የቃየን መንገድ ምነው ኢትዮጵያኖች ጋር በረታ !


 ከወሰንሰገ መርሻ ደምሴ

(ደራሲ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሀያ

አንድ ገበሬ ያደለበውን በግ ገብያ ለመሸጥ አንገቱን አስሮ ወደ ገቢያ እየጎተተ ይዞ ይሄዳል አሉ ። እናማ  በአካባቢው  የታወቁ ሦስት ጓደኛሞች የሆኑ ሌቦች መንገድ ላይ በጉን እየጎተተ ይዘው  ሲሄድ ያዩታል።ሦስቱ ሌቦች «ይህን በግ ከዚህ ሰውዬ ላይ እንዴት ብለን ነው  መውሰድ የምንችለው?»በማለት መመካከር ይጀምራሉ።ከመካከላቸው አንዱ «ለምንድን ነው  ሰውየውን እየጎተትክ ያለኸ ው ውሻ

..ምንልታደርገው  ነው ?ብለን በየተራ  ሰውየውን ብንነግረው!.. በጉ ውሻ ይመስለውና ፈቶ ሲለቀው... የዛን ጊዜ  ይዘን መሄድ እንችላለን!... »በማለት ይህን ከመሐላቸው  አንዱ  ይህን  ሀሳብ ያቀርባል።

በሀሳቡ ሁሉም  ከተስማሙ  በኋላ ከሦስቱ አንደኛው  ወደ ሰውየው ጠጋ ብሎ «እንዴ!... ሰውዬ ..! በገመድ እየጎተትክ  ያለውን ውሻ ምን ልታደርገው  ነው?» ሲል ይጠይቀዋል።

ሰውየውም  ደንገጥ ብሎ «እንዴ!.. ምን ማለት ነው ? ..የምን ውሻ ነው የምትለው?... በግ  እኮ ነው!»ብሎ  ይመልስለታል።ሌባው «ተሳስታሀል !..ይሄ በግ ሳይሆን ውሻ ነው!.. ዓይን በደንብ አያይም ማለት ነው? መነፅር አደርግባት ካልሆነም ካሮት በደንብ ብላበት»በማለት ጥሎት ይሄዳል።ትንሽ እንደተጓዘ ሁለተኛው  ሌባም በግ ወደ ሚጎትተው  ቀረብ ብሎ  በተራው  አንደኛው  ሌባ ያለውን ይደግማል «እንዴ ሰውዬ!.. በገመድ እየጎተትክ ያለውን ውሻ ምን ልታደርገው  ነው?»ሲል ይጠይቀዋል።ሰውየው  አሁን የያዘውን በግ ተጠራጥሮ መልከት ካረገ በኋላ «እንዴት ነው  ነገሩ !..ወቸው  ጉድ!

ሰዉ  ጤነኛ አይደለም  ማለት ነው?...ይሄኮ ውሻ ሳይሆን ያሳደኩት በጌ ነው!» በማለት በመገረም  ይመልሳል። ሌባውም «ባክህ ..ዓይንህን በደንብ አድርገ ተመርመር !..በግ ሳይሆን እየጎተትክ ያለኸው  ውሻ ነው!»ብሎት ጥሎት ይሄዳል።ሰውየውም  ተጠራጥሮ ቆሞ በደንብ ዓይኑን አሽቶ ተመልክቶ «ሰዉ ሁሉ አብዷል ማለት ነው? እነሱ ናቸው የተሳሳቱት!.. ውሻ ሳይሆን በግ ነው»በማለት በጉን

እየጎተተ ይዞ ይሄዳል።

አሁንም ትንሽ እንደተጓዘ  ባልተራው  ሦስተኛው  ሌባ  ይጠብቀውና «ምነው  ጃል!...ሰውየው  ደና አይደለህም  ውሻ እንደ በግ እየጎተትክ ትሄዳለ »ይለዋል።«አረ ውሻ ሳይሆን በግ ነው »በማለት ይመልሳል።ሌባውም«ሰውየው  ጤነኛ አይደለም  እንዴ? የምን በግ ነው!.. ውሻ ነው እንጂ!.. ከፈለክ ሌላሰው  ጠይቅ ይለዋል?» ሰውየውም ተገርሞ ከዚህ በፊት ሌሎች ሁለት ሰዎችም  ተመሳሳይ ነገር ነው  ያሉኝ በማለት ።ያሳደገውን በግ ገበያ ይዞ ሄዶ ማረጋገጥ እየቻለ ይህን ሳያደርግ 

