ረሀብና የወደብ ውዝግብ ያላት ሶማሌላንድ የነፃነት ጥያቄዋን አሁንም ቀጥላለች


ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ

(ደራሲ ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሃያሲ) 

ሶማሌላንድ በሰሜን ሶማሊያ የምትገኝ ራሷን የቻለች ሀገር ስትሆን ለ33 ዓመታት ያለማቋረጥ ነፃነቷን  ለማወጅ ስትታገል ቆይታለች። በአሁኑ ወቅት የመንግስት ተቋማት፣ ወታደራዊ እና ተግባራዊ  የሆነ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ስርዓቶች አሏት።

ታላቋ እንግሊዝ ወይም ዩናይትድ ኪንግደም ሰኔ 26 ቀን 1960 በብሪቲሽ ቅኝ ተይዛ የነበረችው ሶማሊላንድ ነፃነትን በማወጇ በወቅቱ  እንግሊዝ የሶማሌላንድ ግዛት ነፃነት የሰጠች ቀዳሚ ሀገር  ነበረች። ይህን ተከትሎ ጁላይ 1 ቀን 1960 የሶማሊያ የነፃነት ቀን ተብሎ የሚጠራውን የሶማሊያ ሪፐብሊክን ተመሰረተ።

የሶማሊላንድ ነፃነት "ለአምስት ቀናት ብቻ  ነበር " የቆየው ሲል ተመራማሪ ናታሻ ማትሎብ ለዘመናዊ ዲፕሎማሲ መጽሔት ጽፈዋል። “ከዚያ በኋላ ከአሁኗ ሶማሊያ ጋር  ሱማሌላንድ ተቀላቀለች። ይህ ውህደት ግን በሶማሊላንድ ከሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የመንግስት እና የወታደራዊ  አዛዦች  ከሱማሊያ ስለተወገዱ ከብዙዎች ከፍተኛ ተቃውሞ በወቅቱ ገጥሞት  ነበር  በማለት  ተመራማሪው ይገልጸዋል።

ሶማሌላንድ አሁንም የራሷን የነጻነት ቀን ትሻለች።

"አከራካሪው ነገር ፣ ከአፍሪካ ሀገራት እውቅናን የሚከለክለው ዋነኛው ምክንያት የአፍሪካ ህብረት የአህጉሪቱን የቅኝ ግዛት ድንበሮች ለመጠበቅ ያለው የማያወላውል ቁርጠኝነት ነው" ሲል ማትሉብ  ይናገራል።

"የአፍሪካ ህብረት አቋም እነዚህን ድንበሮች መቀየር ያልተጠበቁ የመገንጠል እንቅስቃሴዎችን በመላው አህጉር ሊያመጣ ይችላል ከሚል ስጋት ጋር የተያያዘ ነው፣ ይህም ወደማይታወቅ የጂኦፖለቲካዊ ለውጥ ሊያመራ ይችላል ከሚል ስጋት ነው።" ሲል ይገልጸዋል።

የሶማሌ ላንድ ግዛት ጉዳይ  በተለይም በጥር 1 ቀን 20 ኪሎ ሜትር የባህር ዳርቻ መሬት ወደብ ለሌላት ኢትዮጵያ ሰጥቶ በመቀበል ላይ  በተመረኮዘ መልኩ በኪራይ መልኩ ስምምነት  ከኢትዮጵያ ጋር ሲፈራረሙ ትልቅ ትኩረት  በዓለም ላይ ተሰጥቶት ቆይቷል።

የክራይስስ ግሩፕ የአፍሪካ ዳይሬክተር ሙሪቲ ሙቲጋ “ይህ ስምምነት በአዲስ አመት ቀን እንደ ነጎድጓድ  ከላይ የወረደ  እሳት ነበር” ሲሉ የካቲት 3 ‹ለፋየር  ፖድካስት (Fire podcast)› ተናግረው  ነበር። 

