አብዛኛዎቹ የአብን አባላት ሌላ ፓርቲ ለማቋቋም በሒደት ላይ መሆናቸው ተገለጸ


ከገዥ ፓርቲ ጋር የካቢኔ አባል ሆነው በሚሠሩትና በሌሎችም ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አመራሮች የተነሳ፣ የፓርቲው ህልውና አደጋ ውስጥ በመግባቱ፣ አብዛኛዎቹ አባላት ሌላ ፓርቲ ለማቋቋም በሒደት ላይ መሆናቸውን፣ ፓርቲውን ወክለው ለፓርላማ የተመረጡት የፓርላማ አባል ተናገሩ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ አበባው ደሳለው ከሪፖርተር ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት፣ ፓርቲው (አብን) ስለታሰሩ አባላቱም ሆነ በአገር ላይ እየተከሰተ ስላለው ሁኔታ ምንም እያለ አይደለም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የፓርቲው አባላት (አመራሮች) የፌዴራልና የክልል የካቢኔ አባል በመሆናቸው፣ ካቢኔ ውስጥ ወስነው በፓርቲ ደረጃ መቃወም ስለሚከብዳቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በዚህም ከገዥው ፓርቲ ተነጥለው የማታዩበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን አክለዋል፡፡ ‹‹የምናደርገው ቸግሮን ነው ያለነው›› የሚሉት የፓርላማ አባሉ፣ በአብን ምርጫ ተወዳድሮ የፓርላማ አባል ከተሆነ በኋላ፣ ሌላ ፓርቲ ማቋቋቋም ስለመቻሉም ሆነ ስለመከልከሉ ሕገ መንግሥቱ የሚለው ባለመኖሩ፣ የሕግ ባለሙያዎችን በማነጋገር ከልካይ ሁኔታ እንደሌለ መረዳታቸውን አስረድተዋል፡፡ አቶ አበባው ከሪፖርተር ጋር ያደረጉትን ቆይታ በዚህ ሊንክ ይመልከቱ፡፡