በጃፓን ቮድካ የገደለው የኪንዲያ የዩኒቭርስቲ ተማሪ


ኦሳካ  ውስጥ  እ.ኤ.አ. በ 2017 በተደረገ ፓርቲ ላይ ከመጠን በላይ በመጠጣት የሞተው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወላጆች 50.9-ሚሊዮን-የን (350,000 ዶላር ገደማ) ከ 16 የቀድሞ ተማሪዎች  ጓደኞቹ ገንዘብ  ለመቀበል ጥር 15 ቀን የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር ። .

በወቅቱ የ20 አመቱ የኪንዳይ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ አመት ተማሪ የነበረው ቶሞሪ በታህሳስ 2017 ከፍተኛ መጠን ያለው ቮድካ እና ሌሎች የአልኮል መጠጦችን አውርዶ በፓርቲው ከጠጣ በኋላ ራሱን ስቶ እስከሚቀጥለው ጠዋት ድረስ ወደ ሆስፒታል  ባለመላኩ  ህይወቱ  ሊያልፍ ችሏል። 

የቶሞሪ ወላጆች በጠበቃቸው በኩል በሰጡት መግለጫ “ሀያቶን በማጣታችን የሚደርስብን ስቃይ እና ፀፀት መቼም ቢሆን አይጠፋም። የተሳተፉት ሰዎች በህይወታቸው እንዲቀጥሉ የሰውን ህይወት ክብደት ጠንቅቀው እንደሚገነዘቡ ተስፋ እናደርጋለን።”በማለት ገልጸዋል።

(ምንጫችን የጃፓን ኒውስ  ነው ))