የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳን በስም ማጥፋት ከተከሰሱ በኋላ ዳኛው ከችሎቱ ሊባረሩ ይችላሉ


«ራስህን ብቻ መቆጣጠር አትችልም» ዳኛ ልዊስ ካፕላን የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ትራምፕን ከኢ ዣን ካሮል የስም ማጥፋት ችሎት እንደሚያባርሯቸው ከወዲሁ  ዛቱ።

በቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ ኢ ዣን ካሮል ያቀረቡት የፍትሐ ብሔር ስም ማጥፋት ችሎት የፌደራል ዳኛ ሌዊስ ካፕላን ትራምፕን ከችሎቱ ሊገለሉ እንደሚችሉ ከወዲሁ አስጠንቅቀዋል ።የካሮል ጠበቃ በዳኞች ችሎት ውስጥ የንቀት አስተያየቶችን ትራምፕ ሰጥተዋል ተብሏል። ዳኛው የትራምፕ ባህሪ እንዳሳሰባቸው ገልፀው እንዲህ ያለውን የንቀት ሁኔታ  ግምት ውስጥ ማስገባት እንደሌለባቸው ተስፋ አድርገዋል። ትራምፕ ግን እወደዋለሁ በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። ችሎቱ የሚያጠነጥነው ትራምፕ በ1990ዎቹ አጋማሽ የፆታ ጥቃት እንዳልፈፀመባት ሲክዱ ስሟን አጥፍተዋል በሚል የካሮል ክስ ዙሪያ ነው።

በነገራችን ላይ የ2024 ምርጫ የመጀመሪያ እጩ ተወዳዳሪ  ለመሆን ትራምፕ  ባለፈው ሰኞ ማሸነፋቸው ይታወሳል።

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ2024ቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የመጀመሪያ እጩ ፉክክር ወሳኝ ድል በአዮዋ ካውኩስስ ሰኞ  ዕለት አሸንፈዋል።

«የአይዋ ሰዎች ዛሬ ምሽት ግልጽ የሆነ መልእክት ልከዋል፡- ዶናልድ ትራምፕ ቀጣዩ የሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ ፕሬዝዳንት ይሆናሉ» ሲሉ የ Make America Great Again Inc የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አሌክስ ፒፌፈር በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። ሚስተር ትራምፕ ያሸነፉበት መጠን ባይገለፅም ሰኞ ምሽት ማሸነፋቸው ተነግሯል።የቀድሞ የተባበሩት መንግስታት አምባሳደር ኒኪ ሃሌይ እና የፍሎሪዳ ገዥ ሮን ዴሳንቲስ ሁለተኛ ደረጃን ለመያዝ እየተፋለሙ  እንደሆነ  ተጠቁሟል።