ውሻ ነው!.. ብሎ ፈቶት ለቀቀው።

 

 ሌቦቹም  በጉን ቀልበው  ይዘው  ሄዱ።አንዳንዴ  «ውሽት ሲደጋገም እውነት ይሆናል» የሚባለው  ለዚህ ነው።

 ብዙ ጊዜ ልክ ከላይ እንደቀረበው  ተረት አይነት

በተለያዩ ወቅት የምንሰማቸው  የማደናገሪያና የማወናበጃ የውሸት ወሬዎች ተደጋገመው  እውነት የሚሆንበት ጊዜ ያስተዋልን በርካታዎች ነን ።

  በተለይም በማህበራዊ

ሚዲያዎች ላይ የምንመለከታቸው  አንዳንድ ወሬዎች እንዲሁም

በፖለቲካና በንግድ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የሚያቀርቧቸው  ንግግሮች ፤በአብዛኛው  በዚህ በኩል ግንባር ቀደም  ተጠቃሾች ናቸው። በዓለም ላይ ያሉ አብዛኛው  ፖለቲከኞች  ኃያል የተባሉ  ሀገር የሚመሩ  ፖለቲከኞች ጨምሮ እስከ ድሀ እንደኛ ያሉ የሀገር መሩዎች 

ካልወሹ ሕዝባቸውን መምራት የማይችሉ የሚመስላቸው  በርካታዎች ናቸው።ዛሬ የተናገሩትን የማይደገሙ  ፖለቲካኞች  በየጊዜው እየተበራከቱ መሄድ ብቻ አይደለም  ሌላው ቢቀር የሚያወሩት ውሸት እውነት እንዲመስል በማድረጉ በኩል

በኢኮኖሚ  ካደጉት ሀገሮች የአፍሪካ ፖለቲከኞች ብዙ አለመማራቸው ጉድ የሚያሰኝ ነው።ነገዴም እንደዛው  ነው ካልዋሸ ንግድ መነገድ አይችልም።ቀኑን ሙሉ ሲዋሽ ይውልና በዱአ ማታ ላይ ውሸቱን ያወራርድና ተኝቶ ሲነጋ ተመልሶ ወደ ውሸት ይገባል።ሕይወት እንዲህ እያለ በዓለም ላይ ፀሐይ መሬትን በዛቢያው  ላይ እንደምትዞረው  ሁሉ ውሸትም  በእያንዳንዳችን ሕይወት ላይም  መሽከርከሩን

ይቀጥላል።

  አንድ ነጋዴ  በአንድ ወቅት ያሉኝ አባባል ይህንኑ የሚያመለክት ነው።«እኛ ነጋዴዎችና ፖለቲከኞች አንድ ነን!ካልዋሸን ሥራችንን መስራት አንችልም »ብለውኝ ነበር።

 ነጋዴው ፖለቲከኞችን ውሸታሞች ናቸው  ይላለ።እነሱ ደግሞ  ሲሸጡ ብቻ አይደለም የመንግሥት ግብርና ቫት ወይንም ታክስ  እንዲከፍሉ ሲጠየቁ ማጭበርበርና ማታለል 

ወይም  መዋሸት የተለመደ ትውፊታዊ  እሴት ሆኖ ቀርቷል።«ጫማ  አለኝ ብለህ እሾህ አትርገጥ።

አፍ አለኝ ብለህ በሰው  አታላግጥ።»እንደሚባለው የአባቶች ብሂል  መሆኑ ነው። 

 

