ኢትዮጵያችን እንደ ጁሌስ ኔየሬሬ አይነት መሪ መቼ ይሆን የምታጋኘው?


 

 

ከወሰንሰገድ መርሻ (ጮራ ዘአራዳ)

 

  የእኛ  ሃገር  ፖለቲከኞች  በነፈሰበት  በኩል  የሚሄዱ ናቸው።ስልጣንና  ጉልበት ያለው  ወገን  ሲያጋሳ  አብሮ   ማጋሳት።ሲተነፍስ  አብሮ  መተንፈስ ፣ሲያስካኩ  አብሮ ማስካካት፤ የማያስቅ  ነገር  አውርቶ  ከሳቀ  እነሱም  ጣራ  እስከ ሚቀደድ  ድረስ  መሳቅ  የተለመደ  ከሆነ  እነሆ ሰነባባተን ።ለመሆኑ ኢትዮጵያችን  እንደ ጁሌስ ኔየሬሬ  አይነት መሪ መቼ  ይሆን የምታጋኘው? 

 

 በፊት  ጁንታው  ዛሬ ደግሞ ወዳጃችን የምንለው  ወያኔ የራስን እድል በራስ መወሰን የሚለውን ሁኔታ ተቀብሎ  መተግበር የጀመረው ከጆሴፍ ስታሊን ፍልስፍና  ነው  ።

 

  ጆሴፍ  ስታሊን  የሌኒንን ሚስት  ጨምሮ  ብዙዎቹን የአገሪቱን ዜጎች  ገድሏል።

አንዳንድ  የሶቭየት  ኅብረት ሙሁራኖች  እንደሚገልጹት ከ100 ሚሊዮን  በላይ  የሚጠጉ የሶቭየት ኅብረት ዜጎችን ገድሏል በማለት ይገልጻሉ።

 

 በአንፃሩ  የጆሴፍ  ስታሊን  ደጋፊዎች  ደግሞ  የሟቾች ቁጥር ከ40 ሚሊዮን  አይበልጥም  ብለው ይከራከራሉ።ሆኖም  በሕግ  ፊት አይደለም  አንድ  ሰው መግደልና ያለአግባብ  ሕግን አዛብቶ ማሰርና ማንገላታት

በእግዚአብሔር ዘንድም እንደሚያስጠይቅ  እሙን  ነው።

 

 ጆሴፍ ስታሊን ከሚታወቅበት ዋንኛው  ነገሮቹ መካከል 

ዜጎችን ተዋቂ  በሆነው  የስለላ ድርጅቱ ኤንኬቪዲ አማካይነትሰውን መግደልና

 ማሰር ብቻ አይደለም  ዋናው ተግባሩ ።አገሪቱን እረግጦ

 ለመግዛት ካለው  ፍላጎት

 

አንፃር የሕዝቡን የሰበአዊ መብቶችን በመግፈፍና ሕዝቡን ረግጦ  በመያዝ  ለበርካታ አመታት ሶቭየት ኅብረትን ለመግዛት በቅቷል።

 

 

  ይህን የስታሊን  የአገዛዝ ሥርዓት አብዛኛዎቹ የሦስተኛው  ዓለም  አቀፋዊ መሪዎች  ሕዝባቸውን እየረገጡ በፍረሐትና በእርድ  ውስጥ ከተው  እያንቀጠቀጡ 

ሕዝቡን  ጨ  ቆነውና  ገርፈው ለመግዛት  ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም።

 

 ከእነዚህ  መሪዎች  መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱትና እንደ ጣ ኦት የሚመለኩት የአልቤኒያው  መሪ ኤንቨርሖዥ  ይገኙበታል።

እኚ  መሪ ኮሚኒዝምን በአልቤኒያ እገነባለው  ብለው በርካታ የአገሪቱን ዜጎች ማለትም  ከ250 ሺህ በላይ ዜጎቻቸውን አስረው  ማሰቃየት ብቻ ሳይሆን በርካታዎችንም ገድለዋል።

 

 አገራቸው  ግን ከአውሮፓ ኋላ ቀር ከሚባሉት የመጨረሻ አገሮች ተርታ በቀዳሚነት

እንድትቀመጥ  አድርገውት ነበር።እኚህ መሪ ዛሬም በቆሻሻ ታሪካቸው  እየተዘከሩ ይገኛሉ።

 

