የጃፓን ፖሊሶችና ህፃናቶች


የጃፓን ፖሊሶች በጃፓን ውስጥ  ነገ ቦታውን የሚረከቡ ህፃናትን መንከባከብና ማጫወት የተለመደ ነው።ምክንያቱም ልጆች የፖሊስ ፍቅር እንዲኖራቸው በማሰብ የሚደረግ ነገር  ነው።ከታች በፎቶዎች ውስጥ እንደምታዩት የፖሊስ መኮንን በጃፓን የመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት በመጠለያ ውስጥ ያሉ ልጆችን  በእውነተኛ ፖሊስ መኪና ውስጥ እንዲጫወቱ  ሲያደርጉ  ይታያል።

በፖሊስ መኪና  ውስጥ የከያማናሺ ፕሪፌክትራል ፖሊስ መኮንን በዋጂማ፣ ኢሺካዋ ግዛት ማዘጋጃ ቤት ዋጂማ ጁኒየር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የተጠለሉትን ልጆች  በፖሊስ መኪና ሲያጫውታቸው ይታያል።

ከፖሊስ መኪና ውስጥ ሆነው በማዘጋጃ ቤት ዋጂማ ጁኒየር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዋጂማ ፣ ኢሺካዋ ግዛት ውስጥ ሰላምታ  ሲሰጡም በፎቶው ላይ ይታያል።

ሶታ ሳካጉቺ፣ እና እህቱ አይ በጃንዋሪ ➖ በዋጂማ፣ ኢሺካዋ ግዛት ውስጥ በሚገኘው የማዘጋጃ ቤት ዋጂማ ጁኒየር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፖሊስ መኪና ውስጥ ሲጫወቱ  ይታያል።ይህ በሌላው ዓለም መለመድ  ያለበት ነገር።ልጆች ፖሊስን የሚፈሩ ሳይሆን የሚወዱና ነገ እንደዚህ መሆን አለብኝ ብለው ወደ ዚህ ስራ እንዲገቡ ማበረታታት ጠቃሚ ነው።