕቀፍ ስምምነት ውስጥ ተካቷል።

ከኢትዮጵያ ጋር በተደረገው ወታደራዊ ስምምነት ላይ በፓርላማ ኮሚቴ ውስጥ የተካሄደው የውይይት  ስምምነትም በቱርክ  ፓርላማ  ፀድቋል።

İYİ (ጥሩ) ፓርቲ ምክትልና ጡረታ የወጡ ዲፕሎማት አህመት ካሚል ኤሮዛን ስምምነቱ በተፈረመበት ወቅት ቱርክ ከግብፅ ጋር ከፍተኛ ችግር ስለነበራት አሁን ለማፅደቅ ትክክለኛው ጊዜ አይደለም ብለው ነበር ። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በመከላከያ ሚኒስቴር መካከል ቅንጅት አለመኖሩን የገለጹት ኤሮዛን የስምምነቱ መፅደቅ የግብፁን ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲን ያናድዳል ብለዋል።

ነገር ግን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፋሩክ ካይማክቺ ስምምነቱ የትኛውንም ሶስተኛ ሀገር ላይ ያነጣጠረ እንዳልሆነ ገልፀው እስካሁን ከ86 ሀገራት ጋር ተመሳሳይ ደረጃቸውን የጠበቁ ስምምነቶች ተፈርመዋል።የቱርክና የኢትዮጵያ ወታደራዊ ግንኙነት ወደ አለማቀፋዊ አጀንዳ የመጣው የኢትዮጵያ ጦር ጥር 27 ቀን 2022 ከቱርክ በተገዛው ሰው አልባ አውሮፕላኖች በህፃናት፣ ሴቶችና አዛውንቶች የተሞላውን የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ህንጻ ከደበደበ በኋላ ነው። በጥቃቱ ቢያንስ 59 ንፁሀን ዜጎች ሲገደሉ በደርዘን የሚቆጠሩ ደግሞ  መቁሰላቸው አይዘነጋም ። እስከዚያው ጊዜ ድረስ ቱርክ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ለኢትዮጵያ እንደምትሸጥ አይታወቅም ነበር። ከቦታው የተገኙ የጦር መሳሪያዎች ቅሪቶች MAM-L (ስማርት ማይክሮ ሙኒሽን) በቱርክ ሮኬት ሳን የሚመረቱ ቦምቦችና በቱርክ ከተሰራው ባይራክታር ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጋር ብቻ ተጣምረዋል እነዚህ ሁሉ መሳሪያዎች ከቱርክ የተገዙ ናቸው።

ቱርክ ወደ ኢትዮጵያ የላከችውን የጦር መሳሪያ ለህጋዊው መንግስት መደረሱን የጠቀሱት ካይማክቺ ደንቦቹ የመጨረሻ ተጠቃሚው ማን እንደሆነ ይገልፃል። ነገር ግን እነዚህ የጦር መሳሪያዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ስለተጠቀሙበት ውንጀላ ምላሽ አልሰጠም።የቱርክ ኤምባሲ ወደ ኬንያ የተዛወረው የትግራይ ታጣቂዎች ደም አፋሳሹ ጥቃቱን ከፈጸሙ በኋላ ዒላማ እንደሚያደርጉት ይፋ ባደረጉበት ወቅት እንደሆነ የገለጹት የሕግ አውጪዎች፣ ነገር ግን ካይማኪ በወቅቱ ማክሰኞ ቀን በተደረገው የኮሚቴ ስብሰባ ላይ፣ በጸጥታ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ለጊዜው የለቀቁት ኤምባሲው ሳይሆን አምባሳደሩ ብቻ እንደሆነ ተናግረው  በወቅቱ ብዙ ሳይቆዩ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።

ግብፅ ከየኢትዮጵያና ከቱርክ ያላት ጉዳይ 

በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ባለው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ግብፅና ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል። ግብፅ የመጠጥ ውሃ እና የመስኖ ፍላጎቶቿን ከሞላ ጎደል የምታሟላው በአባይ ወንዝ ላይ ያለው የውሃ መጠን መቀነስ ያሳስባታል። ሶስቱ ሀገራት ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት ተባብረው ለመደራደር ቢያስቡም እስካሁን ተጨባጭ መፍትሄ ለማምጣት የሚያስችል ዘዴ መፍጠር አልቻሉም።በዚህ የተነሳ  ኢትዮጵያ ከግብፅና ከሱዳን ጋር ጥሩ ግንኘነት እንደሌላት ቱርክ ታውቃለች።ምክንያቱም ቱርክ ከግብፅ ጋር ጥሩ ግንኙነት የላትም።

ለተወሰነ ጊዜ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሴፕ ጣይብ ኤርዶጋን መንግስት ከግብፅ ጋር ያለውን ያልተረጋጋ ግንኙነት ለማስተካከል ጥረት ሲያደርግ ቆይተዋል። ቱርክ ከአልሲሲ የግብፅ  መሪ ጋር እስላማዊ ወንድማማችነት በሰጠችው ድጋፍ ላይ ከባድ ችግር አጋጥሟታል በሚል ሁኔታ በተደጋጋሚ ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል።ኤርዶጋን በርዕዮተ ዓለም ግብፅ ለእሳቸው የቀረበች አድርገው ይመለከቷት ነበር። ነገር ግን ቱርክና ግብፅ በየፊናቸው በሊቢያ የሚገኙ ሁለት ተቀናቃኝ ቡድኖችን ይደግፋሉ፣ ሁለቱም ብቸኛ ህጋዊ መንግስት እንወክላለን የሚሉ ናቸው።

