ረሀብና የወደብ ውዝግብ ያላት ሶማሌላንድ የነፃነት ጥያቄዋን አሁንም ቀጥላለች


ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ

(ደራሲ ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሃያሲ) 

( ካለፈው የቀጠለ) 


እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን 2024 በኢትዮጵያ እና በሶማሌላንድ መካከል የተገለጸው የመግባቢያ ስምምነት በአፍሪካ ቀንድ እና ከዚያም በላይ ዲፕሎማሲያዊ ውዝግቦችን አስነስቷል።

 

የስምምነቱ ዝርዝሮች በይፋ ባይታወቁም የሁለቱም የክልል መሪዎች ይዘቱን አንስተዋል። ከዋና ዋና  ነጥቦች  መካከል-

ኢትዮጵያ በሶማሌላንድ ቀይ ባህር ጠረፍ ላይ ለባህር ኃይል እና ለንግድ ባህር አገልግሎት እንዲሁም ለበርበራ ወደብ የ50 አመት የሊዝ ውል  መቀበል።

ሶማሌላንድ  በበኩሏ የኢትዮጵያ አየር መንገድንና  የቴሌ ኮምኒኬሽንን የተወሰነ  ድርሻ  ማግኘት። ኢትዮጵያ ሶማሌላንድን እንደ ሉዓላዊ ሀገርነት እውቅና መስጠትና  ቃል  መግባት። 

ይህን ለማድረግ ኢትዮጵያ  ከወሰነች ለሶማሌላንድ እውቅና በመስጠት የመጀመሪያዋ ሀገር ትሆናለች። በግንቦት ወር 1991 ከሶማሊያ ነፃ መውጣቷን ካወጀች በኋላ ተገንጣዩ መንግሥት ራሱን ችሎ የሚንቀሳቀስ ቢሆንም ዓለም አቀፋዊ እውቅና ግን  እስካሁን የለውም።

የመግባቢያ ሰነድን የሚቃወሙ ሀገራት ዝርዝር እንደ ግብፅ ያሉ በቀጣናው ያሉትን  ሀገራት  ጭመሮ  እንደ  አሜሪካና አውሮፓ ህብረት ያሉ ምዕራባውያን ሀይሎችን ያጠቃልላል። ቻይና እና ቱርክም ከተቃዋሚዎቹ  መካከል ተደባልቀዋል።

የተቃውሞ ምክንያታቶቻቸው ይለያያል። 

አንዳንዶች  ወደቦች፣መንገድ፣ ግድቦች ወይም የባቡር ሀዲድ ያሉ ሌሎች መሰረተ ልማቶችን  ማጠናከር ጂኦፖለቲካዊ ጠቀሜታ  እንዳለው ያረጋግጣሉ። እነዚህ ፕሮጀክቶች ብዙ ጊዜ  በእርግጥ ያከራከራሉ።

መሠረተ ልማት በፖለቲካዊ ማንነቶች ውስጥ በጣም የተጠላለፈ ስለሆነ ነው የሚያከራክሩት።ለምሳሌ የኢትዮጵያ የፖለቲካ አመራሮች ወደብ የሌላቸው ሀገሮች ወደብ እንደሚያስፈልጋቸው የዓለም አቀፍ ህግ ስለሚፈቅድ ይህን  የባህር ላይ መዳረሻን ወይም ወደብን እንደ “የህልውና ጉዳይ” አስፈላጊ መሆኑን ከዓለም አቀፍ ህግ  ጋር  ጭምር በማጣቀስ አውጀዋል። የሀገሪቱ ታሪካዊ ደረጃ እና ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት የባህር ላይ ሉዓላዊነት የማግኘት መብት እንዳላትም  ይሟገታሉ።

በስምምነቱ መሰረተ ልማቶች ብቸኛ መንገዶች  አይደሉም። ነገር ግን የጂኦፖለቲካዊ አቀማመጥ መሰረት በማድረግ  ወደብ  መኖሩ አስፈላጊ እንደሆነ አፅንዖት ይሰጣሉ። በፖለቲካና በኢኮኖሚያዊ ውድድሮች ላይ  ያለው ጠቀሜታም የጎላ ነው። ይህም በአካባቢው እየጨመረ ያለውን አለመረጋጋት አሳሳቢ  እንዲሆን ያደርገዋል።

