ፊሊፔንስ በስደተኛ አያያዝ ከኢትዮጵያ ብዙ መማር ይገባታል !


 

ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ ( ጮራ ዘ አራዳ) 

ደራሲ ፣ ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሃያሲ 

 

ስደተኞች የትውልድ አገራቸውን በብዙ ምክንያቶች ጥለው በአንፃራዊነት ደህና ናቸው ብለው ወደ ሚያስቧቸው አገሮች ይሻገራሉ። ስደተኞች ከሀገራቸው በሚወጡበት ቅጽበት ሀገር አልባ ይሆናሉ ።ዜግነታቸው ይጎድላቸዋል ። ስለዚህ ደረጃቸው ከህጋዊ ዜጋ ወደ ጥገኝነት ጠያቂ ሆነው ስደተኞች ሀገር አልባ ይሆናሉ። በአብዛኛዎቹ ጉዳዮች ስደተኞች ሀገራቸውን ለቀው ሲወጡ፣ ሳይዘጋጁ እና እየተሳቀቁ ይሄዳሉ። ወደማያውቋቸው ሀገራት እና ማህበረሰቦች ሲደርሱ ግራ ይጋባሉ። በዚህ ምክንያት ነው አስተናጋጅ አገሮች እነዚህን በጣም አደገኛ እና ጥበቃ ያልተደረገላቸው የማህበራዊ ቡድኖችን የመቀበል፣ የማረጋጋት እና የመንከባከብ የሞራል ኃላፊነት ያለባቸው።

 

ከስደተኛ ሀገራት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮችን ለመፍታት፣ ተቀባይ አገሮች ሁለት ዋና የሰፈራ ፖሊሲዎችን ያዘጋጃሉ፡ ሰፈር እና ራስን መቻል ወይም የአካባቢ ውህደት።

የካምፕ አሰፋፈር ፖሊሲን የሚያራምዱ አስተናጋጅ አገሮች ስደተኞችን በተጨናነቁ እና በአብዛኛው አገልግሎት በማይሰጡ አካባቢዎች ውስጥ ያከማቻሉ።ከማኅበረሰቦች መነጠልና የመንቀሳቀስ፣ የነጻነት፣ የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን እንዲሁም ትርጉም ያለው መተዳደሪያ መብቶችን ይሰጣሉ። ስደተኞችን የመስራት፣ የመማር እና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን የማግኘት መብት መግፈፍ ሰብአዊነት የጎደለው ተግባር ነው።ይህ አይነቱ ሁኔታ በአብዛኛው ሀገር አይተገበርም።ሌላው ቀርቶ ስደተኞች በቂ እርዳታ የማይሰጡ የመኖሪያ ጊዛዊ ወረቀት ሰጥተው ከፈለክ ኑሮ ካልፈለክ ወደ ሀገር ተመለስ የሚሉ እንደ ፊሊፔንስ ያሉ ሀገራቶችም አሉ።

 

በተለይም ሀገራቶች የሪፊውጅ ሪኮግኔሽን የፈረመች ሀገር ስለሆነች በአብዛኛው ስደተኞችን ሲበድሉ ነው የሚታየው ።አብዛኛው ስደተኞች በቂ መጠለያና በቂ ምግብ በሀገሪቱ ውስጥ አያገኙም። በርካታ ውጭ ሀገር ዘመድና ጠያቂ ወገን የሌላቸው ስደተኞች የቋጠሩትን ገንዘብ ጨርሰው ቤተሰቦቻቸውን ይዘው ለጎዳና የተዳረጉ ሞልተዋል።