መቀመጫውን ናይሮቢ ያደረገው የዩናይትድ ስቴትስ አለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲ-አፍሪካ ፕሮፌሰር የሆኑት አሌክሲ ይልነን የሶማሌላንድ የነጻነት ጥያቄን ያጠኑ ሲሆን ይህንኑ በተመለከተ ፕሮፌሰሩ አሌክሲ ይልነን «ተገንጣዩ መንግስት ከሶማሊያ ጋር ያለው ግንኙነት የተወሳሰበ ነው »ብለዋል።

"አስጨናቂ ነው"  በማለት ለ Conversation Africa ድረ-ገጽ ፕሮፌሰሩ አሌክሲ ይልነን "ከ2012 ጀምሮ በግንኙነታቸው ላይ ድርድር ከጊዜ ወደ ጊዜ የተካሄደ ሲሆን ትንሽ መሻሻል አላሳየም። የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ግንኙነት ለአስርተ ዓመታት ጠንካራ ነበር” ብለዋል።

ሆኖም ከኢትዮጵያ ጋር የተደረገው የወደብ ተጠቃሚነት ስምምነት “በሶማሌላንድ እና በሶማሊያ መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ  እንዲሻከር  አድርጎታል ” ብለዋል።

 

በሌላ በኩል የድንበር ውዝግቦች እና የአካባቢ ወታደራዊ ግጭቶች ታሪክ ስላላት ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኙነትም ተመሳሳይ ነው።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የወደብ መዳረሻ ስምምነቱን ይፋ ባደረጉበት ወቅት  ሲፈራረሙ የሶማሊያን መሪዎችን ወደ ጎን በመተዋቸው  ቁጣን ቀስቅሷል ። ቀድሞውንም ያልተረጋጋው የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ጦርነት እንዲፈጠር ስጋትም ፈጥሯል።

የሞቃዲሾ ባለስልጣናት ስምምነቱን “ፍሬ እና ዋጋ ቢስ” ሲሉ ፤ የኢትዮጵያውያን “ጥቃት” በሶማሊያ ላይ ያለውን ምልክት ያሳየና ያወጁበት ነው  ሲሉ ተናግረዋል። ስምምነቱ  በአብዛኛው  ጎረቤት ሀገራት እና ከክልላዊ እና አለም አቀፍ ድርጅቶች  ሳይቀር ፈጣን ወቀሳ አስነስቷል።

የሊዝ ውል ለህዝብ ይፋ የተደረገው ሶማሌላንድ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወይም በኢትዮ ቴሌኮም ያልተገለፀ የባለቤትነት ድርሻ መውሰዷን ያጠቃልላል። ነገር ግን ለሶማሊላንድ ዋናው  ጥቅምና  ለስምምነቱ  መነሳሳት የዳረጋት ኢትዮጵያ የሶማሊላንድን ዓለም አቀፍ እውቅና የማግኘት እድል ለመጠቀምና  ሁኔታው  ይበልጥ በዓለም አቀፍ ተቀባይነት  ያስገኝልኛል  የሚል እሳቤ  እንድትጨብጥ  በማስቻሉ ነው።

በዚህም የተነሳ "ይህ  ሁኔታ ኢትዮጵያን እውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ የተባበሩት መንግስታት አባል ሀገር ያደርጋታል" ሲሉ ፕሮፌሰሩ አሌክሲ ይልነን ይናገራሉ ። “ለሶማሌላንድ በጣም የምትፈልገውን ነገር  ይሰጣል። ይህ እውቅና  የመስጠቱ ሁኔታ ለአለም አቀፍ የህዝብ ፋይናንስ በሮች ለመክፈት አስተዋጾ  ከማድረጉም ባሻገር  ለሶማሌላንድ በአካባቢው ያላትን ደረጃ ከፍ  እንዲል ያደርጋታል።

የኢትዮጵያ  ፌድራል መንግሥት ግን እስካሁን መንግስት በይፋ ለሀገሪቷ እውቅና አልሰጠም  በማለት መግለጫ አውጥታለች፣ የሶማሊላንድ ባለስልጣናት ግን እውቅና ቀድሞውንም ተረጋግጧል ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣን  አቶ መስጋኑ አርጋን  የብሄራዊ ደህንነት  ዳሪክተር  አቶ ሬድዋን ሁሴንን ጨምሮ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የሶማሌላንድ የስምምነቱን ትርጉም የሚደግፉ ይመስላሉ።