የዲፕሎማሲው ሽኩቻዎች  በአሁኑ ወቅት በቀይ ባህር አካባቢና  ከዚያ በላይና በታች ባሉ ሀገራት ላይ የፖለቲካ ሽኩቻና ውጥረት በይበልጣ እንዲስፋፋና እንዲጠነክርም ያደርገዋል ። የመግባቢያ ሰነዱ የሶማሊላንድን እውቅና ጥያቄ ወደ እነዚህ የፖለቲካ ተለዋዋጭነት ማዕከል  እንዲለወጥ አድርጎታል።

ተቃውሞ

የሱማሌ መንግሥት ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያደረገችውን  የወደብ ስምምነት ትልቁ ተቃዋሚ ነች። የሶማሊያ ፌደራል መንግስት ፕሬዝዳንት ሼክ ሀሰን መሀሙድ « የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት መጣስ ነው ።» ብለዋል። ሶማሊያ ግዛቷን ከኢትዮጵያውያን “ጥቃት” እንደምትከላከልም  አስታውቀዋል።

ክሶማሊያ የተገነጠለችው  የሶማሊላንድ ክልል የህግ አውጭዎች ከኢትዮጵያ ጋር የተደረገውን የባህር  ወደብ አገልግሎት ስምምነት ውድቅ አደረገዋል።

በተለይ ከባህር ዳርቻው ከአውዳልና ከሳላል ግዛቶች የተውጣጡ የሶማሊላንድ ፓርላማ የሁለቱም ምክር ቤቶች አባላትበዚህ ሳምንት  ማክሰኞ መገባደጃ ላይ በጋራ በሰጡት መግለጫ «የቀይ ባህር ተደራሽነት ስምምነት “ህገ-ወጥ ነው።»ከማለታቸውም ባሻገር። «ድርጊቱ የሶማሊላንድን ህዝቦች አንድነት ለመጉዳት ያለመ ነው።»ብለዋል።

«ስምምነቱንና አፈጻጸሙን ውድቅ አድርገናል፤ መንግሥትም የመግባቢያ ሰነዱን እንዲያቆምና እንዲሰርዝ እየጠየቅን ነው»ብሏል  መግለጫው።

መግለጫው ኢትዮጵያ በኤደን ባህረ ሰላጤ ላይ ቋሚ የባህር ሃይል ቤዝ እና የንግድ የባህር አገልግሎት እንድታገኝ በሚያስችለው ስምምነት ላይ የሶማሌላንድ እና የኢትዮጵያ መሪዎች የተናገሯቸውን መግለጫዎች  ማመላከቱም ታውቋል።

ሶማሊያ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የገባችውን የቀይ ባህር ወደብ ስምምነት «ህጋዊ ያልሆነ»ስትል «ለመልካም ጉርብትና ጠንቅ እና ሉዓላዊነቷን የሚደፈርስ ነው »በማለት ውድቅ አድርጋለች። ስምምነቱ ከተገለጸ በኋላ  ሱማሊያ በኢትዮጵያ አምባሳደሯን አስጠርታለች።

ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር በጃንዋሪ 1  ስምምነት ከገባች በኋላ የሁለቱ ጎረቤቶች  ሀገሮች ግንኙነት እየተበላሸ  መጥቷል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከሞቃዲሾ እውቅና ውጪ ስምምነቱን ለመፈረም መወሰኑን ሲገልጽ ከሶማሌላንድ ጋር የተደረገው ስምምነት የትኛውንም ፓርቲና ሀገር አይነካም ሲል  በሱማሌ በኩል የሚቀርብበትን ክስ  ውድቅ በማድረግ ተሟግቷል።

ከ1961 እስከ 1991 ከዘለቀው የኤርትራ የነጻነት ጦርነት በኋላ ኢትዮጵያ በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ የቀይ ባህር ወደቦችዋን አጥታለች።

