የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት በምስራቅ አፍሪካ ላይ አደጋ ሊፈጥር ይችላል?


ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ

(ደራሲ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሀያሲ)

 

ቀደም ሲል በአሸባሪዎች ጥቃቶች እና በድንበር ውዝግቦች የተበጣጠሰችው የሱማሊያ  ክልል የሶማሊላንድ የሶማሊያን ሉዓላዊነት ለመናድ የወሰደችው ውሳኔ በእርግጥ ውድቅ  ማድረግ አትችልም።በየትኛው የህግ መስፈርት ይህ አካሄዷ አዋጪ እንዳልሆነ እሙን ነው።

 

ወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ የሚገኘውን የበርበራ ወደብን ለማግኘት በጥር 1 ከሶማሌላንድ ጋር የመጀመሪያ ስምምነት ከተፈራረመች በኋላ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለው ውጥረት እየጨመረ መጥቷል

 

ሶማሌላንድ የተገነጠለች የሶማሊያ ክልል ነ። እንደ ነጻ ሀገር በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና አልተሰጣትም።

 

ውጥረቱን ለማርገብ ለሳምንታት የተደረገው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ከከሸፈ በኋላ ሞቃዲሾ አዲስ አበባ አወዛጋቢውን የባህር ላይ ስምምነቱን እስካልሰረዘች ድረስ ምንም አይነት ሽምግልና ሊኖር እንደማይችል በመግለጽ  ክስምምነቱ ተቃራኒ  የሆነ   ቃል ተናገራለች።

 

ከዚህ ሌላ በቅርቢያዋ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ባርበራ የሚያደርገውን ጉዞ የሶማሊያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የአየር ክልሉን ተጠቅሞ ወደ ሶማሌላንድ እንዳይበር መከልከሉ ውጥረቱን ይበልጥ እንዲጨመር አድርጎታል  ።

 

በአህጉሩ የታየው  ይህ ቀውስ ኤርትራን እና ጅቡቲን በሚያጠቃልል  መልኩ ብቅ ማለቱ ደግሞ  ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት  ያላት ውስብስብ ታሪክ ላይ  እንዲያተኩር  ማድረጉም አልቀረም ። እነዚህ ሀገራት በአሁኑ ወቅት  ሁሉም የሚገኙት በምስራቅ አፍሪካ ሲሆን በአንፃሩ ከየመን ቀይ ባህርን ተሻግሮ በሃውቲዎች ላይ በዩናይትድ ስቴትስ እየተወሰደ  ያለው እርምጃ እንዲሁም ቀይ ባህር በዘራፊዎች እንቅልፍ ማጣቷ እንዳለ ሆኖ የኢትዮጵያና የሱማሌ  ላንድ ሌላ ችግር ሆኖ ብቅ ማለቱ ለምዕራባውያን  ሀገሮች ጭምር የራስ ምታት ሆኖ ብቅ ብሎ መጥቷል  ።

 

የተሞላ ስምምነት (Full agreement)

 

ጥር 1 ቀን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የመግባቢያ ሰነድ (MoU) ተፈራርመዋል።

 

የስምምነቱ አካል የሆነው ሶማሌላንድ በቀይ ባህር ላይ ያለውን 20 ኪሎ ሜትር የባህር ዳርቻ የባህር ሃይል ቤዝ እና የንግድ ወደብን ለማቋቋም ለኢትዮጵያ መንግሥት በሊዝ ትከራያለች።

 

በወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ  ፅህፈት ቤት የመግባቢያ ሰነዱ የሁለቱን ሀገራት የጸጥታ፣ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ አጋርነት እንደሚያጠናክር ተናግሯል።

 

ነገር ግን በአለም አቀፍ ህግ  መሠረት ስምምነቱ ችግር ያለበት  ይመስላል። ይህ ደግሞ በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ውጥረት ሊያባብሰው ይችላል።

 

ሶማሌላንድ በ1991 እ.ኤ.አ ከሞቃዲሾው መንግሥት ነፃነቷን አውጃለች።ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በፖሊስና በወታደራዊ ኃይል የሚመራ  መንግሥት መስርታ የራሷ ገንዘብ አውጥታ እንቅስቃሴ  እያደረገች ትገኛለች ። ሆኖም ዓለም አቀፍ እውቅና እስካሁን ግን  ማግኘት አልቻለችም።

 