"ስምምነቱ ሁለንተናዊ ጥቅም ነው፣ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ወታደራዊና የስለላ ልምዷን  ታካፍላለች፣ ስለዚህ ሁለቱ መንግስታት የጋራ ጥቅሞችን በማስጠበቅ ላይ መተባበር ይችላሉ" ሲሉ  አቶ ሬድዋን ሁሴን በጥር 1 ቀን የስምምነቱ ፊርማ ላይ ተናግረው  ነበር። "ይህንን ለማመቻቸት ኢትዮጵያ በሶማሊላንድ የጦር ሰፈርና  የንግድ ባህር ቀጠና ትቋቋማለች።" ብለውም አክለው ነበር።

 በኢትዮጵያና በሶማሌላንድ መካከል ያለው የወታደራዊ ትብብር  ማድረግ የሶማሊያ መንግስት መሪዎችን እንደሚያሸብር ጥርጥር የለውም፣ ለዚህም ነው የሶማሊላንድ እውቅና ፍለጋ፣ መሪዎቿ ከሶስት አስርት አመታት በላይ ሲፈልጉት የነበረውን  አላማ  ለማሳካት  ከኢትዮጵያ ጋር የወደብ ስምምነት  መሪዎቹ ያደረጉት ።

"ታላላቅና መካከለኛ  የሆኑ መንግሥታትን ጨምሮ አብዛኛዎቹ  ሀገራቶች  ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠቱ መረጋጋትን  በአህጉሩ  ላያመጣ ይችላል ብለው ይፈራሉ" ሲሉ  ፕሮፌሰሩ አሌክሲ ይልነን  ተናግረዋል። "የፌዴራል ሶማሊያን አንድነት እና ሰላም እና የመንግስት ግንባታን ለመደገፍ  መሪዎቿ  መርጠዋል።" በማለት ፕሮፌሰሩ አሌክሲ ይልነን አስተያየታቸውን አጠቃለዋል።

 

የሶማሊያና የሶማሊላንድ፡ ዋና ዋና ልዩነቶች

 

ሶማሌላንድ በ1991 ከሶማሊያ ተገንጥላ ነፃነቷን ያወጀች በሰሜን ሶማሊያ የምትገኝ ራሷን  ነጻ ሀገር ብላ የጠራች ሀገር  ነች።

የትኛውም የውጭ ሃይል የሶማሌላንድን ሉዓላዊነት እውቅና አልሰጥም ነገር ግን በገለልተኛ መንግስት፣ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እና የተለየ  ሀገራዊ  አስተዳደራዊ ስራዎችን እያከናወነች ነው።

የሶማሌላንድ ስታቲስቲክስ

ዋና ከተማ፡ ሃርጌሳ (ነፃነት በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና አልተሰጠውም)


የህዝብ ብዛት: 3.5 ሚሊዮን


ዋና ቋንቋዎቿ፡ ሶማሊኛ፣ አረብኛና እንግሊዘኛ ናቸው።


ዋና ሃይማኖቷ: እስልምና


ምንዛሬ: የሶማሌላንድ ሽልንግ 

በሶማሌላንድ 2022 የምግብ ችግር

በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙት ኢትዮጵያና ኬንያ ጋር ሶማሊላንድ፣ ከተመዘገበው የከፋ ድርቅ  ካጋጠማቸው ሀገሮች አንዷ ነች።

በሶማሊያ በአሁኑ ጊዜ ከ7 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የምግብ ዋስትና እጦት ተጋርጦባቸዋል—213,000 ሰዎችን ጨምሮ ለከፍተኛ ረሃብ ተጋልጠዋል። ወደ 3 ሚሊዮን የሚጠጉ የቤት እንስሳትም በድርቅ እና በውሃ እጥረት ሞተዋል።

በእርሻ ላይ ጥገኛ የሆኑት በሶማሊያ ና በሶማሊላንድ የሚኖሩ ሴቶችና ልጃገረዶች በተራዘመው ድርቅ ክፉኛ እየተጎዱ ነው። ለከብቶቻቸው ውሃና ምግብ አጥተው ቀለብና መጠለያ ፍለጋ ቤታቸውን እየለቀቁ ነው።