ይሁን እንጂ የኤርዶጋን ፖሊሲዎች ቱርክ በእስላማዊው ዓለም ውስጥ እንድትገለል በሚያስችልበት ጊዜ, ግብፅን እና ሳውዲ አረቢያን ለማበረታታት ድርድር ጀመራ ነበር።, ይህም ቱርክ ጭንቀታቸውን ለመፍታት ተጨባጭ እርምጃዎችን እንድትወስድ  አድርጓት ነበር። ቱርክ ከኢስታንቡል የሚተላለፉ የሙስሊም ብራዘርሁድ ጋር ግንኙነት ያላቸውን የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ማብራሪያ እንዲሰጡ በመጀመሪያ ጠየቀች።እ.ኤ.አ በመጋቢት 2021 የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ከግብፅ ጋር ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ዲፕሎማሲያዊ ድርድር መጀመሩን አስታውቀዋል። የግብፅ ልዑካን የንግግሩን እድገት ለማረጋገጥ በቱርክ እጅ ላይ ግብፅ  እንዳለች መልዕክቱን በማስተላለፍ ከቱርክ ተጨባጭ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚያስፈልግ በቱርክ ሚዲያዎች ተነግረው  ነበር።እ.ኤ.አ. ህዳር 20 በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ በተካሄደው የአለም ዋንጫ መክፈቻ ላይ ኤርዶጋን ከኤል ሲሲ ጋር ሰላምታ ሰጥተው ተጨባበጡ ።የወዳጅነት መጨባበጡ በሁለቱ ሀገራት መካከል ለተጀመረው የመደበኛነት ሂደት ጠቃሚ እርምጃ ተደርጎ  በወቅቱ ተወሰዶ  ነበር።

ኤርዶጋን ከኳታር ሲመለሱ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “የቱርክ ሀገር እና የግብፅ ህዝቦች ባለፉት ዘመናት የነበራቸው አብሮነት ለእኛ በጣም አስፈላጊ ነው። ለምን እንደገና ግንኙነታችንን አንጀምርም?  በማለት ነገሯቸው።ግን በወቅቱ አልተሳካም።

ከኢትዮጵያ ጋር በወቅቱ የተደረገው  ወታደራዊ ስምምነት ወደ ፓርላማ ማምጣት ግብፅ ከግሪክ ጋር በምስራቃዊ ሜዲትራኒያን የምታደርገውን ትብብር የሚቃወም መልእክት ተደርጎ ሊወሰድ  ተችሎ ነበር።ይህ ሁኔታ ነው እንግዲህ ሁለቱም ከግብፅ ጋር ያላቸው ልዩነት ነው ኢትዮጵያና ቱርክን እንዲህ  በወዳጅነት  ያስተሳሰራቸው።

 በዚህ ሳምንት ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ በሶማሊያ-ኢትዮጵያ የድንበር ደህንነት ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመዋል።

ኢትዮጵያና እንግሊዝ «በኬንያ-ሶማሊያ-ኢትዮጵያ ድንበር ሰላምና መረጋጋትን ማጎልበት» በሚል ሁኔታ የመግባቢያ ሰነድ  ነው የተፈራረሙት ።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር«በኢትዮጵያ-ኬንያ-ሶማሊያ ድንበሮች ላይ ያሉ ማህበረሰቦችን ለመታደግና  በአመጽ ጽንፈኛ የሆኑ ወገኖች አሽከርካሪዎች  ላይ የሚፈፅሙትን ዘረፋ በመቋቋም በሚያስችል ሁኔታና አቅምን ለማሳደግ ያለመ  ስምምነት  ነው።» ተብሏል።

ስምምነቱ በኢትዮጵያ ና በሶማሌላንድ መካከል በሁለቱ ሀገራት መሪዎች ከተፈረሙት ስምምነትበመሪ ደረጃ ሳይሆን  በተቃራኒ መልኩ በዝቅተኛ  ደረጃ  ባሉ  ባለስልጣኖች ውክልና  የተከናወነ  እንደሆነ  ተገልጿል ።

በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ በተካሄደ ሥነ ሥርዓት። በኢትዮጵያ በኩል በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ መምሪያ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ጀማሉዲን  ሲፈርሙ በእንግሊዝ መንግሥት በኩል በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ዳረን ዌልች ፈርመዋል። 

የድንበር ደህንነት ስምምነቱ ከአልሸባብ ስጋት አንፃር የተፈረመ ይመስላል ።ነገር ግን ኬንያ የዚህ የመግባቢያ ስምምነት አካል አልነበረችም። ስምምነቱ«የኬንያ-ሶማሊያ-ኢትዮጵያን ድንበር »የሚመለከት ቢሆንም፣ ኬንያ የዚህ አካል አልነበረችም። ይሁንና  ኬንያ በዚህ ሳምንት ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ተፈራርማለች። ይሁንና ሶማሊያም የስምምነቱ አካል አይደለችም።

ሁለቱ ወገኖች [ኢትዮጵያና እንግሊዝ] በአልሸባብ በአካባቢው ያለውን ስጋት ለመቀነስ በጋራ ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት  ያሳየ  መሆኑ ተጠቁሟል።አበቃው ።