  ወደ አገራችን ስንመጣም 

በደርግ ጊዜ በምንከተለው የሶሻሊስት አብዮት በርካታ ትውልድ ተጨፍጭፏል።እርጉዝ ሴት ሳትቀር በመንገድ ላይና ከየቤታቸው  እየተወሰዱ

እንደ በግ ሲታረድ ቆይተዋል

 

 ኢትዮጵያ የተቸገረችው    የስታሊን  ኮሚኒዝምን  በኃይል እገነባለው  ማለቱ ነው።ይሁንና  ኢትዮጵያ ውስጥ  እስካሁን ድረስ ሲስርራ አልታየም

 

 በደርግ ቦታ የተተካው

ወያኔም  የስታሊንን ፍልስፍና በመከተል ሌላው ቀርቶ የእራስን እድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል(Self determination up to secession ) የሚለውን ፍልስፍና ይዞ ቢከተልም  አላዛለቀውም።

በትምህርት ሳቃይነታቸው  የሚታወቁትና ባለቤታቸው  ወ / ሮ አዜብ « የመለስ ጭ ንቅላት አይደለም  ለቤተሰቡ  ለዓለም  

ይብቃል » ብላ  የመስከረችላቸው  አቶ  መለስ

እንኳን ለዓለም  ሊበቃ ለኢትዮጵያም  አለመብቃቱን ተመልክተናል።እንዲያውም አቶ መለስ የዘሩት ተክል ነው  ይኸው  አፍርቶ ኢትዮጵያን ቁም ስቅሏን እያሳያት የሚገኘው።ብሄር የማያውቀው የኢትዮጵያ ህዝብ የብሄርና የጎሳ አቀንቃኝ ሆኖ እርስ በርስ እየተባላ ነው የሚገኘው።

ለምን ብትሉኝ ሶቭት ኅብረትን

ብትንትኗን  ያወጣት  የዕድገት  የአንድነት  ፀር የሆነው  የእራስን  እድል በእርስ  መወሰን  እስከ መገንጠል( self determination up to secession )  የሚለውን  የስታሊን  ፅንሰ ሐሳብ  በርዕዮት  ዓለሙ  ተቀባይነት  አግኝቶ  ስለነበር  ነው።

 

 ማሰር፣መግደልና ሕዝብ ን እየጨ  ቆኑ እረግጦ  መግዛት በኮሚኒዝም  ዕርዮት ዓለም ተከታዮች  ዘንድ  ሲያዋጣ እስካሁን አላየንም። ኢትዮጵያ ውስጥም  የታየው  ይኸው  ነው ።

 

 በኢትዮጵያችን  ውስጥ

በቅርቡ  እንዳ አያነው  የሕዝቡን ቁጣ  ብቻ ሳይሆን የፓርቲዉን አመራር አካሎችን ሁሉ  አስቆጥቶ  ፓርቲውን ግልብጥ ብጡን አስወጥ

ቶታል።ሌሎቹን ደግሞ  የፍልስፍናው ን አቀንቃኞች ደግሞ  የብልፅግና ሰይፍ ብልቷቸዋል።እዚህ ላይ የቀድሞ  የወያኔ አቀንቃኞች አስተሳሰባቸውና አመለካከታቸው  ተለውጧል ወይስ  አልተለወጠም  የሚለው  ሁኔታ  ወደፊት  በሂደት  የምናየው  ይሆናል።

 

 እኔ የምናፍቀው  መሪ እንደ እምዬ ምኒልክ  መሪ እንኳን ባናገኝ እንደ ጁሌስ ኔየሬሬ  አይነት መሪ  እናፍቃለው።ለመሆኑ ኢትዮጵያችን እንደኚህ አይነት መሪ መቼ  ይሆን የምታጋኘው?  የቀድሞው  የታንዛኒያ መሪ የነበሩት ሙዋሲሙ  ጁሊየስ ኔየሬሬ  በሕዝብ  ዘንድ ተወዳጅ መሪ እንደነበሩ እንኳን ታንዛናውያን  ቀርቶ ብዙዎቻችን አፍሪካውያን የአፍሪካ ድንቅ  መሪ እንደነበሩ እንመስክርላቸ

ዋለን።

 

ኔየሬሬ  የአፍሪካን  ሶሻሊዝም  የኡጃማን ፕሮግራም  በጀመሩበት ወቅት ከሚኒስትሮቻቸውና ከሌሎች ሹማምንቶቻቸው  ጋር በመሆን 137 ኪሎ ሜትር የእግር ጉዞ አድርገው  ነበር።