ሌላው ቀርቶ በየአገሩ የሚገኙ የዓለም አቀፍ የስደተኞች ማህበር (ዩ ኤን ኤች ሲ አር) ስደተኞችን ከመርዳት ይልቅ ከሀገራቶቹ ጋር ወግነው የዓለም አቀፍ የሪፍውጅ ሪኮግኔሽን ሀገሪቱ ስለፈረመ እኛ አያገባንም የሚሉም እንደ ፊሊፔንስ ያለ ሀገርም በየቦታው ሞልቷል።ችግር ካጋጠማችሁ ከእኔ ጋር አብሮ የሚሰራውን ፓርትነሬን አናግሩ ይላሉ።ፓርትነር ሆኖ የሚሰራው ደግሞ ስደተኛውን ለአንድ ጊዜ የአንድ ወር የቤት ኪራይ የማይሸፍን ገንዘብ ስጥቶ መርዳት አልችልም ይላል።እንደነዚህ አይነቶቹ ከመርዳት ይልቅ በሙስና የተጨማለቁ ስለሆነ የራሳቸውን ሥራ አጥ ዜጋ ከመርዳት አልፎ በስደተኛው የመጣውን ገንዘብ የራሳቸውን ሰዎች ሥራ ማሲያዣና ኪሳቸውን ማደለብ እንደ አማራጭ አድርገው ይይዙታል ።በዚህ በፊሊፔንስ የሚገኙ ስደተኞች ለዓለም አቀፍ ስደተኞች ማህበር (ዩ ኤን ኤች ሲ አር ) እንዲሁም ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተደጋጋሚ ኢሜሎች ከስደተኞች ቢላክም ለሚላኩት ኢሜሎች ጆሮ ዳባ ልበስን መባላቸውን በርካታ ስደተኞች አጫውተውኛል ።በዚህ ሀገር የሚገኙ በርካታ ስደተኞች በቂ የህክምና አገልግሎት አያገኙም ።በቂ መጠሊያና በቂ ምግብም የላቸውም።የፊሊፔንስ መንግሥት በሶስት ወር አንዴ የአንድ ወር የቤት ኪራይ የማይሸፍን ገንዘብ ይሰጣቸዋል።ይህ ትንሽ ነው ? ለምንስ በሶስት ወር አንዴ ይሰጣል ? ሲባሉ።«ድሀ ሀገር ስለሆንን ነው !» የሚል አጥጋቢ ምላሽ  ይሰጣቸዋል።እንዲያውም ከኦሺኒያ ሀገራቶች እንደ ፊሊፔንስ ካሉ ሀገሮች  ይልቅ የአፍሪካ የስደተኞች አያያዝ የተሻለ ነው።

 

በርካታ ስደተኞች ከ14 አመት በላይ በፊሊፔንስ የቆዩ  ናቸው።ያላቸውን ገንዘብ አጠናቀው ጎዳና ቤተሰቦቻቸውን ይዘው የወጡ ስደተኞች አጋጥመውኛል ።የራሳቸውን ሥራ ጀምረው ጉቦ ባለመስጠታቸው ከሀገሩ እንዲባረሩም  የተደረጉ አሉ ።በፊሊፔንስ ያሉ ስደተኞች  ልብ በሚበላ ሁኔታ የደረሰባቸውን ሁኔታ ሲናገሩ ማዳመጥ አይደለም  ለሴት ልጅ ቀርቶ የወንድ ልጅንም አንጀት በልቶ እንባ ያስረጫል።ግን ለማን አቤት እንደሚሉ  ሁሉም  ማለት ግራ የተጋቡ ስደተኞች  ናቸው።ጊዛዊ የመኖሪያ ፍቃድ ለእነሱ ምንም አይደለም።ምግብ የለም መጠለያ የለም።አንዱ ሲያገኝ ሌላውን ማሰብ በስደተኛ ህይወት የተለመደ ቢሆንም ።አሁን ግን ይህ ሁኔታ ፊሊፔንስ ውስጥ ያውም ከ95 በመቶ በላይ ክርስቲያን በሆነበት ሀገር አይሰራም።የሚያውቁት የሀገር ሰው ወይም አፍሪካዊ ሲያዩ እንዳላዩ ሆኖ ማለፍ በሀገሪቱ የተለመደ ነው።ህዝቡም ቢሆን በአብዛኛው ድሀ ስለሆነ ለስደተኛው ምንም የሚያደርገው ነገር የለም።ምክንያቱም አንዱ ሌላውን ስደተኛ መርዳት አይችልም።ሌላው ቀርቶ በፊሊፔንስ ለውጭ ሀገር ዜጋ የቀን ሥራ መስራትም የማይታሰብ ነው።ሥራ እንኳን ቢገኝ ሥራ ከሚያሰራው አካል ለፍትህ ሚኒስቴር አስቀድሞ ደብዳቤ መጻፍ አለበት።አሰሪዎች ደግሞ ይህን ስለማይፈልጉ ማሰራትን አይሹም።ስደት አንዳንዴ እንደ ፊሊፔንስ ካሉ ሀገሮች ይላቅ አፍሪካ ውስጥ እዛው ስደት ይሻላል ያሉ ስደተኞች በርካታ ናቸው።ኢትዮጵያ የነበሩ የጋናና የናይጄሪያ እንዲሁም የካሜሮን ስደተኞች ይህን የነገሩኝ ናቸው ።እነዚህ ስደተኞች ለእነሱ ከፊሊፔንስ ይልቅ ኢትዮጵያ የተሻለች ነበረች።ምክንያቱም ኢትዮጵያ ስደተኛ ሆነው አይተውታል።ለምን ወደዚህ ሀገር መጣው ያሉኝም አሉ። በፊሊፔንስ ብዙ ስደተኞች ባይኖሩም በሀገሪቱ ውስጥ ያለው የስደተኞች አያያዝ በጦርነት ከምትታመሰው ሱማሌ፣ሊቢያና የመን የተሻለ እንዳልሆነ አብዛኛዎቹ ይስማሙበታል። ባይገርማችሁ በጊዛዊ የሰደተኞች መጠሊያ ውስጥ ያለው አንድ አፍሪዊት ሴት እስከ ነልጇ ብቻ  ስትሆን ቀሪው የፊሊፔንስ ዜጋ ነው።ጊዛዊ የስደተኞች መጠለያ ከመግባት ይልቅ መንግስተ ሰማየት መግባት ይቀላል።ለምን ቢሉ የሜዲካል ሰርተፍኬት ያስፈልጋል።ትንሽ ህመም ካለቦታ በጭራሽ መግባት አይቻልም።ይህም ለይስሙላ ነው ።ምክንያቱም መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ያሉት ፊሊፔንሶች ናቸው።በዚህ የተነሳ በርካታ ስደተኞች በነዚህ የኦሺኒያ ሀገሮች አይኖሩም።ሌላው ቀርቶ በፊሊፔንስ ተቀባይነት ያገኙ ስደተኞች ሳይቀሩ እንደነዚህ ጨካኝ ከሆነ ሀገር ከመኖር ይልቅ በየወሩ ለኑሮ ተብሎ ከሚሰጣቸው አነስተኛ ገንዘብ አጠራቅመው ወይም ዘመድ አስቸግረው አሊያም ስጋቸውን ሸጠው ወደ ሌላ ሀገር መሻገርን ይመርጣሉ።እናም ከፊሊፔንስ ይልቅ  ኢትዮጵያ፣ኡጋንዳና ደቡብ አፍሪካ የተሻሉ ናቸው። ለመሆኑ  ፊሊፔንስ ከኢትዮጵያ  የስደተኞች አያያዝ ምን መማር ይገባታል።