በሶማሊላንድ፣ የአክሽን ኤይድ የድንገተኛ አደጋ ቡድኖች ህይወት አድን ምግብ፣ ውሃና ሌሎች ድጋፎችን ለማቅረብ ከአካባቢው አጋሮች ጋር እየሰሩ ነው። ነገር ግን ሁኔታው ​​በፍጥነት እየተባባሰ ነው ስሰዚህ አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ።ብዙ ሰዎች በረሀብ ሳይሞቱ  በአስቸኳይ መርዳት አስፈላጊ እንደሆነ ተገልጿል።

የሶማሌላንድ ታሪክ ምንድነው?

ሶማሌላንድ ከ 1800 ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ ከሶማሊያ የተለየች ክልል ነች። እ.ኤ.አ. እስከ 1960 ድረስ በእንግሊዝ  የተያዘች ሀገር ነበረች (ማለትም ጥገኛ ግዛት ማለት ነው፣ የእንግሊዝ መንግስት ውሱን ስልጣን የተጠቀመበት ጊዜ ነበር)።
 

ለአምስት ቀናት ብቻ ነፃ የሆነችው ሱማሌላንድ።

በዚህ ጊዜ በጣሊያን አገዛዝ ሥር ከነበረችው ከአሁኗ ሶማሊያ ጋር ተቀላቀለች፣ ረጅም እና ብዙ ጊዜ የከረረ ትግልም  ጀመረች።

በሶማሌ ላንድ በ1980ዎቹ የሶማሌ ብሄራዊ ንቅናቄ (SNM) የተባለ አማፂ ቡድን ተፈጠረ። እ.ኤ.አ. በ1991 ወታደራዊው አምባገነኑ ሲያድ ባሬ ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ ሶማሌላንድ ነፃነቷን አወጀች።

ዋንኛው  የሀገሪቱ ተዋጊ  ኃይል ኤስ ኤም ኤስ ሃርጌሳን የሶማሌላንድ ዋና ከተማ አድርጎ  አወጀ።ምንም እንኳን በአለም አቀፍ ደረጃ እስከ ዛሬ ድረስ እውቅና ባይኖራትም።

በቀጣዮቹ አስር አመታት ውስጥ  ሀገሪቷ የምትመራበትን  ፖሊሲ ኤስኤንኤን አዲስ ህገ መንግስት ለሶማሊላንድ ፈጠረ፣ በ2001 በህዝቡ አማካይነት  ህዝበ ውሳኔ ስምምነት የተደረሰበት ጊዜ ነበር።

ሶማሌላንድ ለምን የተለየ ሀገር አይደለችም?

የሶማሌላንድ ነፃነትን የሚደግፉ ወገኖች ጠንካራ የይገባኛል ጥያቄ አላቸው።ምክንያቱም ክልሎቹ በባህልና በጎሳ  ከሱማሊያ  ጋር  የተለዩ ናቸው ብለው ይናገራሉ።

ሶማሌላንድ የራሷ ገንዘብ አላት ፣የራሷ ወታደር ፣ፓስፖርት አውጥታ የራሷን ምርጫ ታካሂዳለች ።ይህም እንደ አውሮፓ ህብረት ባሉ አለም አቀፍ አጋሮች ታዝቢነት የተካሀደ  ምርጫ ስለሆነ  ምርጫዋ ተሞካሽቷል።

ከሶማሊያ የበለጠ የተረጋጋች  ሀገር ስትሆን ፤ ከ 2008 ጀምሮ ብዙም የአሸባሪዎች እንቅስቃሴ አይታይበትም።

ነገር ግን በተለይ በአፍሪካ ህብረት የሶማሊላንድ  መንግሥትን መደበኛ  በሆነ ሁነታ እውቅና መሰጠቱ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ያሉ የመገንጠል ንቅናቄዎችን የሚያነሱ ብሄሮችን ነፃነታቸውን ለማወጅ የሚፈልጉ ሽምቅ ተዋጊዎችች ስላሉ እነሱን ያበረታታል የሚል ስጋት አለ።