 

 የጉዞው  ዋና አላማ  ደግሞ ፤

ፕሮግራማቸውንና የግንባታ ዘመቻቸውን ማስተዋወቅና

ከሕዝቡ  ጎን መቆማቸውን ለማሳየት ነበር።እናም  ይህን ያደረጉት ረዥም  የሆነውን

ብሔራዊ  ጉዞን በእግራቸው በመጓዝ  ነበር።አብረዋቸው የሚሰሩትንም  አመራራቸውን የሚተማመኑ መሪ ስለነበሩ ፤

እንደሌላው  ብፌ  እያነሱ ፤

ጁስ እየተጎነጩ  ፤ሳይሆን 

ተራ ቤት በተለይም  ማንኛውም ሕዝባቸው  የሚመገብበት ሻይ ቤት እየገቡ ከ15 ሣንቲም በማይበልጥ  ሂሣብ ፣ሻይና ፉል እየተመገቡ ነበር ሕዝቡን መስለው  ይጓዙ  የነበረው።

 የእኛ አገር መሪዎች እስካሁን እስከ ዶክተር አብይ ድረስ አንድ ቦታ ለጉብኝት፣

ለሥራ፣ለሌላም  ነገር ሲጓዙ መንገዶች  እንዳለ  ጥርብ ጥርብ  በሆኑ በታመኝ ወታደሮቻቸው  ይዘጉና ጥይት በማይበሳው  መኪናዎቻቸው ውስጥ  ሆነው  እየተንፈላሰሱ በየትኛው  መኪና ውስጥ እንደሆኑ  እንኳን ማለፋቸውን ሳናውቅ ፤መንገድ ተዘግቶብን ብዙ ከተጉላላን በኋላ ነው  ወደ ም ንሄድበት መንገድ  እያጣደፉ  ቶሎ  ነው 

የሚያሻግሩን ።

 

  የአሁኑ መሪያችን  የኢትዮጵያ ህዝብ ብዙ  ጠብቋቸው  ነበር ።

 

 

  እርግጥ  ያልጠራ ጉሽ ጠላ ውስጥ  ነው የተዘፈቁት።ይህን ማጥራቱ  ደግሞ  ጊዜ  ሊወስድባቸው  ይችል ይሆን ? በትግራይና በአጎራባች  ክልሎች  የሰላም እጦት አሁን መፍትሄ  ተገኘ ሲባል በኦሮሚያ ክልል ሌላ ግጭት ፈነዳባቸው፣የምዕራባውያን ተፅእኖ ፣የአባይና የሱዳን የድንበር ጉዳይ እያለን ብዙ የጋጠሟቸውን ችግሮቻቸውን እንዳጋጠማቸው  ልናነሳ እንችላለን።ምናልባት ጉሽ ጠላውን ከዚሁ  ከመዲናችን ጀመረው  ያጠሩታል ብሎ  የኢትዮጵያ ህዝብ  ተስፋ  ሰንቀናል። 

 

 ይህን የተበላሸ ቤትን ንዶ አዲስ ቤት ለመገንባት ደግሞ ጊዜ  በደንብ   ያስፈልጋቸዋል።ዶክተር አብይና አቶ ለማን ጨምሮ ጥቂት ግለሰቦች  ነው  ማንም  ኃይል ሊንደው  የማይችለውን የወያኔን መዋቅርን ነው   እንዲናድ  ማድረጋቸው፤

ለኢትዮጵያ ሕዝብ  በቂው  ነው።ለዚህ ነው  የኢትዮጵያ ሕዝብ  ለመሪው  ለዶክተር ዐብይ  የፈለገ ስህተት ቢኖርባችርው  እንኳን ሁሉንም  ነገር  ለማስተካከል ጊዜ ያስፈልጋቸዋል 

እያለ  እሳቸውን ተስፋ ሰንቆ የሚገኘው።

 

 በእርግጥ  አንዳንዶቻችን የምንሰጠው  አስተያየት ወይም  ፍርድ ሚዛን ያልደፋ ከብሔርተኝነት ጋር የተቆራኘ በመሆኑእንደ ጎባጣ  ፍርድ-

(Injustice አድርጌ ነው የምመለከተው።ልክ ባልጠራ ጉሽ 

ጠላ ላይ ሌላ ድፍድፍ  እንደ ማላስ ይቆጠራል

 