ስለ ውሸት ወዳጆቼ  ይህን ያህል ካወራን  ዘንዳ ተቃራኒ(አንታይ)ስለሆነው  እውነት ደግሞ  ትንሽ እንጨዋወት።

 ከዛ አስቀድሞ  ግን ለመሆኑ በተሰማራንበት  ሙያም ይሁን በምንኖርበት  ማህበረሰብ ውስጥ  እውነታ

 ይዘን የምንጓዝ  ስንቶቻችን እንሆን? ብዙ ዎቻችን  ስለማንተማመን የፃድቃን የሰማዕታት ስምን እየጠራን ሰዎች የተናገርነውን እንዲያምኑልን  እንፈልጋለን።ይሁንና በኅይማኖታችን የአምላክህን ስም  በከንቱ አትጥራ ብሎ  ስለሚያዝ እውነት የሆነውን እውነት ! እውነት ያልሆነውን እውሸት ማለቱ በቂ  መሆኑን የኅይማኖት አባቶች በተደጋጋሚ  ሲናገሩ  ሰምቻለው።በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥም  ለሙሴ ከተሰጡት አሥርቱ ትህዛዛት መካከል፤በተራ ቁጥር 8  ላይ በሐሰት አትመስክር የሚል ይገኝበታል።ይህ እንግዴ ግዴታ አለመዋሸት  ከተሰጡን ትዕዛዞች መካከል ዋንኛው መሆኑን መዘንጋት የለብንም።በሌላ በኩል  በእኔ እምነት የምንናገረው  እውነትም ይሁን እውሸት እራሳችንን ከማታለል በስተቀር የምንፈይደው  ነገር በተጨማሪ  ያለ አይመስለኝም።ምክንያቱም ለተወሰነ ጊዜ ዋሽተን የፈለግነውን አግኝተን ይሆናል ።ይሁንና አዕይምሯችን በመዋሸታችን ያጣውን የህሊና እረፍት ግን እንድናጣ አድርጎናል።ምክንያቱም  ዳኛው ፤ፈራጁም  ህሊናችን ስለሆነ።ለመሆኑ እውነት ስንልስ ምንድን ነው?

 

 የዐለቃ ኪዳነ ወልደ ክፍሌ መዝገበ ቃላት  እውነት የሚለውን ቃል ትርጉም በተመለከተ  ከገጽ 226-227 አማን 

የታመነ እውነት በውነት ጻዲቅ መጽደት 

እውነተኛ መሆን ፤መርታት በፍርድ ከሐሰት ከበደል መንጻት ፤መጥራት፤መብለጥ፤መሻል(መዝ 16 እና 50ሣራ 1፥22።25፥29፤ዘፍ 30፥26) ጻድቅ እውነተኛ፤ቅን፤መልካም ፤ደግ፤በጎ፤ንጽሕ፤ጥሩ፤ በማለት ይተነትነዋል።

 

 እውነት የሚለው ቃል በግእዝ «ጽድቅ» ወይም «አማን»በግሪክ «አሌቴያ» ሲባል ብሉይ ኪዳን በተጻፈበት በዕብራይስጥኛ ቋንቋ «አሜት» ከሚል ቃል የተገኘ ነው።

 ጽድቅ ሲባል እውነተኛ ሆነ ስሕተት የለበትም ማለት ነው።

 

 ደስታ ተክለ ወልድ  በመዝገበ ቃላታቸው  ጽድቅ የሚለውን ቃል ሲተረጉም«ረታ» እውነተኛ ሆነ፤ከሐሰት ከኅጢአት ተለየ፤ከዚህ የተነሳ መንግሥተ ሰማያት ገባ፤ከኩነኔ ራቀ፤በነፍስ ተጠቀመ በመንፈሳ ዊ ክብር ከበረ» በማለት ይገልጹታል።

 

እውነት ማለት ትክክል ማለት ነው።በሌላ አነጋገር እውነት የውሸት ተቃራኒ ነው።በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥም «ከእናንተ ማንም ከእውነት ቢስት አንዱም ቢመልሰው»(ያዕ.5፥19)ውሸት ከእውነት መሳት ወይንም ማፈንገጥ እንደሆነ ያስረዳናል።ከእግዚአብሔር ባሕርይ ጋር የማይስማማ ሕይወትና  ከእግዚአብሔር ጋር የሚቃረን ንግግር ሁሉ ከእውነት የራቀ ነው።

 ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ  መል እክቱ ላይ ምዕራፍ 2 ቁጥር 8 ላይ «ለዐመፃ በሚታዘዙ እንጂ ለእውነት በማይታዘዙትና በአድመኞች ላይ ቁጣና መቅሠፍት ይሆንባቸዋል» በማለት እንደገለፀው ፤ በአንድ ጊዜ ለእውነትና ለሐሰት መታዘዝ  እንደማንችል ፤አንደኛውን መምረጥ እንዳለብን ፤ለእውነት የማንታዘዝ ሰዎች ዐመፀኞች፣አድመኞችና ሐሰተኞች እንደምንባል፤በውሸት መንገድ የምንሄድ ሰዎች ፍጻሜያችን የእግዚአብሔር ቁጣና መቅሠፍት እንደሆነ ያስረዳናል። 

