ፌደራሊዝም ምንድን ነው? ለምንድነው ኢትዮጵያ ይህንን ርዕዮት ዓለም የምትጠቀመው? ለምንስ ፍፁም ልትሆን አልቻለችም?


ከወሰንሰገድ  መርሻ (ከጮራ ዘአራዳ)

በሀገራችን ውስጥ ያለው የፖለቲካ ሁኔታ ከማሳዘን አልፎ ወደ ባሰ እረመጥ ውስጥ ሀገራችን እየገባች መሆኑ ሁላችንንም የሚያሳዝነን ነው።
ሀገራችን የምታካሂደው ርዕዮት ዓለም ፌደራሊዝም ምንድን ነው? 
ለምንድንስ  ነው  ኢትዮጵያችን  ይህንን ርዕዮት ዓለም የምትጠቀመው? ለምንስ በዚህ ርዕዮት ዓለም ፍፁም ልትሆን አልቻለችም?  በዚህ ዙሪያ በዛሬው መጣጥፌ አንድ ለማለት ወደድኩ።።እንደምን ከረማችሁልኝ ውድ አንባቢያኖቼ።

ለመሆኑ  ፌደራሊዝም ምንድን ነው ? ፌደራሊዝም ሥልጣን በማዕከላዊ ባለሥልጣንና በትናንሽ የክልል መንግሥታት መካከል የሚከፋፈልበት የመንግሥት ሥርዓት ነው።

ብዙ አገሮች በድንበራቸው ውስጥ ያለውን የብሔረሰቦች ልዩነት ለመቆጣጠር እና አንድነትን ለማጎልበት ፌዴራሊዝምን ይቀበላሉ። በአለም አቀፍ ደረጃ 25  በመቶ የሆነው የፌደራል ሀገራት ያሉ ሶሆን  40% የሚሆነውን  የአለም ህዝብ ይህ ርዕዮት ዓለም ተከታዮችን እንደሚወክል የጥናቱ አቅራቢዎች ይናገራሉ።

ፌዴራሊዝም ክልሎች  ቢሆኑም የዋናው  ሀገራቸው አካል ሆነው አንዳንድ ጉዳዮቻቸውን - ለምሳሌ ትምህርትን ወይም የስራ ቋንቋን በሚመለከቱ ውሳኔዎች እንዲመሩ ያስችላቸዋል።

ኢትዮጵያችን  ፌዴራሊዝምን የተቀበለችው በወያኔ ጊዜ በ1991 የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) - የአራት ትላልቅ ፓርቲዎች ጥምረት - ስልጣን በያዘ ጊዜ ነው። ይህም ከ1974 እስከ 1991 ሀገሪቱን ሲመራ የነበረውን የኮሚኒስት ወታደራዊ መንግስት ደርግን ከስልጣን ለማውረድ ለ17 አመታት የዘለቀው ህዝባዊ አመጽ ማብቃቱ ከተበሰረ በኋላ ነው።

በእኔ እይታ ፌደራሊዝም ለኢትዮጵያ የተሻለው አካሄድ ሆኖ ቀጥሏል። ወይስ  አልቀጠለም ብሎ ለመናገር ቢከብድም። የባህል እና የቋንቋ ነፃነቶችን መፍቀዱ። በክልል ደረጃ ራስን በራስ ማስተዳደር  ማስቻሉ፣ ለኢኮኖሚ ዕድገትም አስተዋጽኦ  ሊያደርግ ይችላል የሚል እምነት አለኝ። ይሁንና ስርዓቱ ግን በርካቶች ድክመቶቹ  ያሉበት በመሆኑ  በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ያመጣው ለውጥ አይታየኝም ።እንዲያውም  የዲሞክራሲ ምህዳሩ መጨመር  እንጂ ብዙ  ድክመቶችን  ይዞ እየተጓዘ ነው የሚገኘው።