እ.ኤ.አ. በ1991 ኤርትራ ከኢትዮጵያ ነፃነቷን አግኝታ ሁለት የተለያዩ ሀገራት መመስረት  ችለዋል። የኤርትራ  ከኢትዮጵያ መገንጠል ኢትዮጵያ በቀጥታ የቀይ ባህርን እና ቁልፍ የባህር ወደቦቿን እንድታጣ አድርጓታል።ኢትዮጵያ  የአሰብና የምፅዋ ወደብን ብታጣም በአሰብ ላይ የወደብ ጥያቄ ፋይል  አሁንም አልተዘጋም።ይሁንና የኢትዮጵያ መንግሥት ብዙ አመት ቆይቶ ይህን ጥያቄ ዳግመኛ ወደቡን በነፃ ለማግኘት ጥያቄውን ያነሰዋል ወይ ? የሚለው ነገር   አንዱ ሲሆን ይሁንና ከዚህ በፊት ያንሳው አያንሳው ወይም ለወደፊቱ ያንሳው አያንሳው በውል የሚታወቅ ነገር የለም።ህወሓት ግን ኤርትራ በድንበሯ አካባቢ ያለውን የባድሜን ጉዳይ ፌድራል መንግሥቱ  አቶ መለስ ከምክር ቤት አባላት ጋር  ፈርመው  ተቀብለዋል ቢልም። ህወሓት እስካሁን ይህን ሁኔታ አልተቀበለውም።ከዚህ አንፃር ምናልባት የኢትዮጵያም መንግሥት ሀሳቡን ቀይሮ ከህወሓት ጋር በመነጋገር ሰጥቶ በመቀበል መርሁ መሰረት የአሰብን ጉዳይ እንደመደራደሪያ ነጥብ ሊያነሳው ይችል ይሆናል።በሌላ በኩል የአየር በሯን ከመዝጋት ውጭ ሌላ  ጉልበቷን ያላሳየችው  በሞቃዲሾ የሚገኘው የፌደራል መንግስት  ምንም እንኳን በውስጥ  የእርስ በእርስ ጦርነት  ቢጠመድም የኢትዮጵያን መንግሥትን በኃይል ለማስቆም  አቅሙ በጭራሽ የለውም።ሌላው ቀርቶ በሶማሊላንድ  ግዛት ለመወሰን ቀርቶ በኃይል ሱማሌላንድን ለማቆም አቅሙ ስለሌለው  እስካሁን ድረስ ዝምታን መርጧል። እንዲያውም በመላው ሶማሊያ ላይ ሙሉ የግዛት ቁጥጥር እንኳን መንግሥት ነኝ የሚለው የሙቃዲሾ መንግሥት አያደርግም - ሌላው ቀርቶ አልሸባብ በደቡብ እና በመካከለኛው ሶማሊያ ያለውን ግዛት ስለሚቆጣጠር  እሱን እንኳን  አልቻለም።ሌላው ቀርቶ አካባቢውን  ከአልሸባብ ማፅዳት አቅቶታል። ታጣቂው እስላማዊ ቡድን ስምምነቱ የሶማሊያን ሉዓላዊነት የሚጻረር ነው ይበል እንጂ  በተደጋጋሚ ከኢትዮጵያ ሰራዊት የሚደርስበትን ጡጫ መመካት  ባለመቻሉ እምቡር እምቡር ከማለት በስተቀር ምንም የሚያመጣው ነገር  የለም።

የሶማሌላንድ እና የኢትዮጵያ የቅርብ አጋር የሆነችው የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እስካሁን ዝምታን መርጣለች። የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በቀይ ባህር አካባቢና በአፍሪካ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ፣በሱማሌና በኤርትራ ወዘተ ፣ በዕርዳታና በኢኮኖሚ  እገዛ ሰበብ ተጽእኖዋን እያሳደገች ነው።

የሶማሌላንድን  መንግሥት  በበኩሉ የበርበራ ወደብን  በተሻሻለ  የወደብ ግንባታ ሳይሆን ባለው አቅም  ኮንቴይነር አስገብተው  ወደቡን  ያስተዳድራል።

የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ኩባንያዎች በመላው አፍሪካ የወደብ መሠረተ ልማት በመገንባት ላይ ናቸው። የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ከቻይና፣ ከአሜሪካና ከአውሮፓ ህብረት በመቀጠል በአህጉሪቱ ካሉ ከፍተኛ የውጭ ባለሀብቶች ተርታ መሰለፍ የቻለች ሀገር ነች።