በእርግጥ ሌሎች የስደተኛ አገሮች የበለጠ ሰብአዊነት ያለው እና ተራማጅ የሆነ ራስን በራስ የማቋቋም ወይም የአካባቢ ውህደት ፖሊሲን ስለሚቀበሉ ለስድተኛ አመቺ የሆኑ ሀገሮች መኖራቸውን አልዘነጋውም። ስደተኞች ነፃ የመንቀሳቀስ፣ የትም ቦታ የመስፈር፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች የማግኘት፣ መተዳደሪያ የማግኘት እና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በማህበራዊ ትስስር የመፍጠር መብት አላቸው።ይህ ግን በፊሊፔንስ የለም።

 

በአፍሪካ ውስጥ ያሉ ብዙ ሀገራት የስደተኞች ሰፈራ ፖሊሲን ይቀበላሉ ።ይህም በመንግስት እና መንግስታዊ ባልሆኑ የሰብአዊ እርዳታ ተዋናዮች ላይ ከመጠን በላይ ጥገኛ ያደርጋቸዋል ።በተለይም ዕለት ተዕለት ኑሮአቸው ስደተኞች ዝቅተኛ ግምት እንዲኖራቸውና ከፍተኛ ጭንቀት እና ድብርት እንዲሰማቸው ያደርጋል። አንዳንድ ጊዜ ብዙ ስደተኞች ከእንደዚህ አይነት ካምፖች አምልጠው በድብቅ ወደ ዋና ከተሞች ሄደው ይሰፍራሉ ።በካምፑ አካባቢ የኑሮ ውጣ ውረዶችን ስለማያዩ በከተሞች ይኖራሉ። ጥብቅ የካምፕ ፖሊሲን የሚከተሉ የአፍሪካ ሀገራት ታንዛኒያ፣ ዛምቢያ፣ ማላዊ እና ኬንያ ሲሆኑ ስደተኞች በነፃነት እራሳቸውን እንዲሰፍሩ በአካባቢው እንዲቀላቀሉ የሚፈቅዱት ደቡብ አፍሪካ፣ ኡጋንዳ እና ኢትዮጵያ ይገኙበታል።