የኢትዮጵያ ፌደራሊዝም እንዴት እየተተገበረ ነው 

የኢትዮጵያ የፌዴራሊዝም አካሄድ ከሌሎች ከፍተኛ ልዩነት ካላቸው የአፍሪካ ፌዴራሊዝም መንግስታት ጋር ሲወዳደር  እንደሚታየው  አካሄዱ  ደፋር  ቢሆንም  ርዕዮት ዓለሙን እያካሄዱ ካሉ ሀገሮች አተገባበሩና አፈፃፀሙ ሱታይ የማይሻል ነው።በእርግጥ ከሌሎች አንዳንድ ሀገሮች የተሻለ ሁኔታዎች እናያለን።ለምሳሌ ናይጄሪያ ለብሔር ብሔረሰቦች ሕገ መንግሥታዊ እውቅና  የሰጠች ሀገር ነች። ይሁንና በአተገባበር ሲታይ ግን  ከኢትዮጵያ አትሻልም ፤፤ በ1995 እ.ኤ.አ የፀደቀው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 39ን የተመለከትን እንደሆነ የአገሪቱን የብሔረሰቦች ብዝሃነት በግልፅ ያረጋግጣል  ማለት ይቻላል።

ኢትዮጵያ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 8 ላይ እንደተገለጸው ብሄር ብሄረሰቦችን ያቀፈ ፌዴሬሽን እንደሆነች ይገልጻል ። የግዛት ክልል ያላቸው ብሔር ብሔረሰቦች የየራሳቸውን ክልል የመመሥረት አልፎ ተርፎም ነፃነትን የመሻት መብት አላቸው።

በሀገሪቱ ውስጥ 12 ክልሎች አሉ, እያንዳንዳቸው ሰፊ ስልጣን አላቸው. ይህ ስልጣን ደግሞ  የራሳቸውን  ፖሊሲ የማውጣት፣ ሕገ መንግሥት ማውጣት፣ የሥራ ቋንቋ መምረጥ፣ የክልል ፖሊስና ሲቪል ሰርቪስን መጠበቅን ይጨምራል።

ነገር ግን የእነዚህ ስልጣኖች አጠቃቀም  ሀገሪቱን በሚመራው  በዶክተር ዐብይ የብልፅግና ፓርቲ ስርዓት የበላይነት  እንዲገደብ  ተደርጓል።

ከ1991 እስከ 2019  እ.ኤ.አ ባለው ጊዜ ውስጥ ኢህአዴግ የክልል መንግስታትን ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግበት አድርጓል። ራስን በራስ የማስተዳደር ማንኛውንም ጥያቄ  እንዲታፈን ተደርጓል። በ2018 እ..ኤ.አ  ወያኔ  ያሳደጋቸው የአሁኑ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የአብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣት የፖለቲካ ምህዳሩን  ከበፊቱ  በተሻለ መልኩ ከፍ እንዲል አድርጎታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የብልጽግና ፓርቲን ያቋቋሙት ወያኔን በትሪ ዘርግተው ኢህአዴግን ከመሰረቱት ሦስቱን ፓርቲዎች እና ትናንሽ አጋር ድርጅቶችን  እንደገና በማዋሃድ ነው። ነገር ግን ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ  የዐብይን  ፓርቲ  ለመዋሃድ ፈቃደኛ አልሆነም።

ዶክተርብአብይ ከተለያዩ ብሄረሰቦች ለቀረበላቸው የክልልነት ጥያቄ አንዳንድ ጥያቄዎችን አስተናግደዋል። ከ2019 - 2023  እ.ኤ.አ ሀገሪቱን እየመሩ ባለበት ወቅት ሶስት ተጨማሪ ክልሎችን እንዲፈጠር  አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም አሠራር  ግን በፓርቲ ሥርዓቱ ላይ  ማለትም በብልፅግና  ፓርቲ ላይ የተመሰረተ ነው። የብልፅግና  ፓርቲ  የፓርቲዎችን  ደንቦች ብዙውን ጊዜ ሕገ መንግሥታዊ መርሆችን አልፎና  ተሻግሮ በእራሱ አካሄድ  የግድ ተቀብለው እንዲተገብሩ  ያደርጋል። ይህ ደግሞ  እንደሚታየው የውስጥ ፓርቲ  ሽኩቻና ቀውሶች ወደ መንግስት አለመረጋጋት እና ግጭት እንዲያመራ እያደረገ  ነው።