በአለም አቀፍ ህግ መሰረት እስካሁን ድረስ ሶማሌላንድ የሶማሊያ አካል እንደሆነች ይታወቃል። ለዚህ ነው የዓለም አቀፍ ህግ  መሰረት ስምምቱ ችግር አለበት የሚባለው።ጉዳዩን ይብስ ያወሳሰበው ደግሞ የክልሎች ፉክክር እና ጂኦፖለቲካዊ  የሆነው  የተፈጥሮ አቀማመጣቸው ሁኔታ ነው።ኢትዮጵያ  የባህር ድንበር ሳይኖራት ጠንካራ ባህር ኃይል መገንባታው ለፖለቲካው ጨዋታ ጡዘት  ውሳኝ ሆኖ ብቅ ማለቱ  የሚያስገርም አይደለምምክንያቱም በክልሉ ጠንካራ የመከላከያ ሠራዊት ያላት ኢትዮጵያ ስለሆነች።ምንም እንኳን በውስጧ ያለው የእርስ በእርስ ጦርነት እንዳለ ሆኖ ማለት ነው።

 

ሌላው  የኢትዮጵያ ችግር ግብፅ ጋር በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ  ዙሪያ ከሱዳን ጋር በመሆን ከኢትዮጵያ ጋር ውዝግብ ውስጥ  መግባቷና እስካሁን  ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ የቅኝ ግዛት ስምምነትን ይዛ በማን አለብኝነት ድንፋታ ማሳየቷ  ኢትዮጵያ የባህር ወደብ የግድ እንደሚያስፈልጋት ያረጋገጠ ጉዳይ መሆኑን ማሳየቱም አልቀረም  ። ምክንያቱም እንደ ኢትዮጵያ ጠንካራ መከላከያ ያላትን ግብፅን ለመመከት የባህር ኃይልና ወደብ እንደ ግብፅ ኢትዮጵያ ሊኖራት ግድ ነው።ሌላው ሁቲዎች ፍልስጤማውያንን ለመደገፍ በአቅራቢያው በሚገኘው ባብ ኤል ማንደብ ስትሬት ውስጥ  የውጭ የመርከብ መስመሮችን በአሁኑ ወቅት እያጠቁ  ነው የሚገኙት። ሱዳን በውስጥ  ግጭት ውስጥ መሆኗ   ተደማምሮ ለኢትዮጵያ   መልካም ቢሆንም  ለአካባቢው ሰላም ግን አደገኛ እንደሆነ መገመት አያዳግተንም።

 

በክልሉ ብዙ  ችግሮች እየተከሰቱ  ባለበት ሁኔታ ነው ፤ኢትዮጵያና ሱማሌላንድ ሰጥቶ መቀበል በሚል መርህ ከስምምነት ላይ የደረሱት። 

ከዚህ አንፃር የኢትዮጵያን  በሱማሌላንድ  ያላትን ፍላጎትና ዓላማዎች መተንተኑ  አስፈላጊ በመሆኑ በዚህ ጉዳይ በርካታ ነጥቦችን ለማንሳት ጸሐፊው  ይሞክራል ።ለዛሬም የተውሰኑ ነጥቦችን እናንሳ  ።

 

የኢትዮጵያ ክልላዊ ስትራቴጂ (Ethiopias regional strategy)

 

የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ንግድ ከቀይ ባህር ጎረቤት ሀገራት ጋር ከምታደርገው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጋር የተያያዘ ነው።

 

ስለዚህ ኢትዮጵያ ከኤርትራ፣ ጅቡቲ እና ሶማሌላንድ ጋር ያላት ግንኙነት በውጭ ፖሊሲዋ ቁልፍ ሚና  እንድትጫወት  ያደርጋታል።

 

ኤርትራ ነጻነቷን እስካወጀችበት እስከ 1993 እ.ኤ.አ   ድረስ ኢትዮጵያ የቀይ ባህር መዳረሻ ሀገርና ባለወደብ ሀገር ነበረች።ይሁንና  ለአስርት አመታት የዘለቀው  የእርስ በርስ ጦርነትን አስከትሎ ኤርትራ  ከተገነጠለች በኋላ ግን ኢትዮጵያ ወደብ አልባ ብቻ ሳትሆን አሁን ከተገነጠለችው  ኤርትራ ጋር የድንበር ውዝግብ  ማስከተ  አልቀረም። 

 

ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ  በኋላ በ2018  እ.ኤ.ኤ  ከኤርትራ ጋር የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለው ግንኙነት በከፍተኛ መሻሻሎችን ማሳየቱም ባሻገር የንግድ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ሁለቱ ሀገሮች በማደስ ጥሩ እንቅስቃሴ  ላይ  ነበሩ ።