ስምምነቱን የሚቃወሙት የአለም አቀፍና ኃያላን ሀገራት  እንደ ምክንያት የሚያቀርቡት ሁሉም ሀገራቶች  ቦታው ካለው ስትራቴጂካዊ  ጠቀሜታ አንፃር ነው።

አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረትና ቱርክ የሶማሊያን መንግስት የጸጥታ መዋቅር መልሶ ለመገንባትና እስላማዊ ሽብርተኝነትን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ  እያፈሰሱ ነው።ግን ይህን ማቆም ሳይችሉ ሌላ የቀይ ባህር አሸባሪ ኃይል ከየመን ተንስቶ ቀይ ባህርን ቤርሙዳ ትሪያንግል አድርጎታል።

ለምሳሌ ቱርክ በሞቃዲሾ የሚገኘውን የአየር ማረፊያና የባህር ወደብ አስተዳደሪነት ተረክባለች። በዋና ከተማው ማህበራዊ እና አካላዊ መሰረተ ልማቶችን ገንብታለች።በአገሪቱ ውስጥ የመጀመሪያውን የውጭ ወታደራዊ ሰፈርም  ከፍታለች።

አሜሪካና ቱርክ  በየፊናቸው  ልዩ ሃይል በሶማሊያ ያሰለጠኑ ሲሆን ሁለቱም ሀገራት በመሬት ላይ  የተደራጀ  ወታደር  ኃይል አላቸው። ይህ ደግሞ በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል የሚፈጠር ግጭት ኢንቨስትመንቶቻቸውን አደጋ ላይ ይጥላል፣ ከዛም አልፎ ለቀጣናው  አለመረጋጋት  ከፍተኛ ስጋት ከመፍጠሩም በተጨማሪ ሌላ ፈተናዎችን ይፈጥራል ። ምናልባትም ቦታው በአልሸባብ እጅ ውስጥ ሊገባም ይችላል የሚል ስጋት አላቸው።

የአውሮፓ ህብረትና የአውሮፓ ሀገራት ሚና በአሁኑ ወቅት የበለጠ አሻሚ ነው።የአውሮፓ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ግሎባል ጌትዌይ ኢኒሼቲቭ አካል ለሆነው የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ወሳኝ የገንዘብ ድጋፍ ሰጪ ነው።

ኢኒሼቲቩ የኢኮኖሚ ውህደትን ለማጎልበት የክልል መሠረተ ልማትን ለማገናኘት ቃል ገብቷል።ያ ነው ኢትዮጵያም ከመግባቢያ ሰነድ ጋር  አብራ ቃል የገባላት። የአውሮፓ ህብረት ሶማሊላንድን አይቀበልም  ነገር ግን የመንግስት ተቋሞቿን ለመገንባት ድጋፍ አድርጓል።

እንግሊዝ የሶማሌላንድ ወደብን ከኢትዮጵያ ድንበር ጋር የሚያገናኘውን የበርበራ ኮሪደር አካል የሆነውን የሃርጌሳ ማለፊያ መንገድን እንኳን ሳይቀር እንዲጠናከር የገንዘብ ድጋፍ እያደረገች ነው።

የጅቡቲና የቻይና ተቃውሞ ምንም አያስደንቅም። የጅቡቲ የባህር ወደብ ከ 80% በላይ የሚሆነውን የኢትዮጵያ የባህር መርከብ ንግድ ያስኬዳል። ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብን መጠቀሟ በጅቡቲ ያለውን የንግድ ልውውጥ መጠን ሊቀንስ ይችላል።

ጅቡቲ በቻይና ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ ውስጥም ወሳኝ ቦታ ነች። ቻይና የጅቡቲን ወደብ ልማት ትደግፋለች፣ አለም አቀፍ የነጻ ንግድ ቀጠና  እንዲኖር ትሰራለች ። የባቡር መስመር እድሳት ለኢትዮጵያም ትረዳለች።

ኤርትራና ግብፅም ሶማሊያን ይደግፋሉ። ይህ የሆነው በዋናነት ከኢትዮጵያ ጋር የነበራቸው ግንኙነት በግጭት የተበላሸ በመሆኑ ነው። በህዳር 2022 እ.ኤ.አ ኢትዮጵያ ከህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ጋር ሰላም ከፈጠረች በኋላ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ እንደገና  ፊትና ጀርባ ሆነዋል።