እ.ኤ.አ ጥር 2019 ኢትዮጵያ ስደተኞችን በሀገሪቱ ውስጥ በማንኛውም ቦታ ሰርተው መተዳደሪያቸውን እንዲያገኙ የሚያስችል አዲስ ህግ አውጥታለች። በተጨማሪም በማንኛውም የትምህርት ተቋም መማር፣ የፋይናንስ አገልግሎት ማግኘት እና ልደትና ጋብቻ መመዝገብ ይችላሉ።

እንዲህ ዓይነት ድንጋጌዎች በኢትዮጵያ ብቻ አይደለም ያለው።እንደ ደቡብ አፍሪካ እና ኡጋንዳ ያሉ ሌሎች ሀገራትም ለስደተኞች እንደዚህ አይነት መብቶችን ይሰጣሉ ።

ነገር ግን የኢትዮጵያን ጉዳይ በአፍሪካ ልዩ የሚያደርገው ተራማጅ የስደተኞች አቀባበልና አሰፋፈር ፖሊሲው በተጨማሪ የሕዝብ ጥላቻ አዘል አስተሳሰብና ጥቃት ከሞላ ጎደል ጨርሶ አለመኖሩ ነው። ብዙ ኢትዮጵያውያንን ስለስደተኞች በሀገሪቱ ውስጥ መኖር አነጋግሬስለው አንድም ኢትዮጵያዊ ፀረ ስደተኛ ስሜት ያለው አጋጥሞኝ አያውቅም።ፊሊፔንስ ሲመጡ ህፃን ልጅ ሳይቀር ጥቁር ባዩ ቁጥር ኔግሮ ማለት ይቀናቸዋል።ይህ ብቻ አይደለም ህቃ መግዛት ሲፈልጉ ለውጭ ተወላጅ  ፊሊፔንሳውያን ከሚገዙት ዋጋ ይጨምራል።

በርካታ የምርምር ጥናቶች እንዳረጋገጡት የህዝብ ተወካዮች የስደተኛ ጉዳዮችን እንዴት እንደሚቀርጹ ዜጎች ለስደተኞች ባላቸው ህዝባዊ አመለካከት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ። የኢትዮጵያ ህዝብ እና የፖለቲካ ሰዎች ስደተኞችን በአገራቸው ላሉ ችግሮች ተጠያቂ አይሆኑም ይህም በብዙ የአለም ሀገራት ዘንድ የተለመደ ነው። ይህ በሀገሪቱ ያለውን የአመራር ጥበብ እና የሞራል ኃላፊነት እንዲሁም የኢትዮጵያን ማህበረሰብ እንግዳ ተቀባይነት፣ መቻቻል፣ አብሮ መኖር እና መንፈሳዊነት ባህልና ወግ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ተራማጅ የስደተኞች አሰፋፈር ፖሊሲ ከፖለቲካዊ እና ማህበረሰባዊ መቻቻል እና ከስደተኞች ጋር አብሮ የመኖር መንፈስ ተዳምሮ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ መሆን አለበት። ምንም እንኳን ሀገራዊ የሀብት ውስንነቶች እና እጥረት ቢኖርም ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ስደተኞች አሁንም በሰላም መኖር እና ከተቀባይ ማህበረሰቦች ጋር መተዳደር ይችላሉ።

 

አፍሪካውያን ስደተኞችን ወደ ገለልተኛ ካምፖች መልቀቅ የፓን አፍሪካኒዝም መንፈስን እና የአፍሪካን አብሮ የመኖር እና የመቻቻል ባህልን ይፃረራል። እንደ ደቡብ አፍሪካ ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ባሉ የህዝብ ተወካዮች በተጋለጡ ስደተኞች ላይ የሚሰነዘሩ አሰቃቂ ትረካዎች የህዝብን የውጭ ጥላቻ አስተሳሰብ እና አለመቻቻል ያባብሳሉ። ተራማጅ የስደተኞች ፖሊሲዎች መኖር በቂ አይደለም; ይልቁንም ስለ አፍሪካውያን ስደተኞች አወንታዊ እና ታጋሽ ትረካዎች ጋር መስማማት አለባቸው።

አበቃው ክብረት ይስጥልኝ።