 

ይሁንና ኢትዮጵያ  ከኤርትራ ይልቅ  በባህር ንግዷ የምትመካት ሀገር ከኤርትራ  ይልቅ  ጎረቤት  ሀገር ጅቡቲ  ብቻ ሆነች 

 

ከጅቡቲ  ጋር ያለው ግንኙነት የጠነከረ ከመሆኑም ባሻገር የኢትዮጵያን የገቢ እና የወጪ ንግድ ከፍተኛ ድርሻ  እንዲይዝ አስችሎታል። በእርግጥም ይህንን ንግድ  ለማሳለጥ በተለይም ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር  ያላትን የንግድ ልውውጥ  ይበልጥ ለማጠናከርና  የንግድ ግንኙነቷን ለማጠናከር ከኢትዮጵያ  እስከ ጅቡቲ  የሚደርስ የባቡር እና የመንገድ ፕሮጀክቶች  በቻይና መንግሥት እርዳታ ታግዞበት ግንባታ ማድረጓና ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ወጪ   ለማድረግ ችላለች።

 

እ.ኤ.አ. በ 2021 የአዲስ አበባ አስተዳደር ይህንን የባቡር መስመር ሶማሌላንድ በርበራ ወደብ ጋር ለማራዘም ፕሮጀክት ይፋ ደረጎ  ነበር።

 

በኢትዮጵያ እና በሶማሌላንድ መካከል የተፈረመው የኢኮኖሚ እና የጸጥታ ስምምነቶች ኢትዮጵያ ከኤርትራ እና ጅቡቲ ጋር ካላት ባህላዊ ግንኙነት በተጨማሪ አማራጭ የንግድ መስመር ያቀርባል ተብሎ የታሰበ  ዕቅድ ነው።

 

ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር ያደረገችው ስምምነት በጅቡቲ ወደብ ላይ ያላትን ጥገኝነት ለመቀየር እና ከኤርትራ ጋር ሊፈጠር ስለሚችል ግንኙነት ከመጨነቅ ለመዳን ስልታዊ አማራጭን እንደተጠቀመች ተደርጎ  ሊገለፅ ይችላል ።ይሁንና  ይህ ሁኔታ ኤርትራን አላስደሰተም።አሁን ድግሞ ከኤርትራ  ይልቅ  ኢትዮጵያ ሱማሌላንድን መምረጧ  ይበልጥ  ኤርትራ በሁኔታው  ቅሬታ  ገብቷታል።ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ያለው የባድሜ ጉዳይና የድንበር ጉዳይ መፍትሄ አለማግኘቱ ሌላው ለሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት መሻከር አስተዋጾ አለው።በእርግጥ ኢትዮጵያ ከትግራይ ክልልና ከኤርትራ ጎረቤት ከሆነችው  ጋር  የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ በገባችበት ወቅት እጅና ጓንት ነበሩ።አሁን ግን ይህ ሁኔታ የለም።

 

ይህ ሁኔታ ተደማምሮ በተጨማሪም ኢትዮጵያ በጅቡቲ ላይ ያላትን ጥገኝነት የመቀነስ ፍላጎት  ያላት እንዳለ ሆኖ ሶማሊያ፣ ጅቡቲ እና ኤርትራ በአካባቢው የጋራ ጥቅም ዙሪያ  በጣምራ እንዳይሰለፉባት ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል። ይህን ካደረገችና እነዚህን ሀገሮች ካላስከፋች ኢትዮጵያ በክልሉ  ያላት ንግድን የማስፋፋት እና የማስጠበቅ  ፖሊሲዋን እዳር ለማድረስ  ትልቅ እርምጃ  እንድትወስድ  ያስችላታል ።

 

ነገር ግን ሶማሊላንድ የሶማሊያ አካል እንደሆነች እያለ  አለም አቀፍ እውቅና መስጠቷ  ፤በተለይም በአዲስ አበባ እና በሞቃዲሾ መካከል የቆዩ በተለይም ከ50 አመታት በዘለቀው ታሪካዊ  የሆነው የሁለቱ ሀገራትን  የጦርነት  ግጭቶችን  ስናጤን በኢትዮጵያ እና በሶማሌላንድ መካከል ያለውን ስምምነት ፈተና  እንፈጠር ማድረጉ አይቀሬ መሆኑን መረዳት  አያቅትም።

 

የአህጉሩ ሃይሎች ምን ይላሉ ?