ከ2020  -2022  እ.ኤ.አ  ባለው  ጊዜያት የትግራይ ጦርነት  ለዚህ  ጥሩ ማሳያ ምሳሌ ነው። በህዝባዊ ወያኔ  ሓርነት ትግራይና በፌደራል መንግስት መካከል ካለው አለመግባባት የመነጨ ነው የእርስ በርሱ  ጦርነት እንዲካሄድና ለበርካታ ወገኖቻችን ስድት፣እልቂትና ችግር  ሊሆን የቻለው። በሁለቱ ወገኖች አለመግባባት የተፈጠረው  በሟቹ የወያኔና የኢትዮጵያ መሪ  በአቶ መለስ ዜናው የተመሰረተው የኢህአዴግ  ፓርቲ መፍረስ ነው።

የፌድራሊዝም  ፓርቲ  ዋንኛ  ጥቅሞች

የኢትዮጵያ ፌደራሊዝም ሶስት ዋና ዋና ጥቅሞች አሉት።

በመጀመሪያ የቋንቋ እና የባህል ነፃነት እንዲኖር ያስችላል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በትንሹ  80 ብሄረሰቦች  ያሏት  ሲሆን እነዚህ  ብሄረሰቦች የባህል፣ የቋንቋ እና የማንነት መብቶቻቸውን ለማስከበር ብዙ ታግለዋል። በኢትዮጵያ ከሚገኙት 80 ቋንቋዎች ከ57 በላይ የሚሆኑት በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንደ ማስተማሪያ ዘዴዎች  በአሁኑ ወቅት እያገለገለ  ነው።ይህ ደግሞ ጠቀሜታው የጎላ ቢሆንም የትምህርት አሰጣጡ ደካማ መሆን ግን የታለመለትን ግብ መምታት አልቻለም።

በሁለተኛ፣  ደረጃ  የፌድራሊዝም  ሥርዓት ብዙ ብሔረሰቦች በብዛት በሚገኙባቸው አካባቢዎች ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ አስችሏል። ሌላው ቀርቶ አናሳ ብሔረሰቦች  ሌላው ቀርቶ  እንደ ወረዳ  ያሉ አስተዳደሮችን  ያሉ  የአካባቢ መስተዳድሮችን የማቋቋም መብት አላቸው።

በሦስተኛ ደረጃ የፌዴራል ሥርዓቱ  እንደታሰበው ባይሆንም ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገትና አንጻራዊ መረጋጋት አስተዋጽኦ አድርጓል። በተለይም በደቡብ ክልል  ያለውን ሁኔታ  መመልከቱ  በቂ ነው።በተለይም ስልጣንና ሃብትን ለክልሎችና ለአካባቢው አስተዳደር በማካለል  የተደረገው  ሁኔታን  መጥቀሱ  በቂ ነው።

ቁልፍ ተግዳሮቶች

የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም አንዱ ተቀዳሚ ፈተና ግጭቶችን ሙሉ በሙሉ መፍታት አለመቻሉ ነው።

ከእነዚህ ግጭቶች ውስጥ አንዳንዶቹ ለምሳሌ በምእራብ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በምዕራብ ትግራይ - ስርአቱ በአንድ አካባቢ አንድን ብሄረሰብ ለማንበርከክ የሚያደርገው ጥረት በከፊል  ችግር በክልሉ ውስጥ እንዲፈጠር  አድርጓል። ይህም ስልጣን በተሰጣቸው ቡድኖች እና በሌሎች መካከል በመሐከላቸው  ልዩነት  እንዲፈጠር ከማድረግ አልፎ መለያየትን መለያየት ፈጥሯል።

የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ ከሚገኙት 4.4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮች መካከል አብዛኛዎቹ  ማለትም ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በግጭት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ናቸው።እነዚህ ስድተኞች ቤት ንብረታቸውን ጥለው መውጣታቸውን ተረጋግጧል።

ሁለተኛው ተግዳሮት በሕገ መንግሥቱና በፖለቲካዊ መብቶች አሠራር መካከል ያለው ክፍተት ነው። አንዳንድ ብሄረሰቦች በፖለቲካዊ ጭቆና ምክንያት መብታቸውን አልተጠቀሙም።

እ.ኤ.አ. በ2018  ዶክተር አብይ ስልጣን ከያዙ ወዲህ የብሄር ብሄረሰቦች የክልል  የመሆን ጥያቄ  በብዛት ጨምሯል። መንግሥት ከእነዚህ ጥያቄዎች መካከል አንዳንዶቹን ቢመልስም፣ አንዳንድ ጥያቄዎችን ለማፈን  መሞከሩ ቅሬታንና ግጭትን  በተለያዩ አካባቢዎች እንዲፈጠር አስችሏል። በእርግጥ መንግሥት ይህን ጥያቄ ለመመለስ  አንዳንድ ብሄረሰቦች  አናሳ መሆናቸው የራሳቸውን  ክልል እንዳይኖራቸው  አድርጓል ።

ሦስተኛው ፈተና የገዥው ፓርቲ የበላይነት እና የዴሞክራሲ እጦት ነው። በሀገሪቱ ውስጥ ያለው የፕሬስ ናፃነት አለመኖር፤የመናገርና ሀሳብን የመግለፅ ሁኔታ እንደታሰበው  አለመሆኑ  ጨምሮ የፓርቲዎች ደንብ ሕገ መንግሥታዊ መርሆዎችን የመናድ አዝማሚያ በፌዴራላዊ ሥርዓቱ ላይ  መታየቱ  ጥቁር ጥላ  እንዲጥል አስችሎታል።

ወደፊት

ፌደራሊዝም በቅርጽ ሊኖር ቢችልም፣ ከዴሞክራሲና ከመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ውጭ በብቃት ለመንቀሳቀስ  ገና ነው።ስለዚህ ይበልጥ አተገባበሩ ላይ መስራት ያስፈልጋል።

በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት  ውስጥ የሕግ የበላይነትና የግለሰብ መብቶች ጥበቃ  እንዲሁም የዜጎች መብት መከበርን በማረጋገጥ  በኩል ፌዴራሊዝም ጠቀሜታው  የጎላ  ነው። የመድበለ ፓርቲ ስርዓት በውሳኔ አሰጣጥ ውስጥ የተለያዩ ድምፆችን ያካትታል ።ከዚያም  አልፎ  አናሳ ብሄረሰቦችን ለመጠበቅ  ጉሉ  ሚና ይኖረዋል።. ይህን መርሆ  ኢትዮጵያ  መከተሏ ጠቀሜታ እንዳለው የፖለቲካ ሙሁራኖች ሳይገልጹ አላለፉም።ብሔር ብሔረሰቦች ባሉበት አገር ሰላምና አንድነትን ለመገንባት  ስለሚረዳ።በአሁኑ ወቅት፣በአማራና በኦሮሚያ ክልል  እንዲሁም በደቡብ  ብሔረሰቦች ያለውን አለመረጋጋት ለማስወገድ የፌድራሊዝም  ግንባታ ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን በመጠቆም መጣጥፌን በዚሁ እቋጫለው።ክብረት ይስጥልኝ።