የቶዮታ ነገር


መንግስት በቶዮታ አጋርነት ማጭበርበር ላይ የእርምት ትዕዛዝ ሊሰጥ ነው።

የጃፓን የትራንስፖርት ሚኒስቴር ለቶዮታ ሞተር ኮርፖሬሽን በሞተር መረጃ ማጭበርበር የኦፕሬሽን ማስተካከያ ትዕዛዝ ሊሰጥ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ያለፈው  ሳምንት ሰኞ ገለፀዋል።????????????

ሚኒስቴሩ በቶዮታ ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን አንዳንድ ሞተሮችን በብዛት ለማምረት የሚያስፈልጉትን የምስክር ወረቀቶች ለመሻር እያሰበ መሆኑን ምንጮቹ  የገለጹት።

ባለፈው ወር በኩባንያው ላይ ተጨማሪ የመረጃ አያያዝ ጉዳዮችን ማግኘቱን ያስታወቀ ሲሆን  ቶዮታ ሞተሩ  በሰው ላይ  ጉዳት ያደርሳል በሚል ሁኔታ በርካታ ለገበያ የቀረቡ  ሞተሮች ባለፈው ወር በዓለም ላይ እንዲቆሙ ኩባንያው ማድረጉ ይታወሳል።በዚህምየተነሳ በርካታ  ተሽከርካሪዎች እንዲቆም አድርጓል።????????????