 

 እውነተኛነት ፍጹምነት ነው፤እግዚአብሔር የእውነተኛ አምላክ እንደሆነ ሁሉ ፤ቃሉ ም እውነት ስለሆነ ፤እውነትም እግዚአብሔር ስለሆነ ፤የሰው ልጅም በባህሪውና በአምሳሉ የፈጠረን ስለሆነ እኛም እውነተኞች መሆን የግድ ይኖርብናል ።

 

  ዋናው ቁም ነገር መረዳት ያለብን ነገር እውነት ሰዎች የሚፈጥሯት ወይም  የሚያኖሯት አይደለችም።ስለ እውነት ልናውቀው  የሚገባን ነገር ከእውነት ጋር አብረን ልንቆምና በእውነት መንገድ ልንሄድ ይገባናል።ይህ ማለት በእኛ አስተሳሰብና በእኛ ውሳኔ እውነትን እናገራለው ብለን ብቻ የሚተገበር አለመሆኑን ማወቅና መረዳት ይኖርብናል።

 

  አንዳንዴ  እውነትን እንናገራለን ብለን ውሸት የምንናገር ሰዎች አንኖርም? ከዚህ አንፃር እውነት በራሷ ዛቢያ ላይ ቆማ ያለች፣የምትኖርና ልትለወጥም  የማትችል እንደሆነች መረዳት አለብን።በመሆኑም ፈለግንም  አልፈለግንም በእውነት ላይ አንዳችም ነገር ማድረግ አንችልም ።ይህ ማለት እውነት ውሸት እንዲሆን ማድረግ አንችልም።

 

 በእርግጥ ሰዎች እውነት የሆነውን ነገር ዐውቀው  እውነትን ሊናገሩ በእውነትም  ሊኖሩ ይችላሉ።ይህን ለማድረግ ግን አስቀድሞ  እውነትን ማወቅ ያስፈልጋል።እውነትን ሳያውቁ በእውነት እኖራለው ብሎ  መደስኮር የሚያስኬድ አይደለም።ብዙን ጊዜ  በርካታ ሰዎች እውነት እንደሚያወሩ ይነግሩናል ይሁንና እውነትን እያወቁ ውሸትን የሚናገሩና በውሸት ውስጥ የሚመላለሱ በርካታዎች ናቸው።እየዋሹ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ መኖር ይቻላል።ዳሩ ግን እውነትን አወቁም አላወቁም ፤ዋሹም አልዋሹም፤ሰዎች  እውነትን ከእውነታው  ሊቀይሯት ውሸትን እውነት ወይም እውነትን ውሸት ማድረግ አይችሉም።ምክንያቱም እውነት አትለዋወጥምና ነው።