ግብፅ የኢትዮጵያን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ትቃወማለች፣ ይህም ኢትዮጵያ በሁለቱም ሀገራት የተመካችበትን የዓባይን ውሃ  ይቀንሳል በሚል ሁኔታ ከኢትዮጵያ ጋር ባላንጣ ሆናለች። በዚህ  የተነሳ ግብፅና ኤርትራ በጭራሽ  ኢትዮጵያ የባህር ሃይል ኖሯት ለማየት ጉጉ አይደሉም።ግብፅ በቀይ ባህር አካባቢ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የኃይል መስፋፋትን በመቃወምም ትሰራለች።

የቀጣይ መንገድ

በጅቡቲ ሰብሳቢነት የሚመራው የቀጣናው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል ስላለው ውጥረት ለመምከር በቅርቡ ያልተለመደ ስብሰባ አድርጓል። የሶማሊያን የግዛት አንድነት አረጋግጧል።ነገር ግን የስምምነቱን ተግባራዊነት ፍጥነቱን እንዲቀንስ ና እንዲወያዩም  ጠይቋል።

ኢትዮጵያ በስብሰባው ላይ አልተገኘችም። ነገር ግን የህዝብን ድጋፍ ለማሰባሰብ የባህር  ወደብን  በመክፈት መዳረሻ ለማድረግ  የሚጥሩት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ  እነዚህን ችግሮች በማስወገድ ሀገሪቷ ያለችበትን የኢኮኖሚ ምስቅልቅል መስመር በማሲያዝ ከፍታ ማማ ላይ ሀገሪቷን ለማስቀመጥ ጠንክረው እየሰሩ ነው።በተለይም በጁቡቲ ያለውን የወድብ ግንባታና የወጣውን ኪሳራ  ታሳቢ በማድረግ። የሀገሪቱ መንግሥት አለም አቀፋዊ  ተቀባይነት አሁን እየተሸረሸ  ይመስላል።በተለይም በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በትግራይ የጦር ወንጀልና የጅምላ ጭፍጨፋዎች  ክስ ሀገሪቷ ላይ ቀርቦበታል።መንግስት በተለያዩ ክልሎች ለሚነሱ ተቃዋሚዎች የወሰደው ወታደራዊ ምላሽ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል ።ለምግብ ዋስትና እጦት አስተዋጽኦም  አድርጓል።

ደስ የሚለው ና  አስፈላጊው ነገር ጠቅላይ  ሚኒስትር ዐብይ እንዳሉት በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል ከፍተኛ የሆነ ግጭት መፍጠር የማይመስል ነገር ነው። እንደ አፍሪካ ህብረትና የአረብ ሊግ ያሉ ታላላቅ የአለም ኃያላን መንግስታት የሶማሊያን የግዛት አንድነት ስላረጋገጡ ኢትዮጵያ የፖለቲካ መገለልን አደጋ ላይ ስለሚጥል  ስምምነት ከሌለ ሌላ አማራጭ ኢትዮጵያ ትፈልጋለች እንጂ እጇን ቶሎ  ዘው አታደርግም።ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐብይ ከዚህ በፊት እንደነበሩት መሪዎች ግትር አቋም የሌላቸው ከመሆናቸውም ባሻገር የኢትዮጵያን ጥቅምና  ጉዳት ላይ በማይጥል መልኩ የሚጓዙ መሪ ስለመሆናቸው  ምዕራባውያን ጭምር  ይመስክሩላቸዋል ።ምክንያቱም ምዕራባውያንን በጭራሽ አያስከፉም።ይህንንም የሚያደርጉት ከኢትዮጵያ  ጥቅም አንፃር ብቻ ነው።

በቀጠናው እየተባባሰ ያለው የፖለቲካ ውጥረት አሸናፊ እሆናለው እያለ የሚፎክረው  አልሸባብ ሲሆን ሶማሊያውያን መሬታቸውን ከውጭ ጣልቃ ገብነት እንዲከላከሉና ተቀባይነትን በህዝቡና በፖለቲካ ለማግኘት  የሽብር  ቡድኑ በማስተባበር እየጠራ ነው የሚገኘው።

በዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ  መንገድ ልትሸነፍ የምትችለው  ኢትዮጵያ ፊቷን ካዞረች ሶማሊላንድ  ብቻ ናት ብቻዋን የምትቀረው።ይህ ደግሞ ከሆነ የምትፈልገውን አለማቀፋዊ እውቅና  ማግኘት ባትችልም።እንደሌሎች በተባበሩት መንግስታት እውቅና ያልተሰጣቸው 7 አገሮች አንዷ  ሆና ትቀጥላለች፡-እነዚህ ሀገራት 
አብካዚያ ፣ኮሶቮ ፣ሰሜናዊ ቆጵሮስ፣ፍልስጥኤም
፣የቻይና ሪፐብሊክ (ታይዋን)፣ሳህራዊ አረብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ (ምዕራባዊ ሰሃራ)
እና ደቡብ ኦሴቲያ እንዳሉ ሀገሮች እየተወዛገብች መኖርን ትመርጣለች።

 

እነዚህ  ሰባት አገሮች በተባበሩት መንግስታት እውቅና ያልሰጣቸው ምክንያቶቻቸው  ይለያያል።አንዳንዶቹ አወዛጋቢ ክልሎች ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ ነፃነታቸውን አውጀው በአብዛኞቹ አገሮች እውቅና አልተሰጣቸውም።

አብካዚያ በ1992 ነፃነቱን ያወጀች በምዕራብ ጆርጂያ የሚገኝ ክልል ነው። በሩሲያ፣ ኒካራጓ፣ ቬንዙዌላ፣ ናኡሩ እና ቱቫሉ እውቅና  ሰጥተዋታል።

ኮሶቮ በ2008 ከሰርቢያ ነፃ መውጣቱን ያወጀ በደቡብ ምስራቅ አውሮፓ የሚገኝ ክልል ነው። አሜሪካ፣ እንግሊዝ እና ፈረንሳይን ጨምሮ በ98 ሀገራት እውቅና ተሰጥቶታል።

ሰሜናዊ ቆጵሮስ በሰሜን ቆጵሮስ በ1983 ከቆጵሮስ ሪፐብሊክ ነፃነቱን ያወጀች ክልል ነች። በቱርክ እንጂ በሌላ ሀገር አትታወቅም።

ፍልስጤም በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኝ ግዛት ሲሆን ከ 1967 ጀምሮ በእስራኤል ተይዛለች ። እንደ ሀገር ያለው እውቅና ውስን ነው ። በ 138 አገሮች እውቅና ያገኘች ቢሆንም ፣ አሜሪካ ፣ እንግሊዝ እና ፈረንሳይ  እውቅና ሰጥተዋታል።

የቻይና ሪፐብሊክ (ታይዋን) በአንድ ወቅት የቻይና አካል የነበረች እራሷን የምታስተዳድር ደሴት ናት። እ.ኤ.አ. በ 1949 ነፃነቷን አውጃለች ።ነገር ግን በተባበሩት መንግስታት እውቅና አልተሰጣትም።

ሳህራዊ አረብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ (ምዕራባዊ ሰሃራ) በሰሜን አፍሪካ የሚገኝ ክልል ሲሆን በሞሮኮ የይገባኛል ጥያቄ የቀረበባት ሀገር ነች። እንደ ሀገር ያላት ዕውቅና የተገደበ ሲሆን በአልጄሪያ፣ ኩባ እና ቬንዙዌላ ጨምሮ በ84 ሀገራት እውቅና ተሰጥቶታል።

ደቡብ ኦሴቲያ በሰሜን ምስራቅ ጆርጂያ በ1991 ነፃነቱን ያወጀች  ሀገር ነች። በሩሲያ፣ ኒካራጓ፣ ቬንዙዌላ፣ ናኡሩ እና ቱቫሉ እውቅና አግኝታለች።

ሶማሌላንድ በ1991 ነጻነቷን ያወጀች ስትሆን በሰሜን ምስራቅ ሶማሊያ የሚገኝ ክልል ነው።በየትኛውም ሀገር እውቅና ባይኖረውም ራሷን በራሷ የምታስተዳደር  ሀገር ነች።

የእነዚህ ሀገራት ሁኔታ  ግን ውስብስብ  ነው።ለወደፊቱ በተባበሩት መንግስታት እውቅና ሊሰጣቸው ይችላል የሚል ትንበያ አለ ።አበቃው ክበረት ይስጥልኝ ።