ጃፓን ውስጥ አንድ የ62 አመት አዛውንት የውሻቸውን እዳሪ አላግባብ በመወርወር ክስ ተመሰረተባቸው


 እጅ ከፍንጅ  እዳሪውን ሲወረውሩ  የተያዙት የ62 አመቱ  ዋታናቤ `` በግዴለሽነት ነው ያደረኩት።'' ሲሉ  ቃላቸውን ሰጥተዋል።ግለሰቡ በተመሳሳይ ሁኔታ ወደ 20 የሚጠጉ ቅሬታዎች  ቀርቦባቸው እንደነበር ተገልጿል።

ተጠርጣሪው ዩዙሚ ዋታናቤ (62) ውሻውን በሂራቱካ ከተማ ካናጋዋ ከቀኑ 4፡45  ላይ  አካባቢ እዳሪውን  እየሄዱ ይጥሉ ነበር ተብሏል። በ15ኛው ቀን  የውሻዎችን እዳሪ በከረጢት ውስጥ ከትቶ ወደ ጎረቤት ቤት ሲወረውር ፖሊስ  እጅ ከፍንጅ የያዛቸው  ሲሆን ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውሏል።


ዋታናቤ የተከሰሰውን ክስ መመስረቱን አምኖ ''ቀላል  ነገር ነው የሰራሁት'' ሲል ፖሊስ እየመረመራቸው ሲሆን ዋታናቤ የውሻውን ሰገራ ደጋግሞ በመወርወሩ ጥፋተኛ ሊሆን እንደሚችል እያጣራ  መሆኑንና ክስ  የተመስርተበት ሲሆን  ቅጣት ሊጠብቀው እንደሚችል ተገልጿል ።