ብዙዎቻችን ከእውነት ጋር ብንስማማ  ማለትም እውነትን ዐውቀን የምንኖር ከሆነ እውነተኞች እንባላለን ፤

ይህ ብቻ አይደለም ከፈጠረን አምላካችንም  ጋርም  እንስማማለን።

እውነተኛነት በየትኛውም ኅይማኖት ተፈላጊ ነገር ነው።በክርስቲያኑ ብቻ ሳይሆን፣በቡዲዝሙ፣በሽንቶይዝሙ፣በሂንዶይዝሙ፣በሙስሊሙ ወዘተ.አንድ ሰው መዋሸት በጭራሽ እንደሌለበትና ንግግራችን እራሱ በእውነትኛነት ላይ የተመሠረተ ከመሆኑም ባሻገር ስናስረዳ እንኳን የምናወራው  ነገር ተአማኒነት እንዲኖረው  ከፈለግን በማስረጃ የተደገፈ መሆን እንዳለበት በኅይማኖታቸው ተምህርቶቻቸው  ላይ ያብራራሉ።ስለሆነም  የሰው ልጅ እውነትን ዐውቆት በእውነት ይኖራል እንጂ ሰዎች የራሳቸው  እውነት የላቸውም።ይህ ማለት ሰዎች እውነትን ራሳቸው የሚፈጥሯት ወይም በሰዎች ላይ የተመሰረተች አይደለችም። ምክንያቱም እውነት አንድ እንጂ ብዙ እውነቶች አይኖሩምና።በክርስቲያን ኅይማኖት ትምህርት እውነት እግዚአብሔር ነው፤የእግዚአብሔር ባሕርይ ነው።ብዙ እግዚአብሔር እንደሌለ ሁሉ ብዙ እውነቶች የሉም።በመሆኑም  እውነተኛ ሆንን ማለት፤እግዚአብሔርን እናውቃለን፤እግዚአብሔርን እንመስላለን፤ስለ እውነት እናወራለን በእውነትም መኖር እንጀምራለን።ማለት ነው።በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 8 ቁጥር 32 ላይ እንዲህ ይላል።«እውነትን ስናውቅ በእውነትም ስንኖር እውነት አርነት ታወጣናለች።በእውነት የማይኖር የሐሰት ባሪያ ነው» በማለት መጽሐፍ ቅዱሳችን  የሚናገረው  ለዚህ ነው።

 «በልብ ከሸሸጉት እውነት በግል የተቀበሉት እሳት ሳይበልጥ ይቀራል? »የሚባል አባባልም አለ።

 

 ከላይ ለማንሳት እንደሞከርኩት እውነት

 የእግዚአብሔር ባህርይ እንደሆነ፤የውሸት ተቃራኒ(አንታይ)መሆኑን፤እውነት የማይለዋወጥ ዘላለማዊ ከመሆኑም ባሻገር የሰው ልጅ ምንም ሊያደርግ እንደማይቻል በጥቂቱ ለመመልከት ችለናል።

 በተረፈ በርካቶቻችን የምናስባቸውና የምናቅዳቸው በርካቶች ነገሮች ይኖሩናል።ታዋቂ ሰው መሆን፣ባለጠጋ መሆን፣

ባለሥልጣን መሆን፣በትምህርታችን ውጤታማ መሆን ወዘተ.ፍላጎታችንን ለማሳከት እንጥራለን።

እነዚህን ምኞታችንን ለማሳከት አታለንም ሆነ አጭበርብረን አሊያም  ዋሽተን  ወይን ም ጉቦ ሰጥተን ስኬታማ  ልንሆን እንችላለን።ይሁንና ስኬታችን ጣፋጭ  የሚሆነው ከላይ ከተነሳው  ነጥብ በተቃራኒ መልኩ ሆኖን ስንገኝና ጥረታችን በእውነት ላይ የተመሰረተ ቢሆን ነው የሚመረጠው።ከዚህ ሌላ ወንድማቸውን እየበደሉና እያሳዘኑ ፤በጥላቻና በክፋት በተሞላ ኑሮ ውስጥ  ተዘፍቀው  አካሄዳቸውን ያበላሹ ወገኖች እራሳቸውን መፈተሽ እንደሚኖርባቸው  ከወዲሁ ሳላሳስብ  አላልፍም።

  በእርግጥ ቃየን ወንድሙን አቤልን ቡክርናውን ለመውሰድ ገደለው እያልን ታሪኩን ማውራት ብቻ ሳይሆን ራሳችንንም ፊታችንን በመስታወት ፊት ቆመን እንደምንመለከተው ሁሉ  የራሳችንን ሰብዕናና ሕይወትንም በእውነት መንገድ እየሄድን ነው  ወይ ብለን መመልከት  ያስፈልጋል።በክፋትና በምቀኝነት ተሞልተን ፤እየዋሸንና እየቀጠፍን፤የተጣላናቸውንና የበደሉንን ይቅር ሳንል ወደ ቤተክርስቲያን ጠዋት ማታ ያለማቋረጥ  ብንመላለስ ለእግዚብሔር የምናቀርበው  መስዋዕት ሁሉ ከንቱና የቃየን አይነት መሥዋዕት ነው የሚሆነው።