 

በኢትዮጵያ እና በሶማሌላንድ መካከል የተደረገው የመግባቢያ ስምምነት እንደ አፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ላሉ የአህጉሩ ሀገሮች ሁለቱንም  ወገኖች ለማስማማት ትልቅ  ፈተናዎች ከፊታቸው ስለሚጠብቃቸው ይህን ማለፍ ግድ  ይሆንባቸዋል።

 

ስምምነቱ  አህጉራዊ ኢኮኖሚያዊ ልማትን እና ትብብርን የሚያበረታታ ቢሆንም በክልሉ  ደህንነት እና በፖለቲካዊ ሚዛን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ  ማሳደሩ  አይቀርም። ለምሳሌ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) እና የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ የሶማሊያን ስጋት መፍታት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። ይህን አለማድረግ  ደግሞ  ክልሉ በአሸባሪ ቡድኖች እጅ ሊወድቅ ይችላል።

 

ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው አሸባሪ ቡድን አልሸባብ የሶማሊያን ማዕከላዊ መንግስት ለ17 ዓመታት ያህል ሲዋጋ ቆይቷል። አልቃይዳ በኬንያ እና በኡጋንዳ ጥቃቶችን ፈጽሟል። የኢትዮጵያ እና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ የትኛውም ቀጣናዊ ግጭት የሚመራ ከሆነ ሱማሌ ተጠቃሚ ትሆናለች።

 

እንዲህ ያለው ሁኔታ ደግሞ የአልሸባብን መሰረት ለማጠናከር እና ከሶማሊያ ማህበረሰብ ውስጥ ምልመላ እንዲጨምር ያስችለዋል።

 

አልሸባብ በኢትዮጵያ-ሶማሊላንድ የመግባቢያ ስምምነት ላይ የሰነዘረው ተቃውሞ ስምምነቱን በሉዓላዊነታቸው ላይ እንደ ጥቃት በሚያዩት በሶማሊያውያን መካከል ያለውን አቋም ሊያጠናክር ይችላል ።አሸባሪው  ቡድን  እራሱን የሶማሊያን ጥቅም አስከባሪ አድርጎ  እንዲመለከትና እንዲታይ  ጥሩ  አጋጣሚ እንዲፈጠርለት  ያደርገዋል ።

 

ሌላው ወሳኝ ገጽታ በክልሉ ውስጥ እየተጫወተ  ያለው ሁኔታ( Another critical dimension is at play in the region.)

 

በጃንዋሪ 1 በይፋ የBRICS ቡድን አባል የሆነችው ኢትዮጵያ ከቤጂንግ ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላት። በተመሳሳይ ቤጂንግ የራሷ ግዛት ነው የምትለው ታይዋን ከሶማሌላንድ ጋር ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት መሥርታለች።ይህ ቻይናን አላስደሰተም።

 

የአሜሪካ አቋም 

 

በአንፃሩ አሜሪካ  ደግሞ   ከሶማሊያ ጀርባ  ሆና እንደ ቆመች አሳይታለች ። (The US has put its weight behind Somalia.)

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሀመር በቅርቡ ዋሽንግተን የሶማሊያን «ሶማሊላንድን ጨምሮ ፤ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት፣ አንድነት  » እንደምታምንና  ለግዛት አንድነቷ  እውቅና እንደምትሰጥ ተናግረዋል።

 

 

የዓባይን ውሃ በጋራ ለመጠቀም ከኢትዮጵያ ጋር ፍጥጫ ውስጥ  ያለችው የቀጣናው የከባድ ሚዛን ተፋላሚ  ነኝ የምትለው ግብፅ ሶማሊያን ትደግፋለች። የአረብ ሊግ፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት የሶማሊያን የግዛት አንድነት እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል።ኢትዮጵያም የአረብ ሊግን የተቃወመች ሲሆን ።የማንንም ድንበር እንደማትገፋና ሰጥቶ መቀበል ላይ የተመረኮዘ ስምምነት መፈፀሟን ደጋግማ ትናገራለች።ያም ሆነ ይህ ከዚህ ጀርባ፣ ኢትዮጵያ ክልላዊ ውጥረቶችን ሳታባባስ ንግዷን እና ደህንነቷን የምታጠናክርበትን መንገድ በመፈለግ እነዚህን ውስብስብ ነገሮች በመፍታት ላይ ማተኮር እንደሚኖርባት በማሳሰብ ጽሑፌን በዚሁ ቋጨው ክብረት ይስጥልኝ።