ኢትዮጵያዊው የናሳ ሳይንቲስት ከ100 ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች አንዱ ሆኑ


ኢትዮጵያዊው የናሳ ሳይንቲስት ብርሃኑ ታፈሰ ቡልቻ (ዶ/ር) በፎቶኒክስ ቴክኖሎጂ ተፅዕኖ ፈጣሪ በመሆን ከ100 ሰዎች መካከል አንዱ ሆነው መመረጣቸውን “The Photonics100” በድረገጹ አስታውቋል፡፡  

ዶክተር ብርሃኑ የተመረጡት በፎቶኒክስ ቴክኖሎጂ ምርምራቸው ሲሆን፣ በዚህም በጨረቃ ላይ ውሃ የሚያስሰውን መሣሪያ ሠርተው ዕውቅና አግኝተውበታል።  

የፎቶኒክስ ቴክኖሎጂ የብርሃን ሞገዶችን በመጠቀም ከሰው ልጆች እይታ ውጭ ያለውን ተፈጥሮ እና ብርሃን በመለየት ለሰው ልጆች ያላቸውን ጠቀሜታ የሚያጠና ዘርፍ ነው።  

 

በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ ዶክተር ብርሃኑ ላገኙት ዕውቅና የእንኳን ደስ አለህ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ 

 

 

https://www.youtube.com/watch?v=957peb33db4