በተለይም በዚሁ በሀገራችን

ወንድሙን የሚጠላና ወንድሙን የሚያሳድድ ምእመንና የቤተክርስቲያን አባቶችና ወንድሞች በርካቶች ናቸው።

እነዚህ የቃየ ልጆች ናቸው  እንጂ  የክርስቶስ ልጆች አይባሉም

ዛሬ በዘመናችን የአቤልና የቃየን ልጆች በአገራችን ውስጥ በርካቶች አሉ።ቃየን አቤልን እንዳሳደደውና እንደ ገደለው  እንዲሁ በጥለቻ ፥በቅናትና በክፋት ልባቸውን ሞልተው፤በእግዚአብሔር ፊት ቅዱስ ስሙን እየጠሩ መሥዋዕታቸውን ይዘው የሚያቀርቡ ነፍሰ ገዳዮች የሆኑ መተተኞች የሆኑ ካህናቶች፣ደብተራዎች፣ዲያቆኖች አሉ።እንደ አቤል ደም በግፍ የተገደሉ፣ንብረታቸውን የተዘረፉ፥ከሥራ የተፈናቀሉ ከቤተክርስቲያንና ከአገር የተሰደዱ፤በእግዚአብሔር ፊት የሚጮኹ  የየዋሃን ምእመናን(ናት)ብቻ ሳይሆን በግፍ የተገደሉ የበርካታ ኢትዮጵያውያን ነፍሳት ምድራችንን ሞልተውታል።

በእርግጥ ይህን የሚያደርጉ ኢአማንያን ቢሆኑ ኖሮ አያደንቅም ነበር።ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ፊት የሚጸልዩ ፣ቁርባን ይዘው የሚያቆርቡና የሚቆርቡ፤በክርስቲያንነታቸው የሚማጻደቁና ስለ ሃይማኖታቸው የሚቆረቆሩ የሚመስሉ  ሰዎች መሆናቸው ግን ነገሩን ይበልጥ አሳዛኝ ያደርገዋል።

 የቃያን መንገድ የክፉው መንገድ ነው።የጥላቻ ፥የቅናት ፥የመግደል መንገድ ነው።ሰውን በድንጋይ ወርውረን  ፤በዱላ ደብደብን ወይም በጥየት ተኩሰን ላንገድለው እንችላለን።ማንም ወንድሙን የሚጠላ ሰው ሁሉ እርሱ ነፍሰ ገዳይ ነው እንዳለው ሐዋርያው  ዮሐንስ  ነፍሰ ገዳይ መሆን አይኖርብንም ምክንያቱም  ነፍሰ ገዳይ ወንጀለኛ ነው ፤ወንጀለኛ ደግሞ ኅጢአተኛ ነው።ስለዚህ  ኅጢአተኛ ደግሞ በሞት ውስጥ ያለ ነው።ውሸት ከኅጢያት መንገዶች አንዱ ነው።በአሁኑ ወቅት በአገራችን በብዛት የሚስተዋለው ደግሞ ውሸትና የውሸት ካባ ደርበው የሚንቀሳቀሱ ወገኖች ናቸው።እንዲያውም  «ውሽት ሲደጋገም እውነት ይሆናል» እንደሚባለው ውሸታቸው ተደራርቦ ተደራርቦ እውነት እየሆነ በመምጣት ላይ ይገኛል። እነዚህ  የቃየ መንገድ ዛሬም አለ።የቃያን መንገድ የሚከተሉ በልባቸው  የክፉ፣የጥላቻ ፣የቅናት  ፥የመግደል መንገድ ነው።ሰውን በድንጋይ ወርውረን  ፤በዱላ ደብደብን ወይም በጥየት ተኩሰን ላንገድለው እንችላለን።ይሁንና በክፋትና በተንኮል ተነስተን በሰው ልጅ ላይ የምንወረውረው  ቀስት ምንም እንኳ ትንሽ ጊዜ ሰውየውን ቢጎዳውም መልሶ ግን

ጊዜውን ጠብቆ እራሳችንን መውጋቱ አይቀሬ ነው።ምክንያቱም እውነት ምንግዜም እውነት ነው።እውነትን የያዘ ሰው ምንም እንኳ ችግርና መከራ ቢደራረበትም  የእውነት አምላክ የቃየን ሰዎች 

የወረወሩትን የክፋትና የተንኮል ቀስት መልሶ ወደ ወረወረው  ግለሰብ ላይ ይተክለዋል።

ስለሆነም እውነትን ይዘን ስለእውነት መጓዝ ይኖርብናል።እላለው።አበቃው !ክብረት ይስጥልኝ !