ምንም እንኳን በአለም ደረጃ በአንፃራዊነት የተረጋጋ ክልል ቢሆንም ፣እጅግ በጣም ድሃ ነው - የአለም ባንክ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት በነፍስ ወከፍ 348 ዶላር (£267) ብቻ  እንደሆነ ገምቷል ፣ይህም ከአለም አራተኛዋ ድሃ ሀገር  እንድትሆን ያደርጋታል።

የአየር ንብረት ለውጥና ዛሬ በሶማሌላንድ ላይ ያሉ ተግዳሮቶች

ዛሬ ሶማሌላንድ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ለሚከሰቱ ጉዳዮች እጅግ በጣም የተጋለጠች ነች።

ለዓመታት የዘለቀው ከባድ ድርቅ፣ረሃብና ሌሎች አደጋዎች ሰዎች ወደ ሰብአዊ ቀውስ እንዲገቡ አድርጓቸዋል።

እ.ኤ.አ. በ2017 ካበቃው የሁለት አመት ድርቅ ለማገገም የሚታገሉ ማህበረሰቦች አሁን በሶስት አስርት አመታት ውስጥ ከታዩት የዝናብ ወቅቶች አንዱ የሆነውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሶማሊያ/ሶማሊላንድ ክልል 2.2 ሚሊዮን ሰዎች ለረሃብ የተጋለጡ መሆናቸውን ተናግሯል።

ይህም በሶማሌላንድ ላሉ ሴቶችና ልጃገረዶች ህይወት እጅግ በጣም ከባድ ሊሆን ይችላል።

98% የሚሆኑ ሴቶች የሴት ልጅ ግርዛት እንደተፈጸመባቸው ይገመታል።በአስር ሺዎች ለሚቆጠሩት ሴቶች እና ልጃገረዶች በአገር ውስጥ ለተፈናቀሉ ሰዎች ካምፕ ውስጥ ለሚኖሩ፣ የማያቋርጥ የጥቃት ሰለባም እየሆኑ  እንደሆነ ተነግሯል።

ለዚያም ነው አክሽን ኤይድ በሱማሌላንድ በሚገኙ የተፈናቀያ ካምፖች ውስጥ የሚሰራው፣ ሴቶችና ልጃገረዶች ከጥቃት እንዲድኑ ለመርዳትና ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለማስቆም ነው።

በመላው ሶማሊላንድ ውስጥ የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቆም፣የልጃገረዶችን ትምህርት ለመደገፍና ሴቶችን ከድህነት ለማውጣት ፤ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም በሚያስፈልጋቸው መሳሪያዎችና ክህሎቶች ለማሰልጠን ከሴቶች ቡድኖች ጋር  አክሽን ኤይድ እየሰራ ነው።

በሶማሌላንድ ሪከርድ የሰበረ ድርቅ

የአፍሪካ ቀንድ በአሁኑ ወቅት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ፣ የነዳች ዋጋ በኃይል  መጨመርና  ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዙ አደጋዎች ምክንያት ከተመዘገበው እጅግ የከፋ ድርቅ አንዱ  እየተመዘገበ ሲሆን ይህም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና  እየጠነከረ ነው።

የ90 ዓመቷ አሚና በሶማሌላንድ 12 የተለያዩ ድርቅዎችን አሳልፋለች፣ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ካጋጠሟት ሁሉ የከፋ እንደሆነ ትናገራለች።

“ድርቁ ክፉኛ ጎድቶናል” ትላለች።

«ውሃ የለንም። ነዳጅ በጣም ውድ ነው።ማሽላ፣ ሩዝ፣ ፓስታና ማካሮኒ እንበላ ነበር። አሁን ግን እነዚህን ምግቦች ለመግዛት የሚያስችል ገንዘብ የለንም። እየተራበን ነው።» ብላለች።
ለአደጋ ጊዜ የድርጊት ፈንድ የሚደረግ ልገሳ እንደ አሚና ላሉ ሰዎች ሕይወት አድን ምግብ፣ ውሃ እና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎችን እንዲሰጥ  ይረዳናል በማለት አክሽን ኤይድ ይገልጻል። ( ይቀጥላል)