 የሀገራችን ፖለቲከኞች መሥራት ሲያቅታቸው  የስም ማጥፋት Defamations በተዘዋዋሪ የተወሰኑ ውጭ  ያሉ  ሰዎችን ይዘው  ሲጫወቱም  እየተመለከ

ትን ነው።በእኔ  በኩል አህያውን ለማሞገስ በቅሎዎችን ለማኳሰስ የሚሯሯጡ  አድርጌ  ነው  የተመለከትኳቸው 

 

 መሪዎቻችን ብቻ ሳይሆኑ ፖለቲከኞቻችን ጭምር ሰበአዊነት ያለው  አገር መገንባት፣ሕዝቡን በዚህ መልኩ መምራትና ዲሞክራሲ  ያለውን መንግሥትን መስርቶ ሕዝቡ እንዲያየውና እንዲያጣጥመው

አድርጎ ማየትና ማወራት ለየቅል መሆኑን በተግባር ሊያሳዩን እንደሚገባ ግን ማወቅና መገንዘብ ያስፈልጋል።Now you see me,now you don't  ወደ አማርኛችን ስንመልሰው ጥሬ ትርጉሙ  ''አሁን ታየኛለህ ፤አሁን አታየኝም '' እንደሚባለው  አይነት ግን ፖለቲከኞቻችን እየተለዋወጡ  እንደ እስስት መኖር  ግን  ተገቢ  ነው  የሚል  እምነት  የለኝም 

 

 ማንም ባ ለስልጣን ገና ስልጣን ላይ ሲወጡ  የነበረው ሁኔታና  እያደረ እየተኮፈሰ ከሥራ ይልቅ  መቅድድ ሲጀመር የጠራው  ውኃ እየደፈረሰ እንደሚሄደው  አይነት ውኃ እየሆኑ  ሲሄዱ ነው  የሚስተዋለው።

 

 በጉልበትና ሬሳ በመረማመድ ስልጣን ላይ የወጡ  ወገኖች የባላንጣዎቻቸውን ብቻ አይደለም  የወዳጆቻቸውንም ሕይወት ያለአግባብ  እንዲሰዋ ሲያደርጉ በቅርቡ

ተመልክተናል።

 

 የዘረፉትን ገንዘብ  አርፈው ቁጭ  ብለው  መብላት ሲችሉ ለሥልጣን ሲሉ ህዝባቸውንና ወገኖቻቸውን ለሞት፣ለስደትና ለረሀብ  እንዲሁም ለችግር ከመድስረግ  አልፈው  የራሳቸውንም  ውድ ሕይወታቸውን ያላስፈላጊ ቦታ ላይ መክፈላቸው የሚያሳዝን ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም  ትምህርት ሰጥቶ ያለፈ ነው  የሚል እምነት አለኝ።

 

 ለወደፊቱ ይህ አይነቱ ሁኔታ እንዳይደገም  ምን እናድርግ የሚለው  አንኳር ጥያቄ የሁላችንም  ይመስለኛል።

 

ብዙዎቻችን ሽንፈትን አሜን ብሎ መቀበል አለመፈለግ  አንዱ  መልስ ሲሆን ሌላው  ሰላማዊ  ሽግግር ልክ እንደ ቀድሞ  ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም  በሰላም  ደም  ሳይፈሰስ ማስረከብ  ሌላው  መልስ ሊሆን ይችላል። 

 

የቀድሞው የአሜሪካው  ፕሬዝዳንት ትራምፕ በጆን ባይደን ሽንፈትን ሲቀምሱ ከኃላፊነታቸው  እንዲህ መነሳታቸው  ላይቀር

ሰላማዊ  ሽግግር ከማድረግ ይልቅ በሕዝብና በሕዝብ መካከል ግጭት እንዲፈጠር ማድረጋቸው  አይዘነጋም።

በዚህም  የመወሰኛው  ምክር ቤት ያለመከሰስ መብታቸውን ገፎ ክስ እንዲመሰረትባቸውና አንድ አመት እንዲፈረድባቸው  ማድረጉ ይታወሳል።

 

 የእኛ አገር የቀድሞ ባለስልጣኖች ሰው  የማይኖርበት ዋሻ ውስጥ ገብተው  ግማሾቹ እጅ ሲሰጡ በረሀብ  ደክመው  ጣረሞት መስለው  ሲወጡ፤ከፊሎቹ ደግሞ ቀባሪ አጥተው  የውሻ ሞት ሞተው  ስንመለከት እንደ ሰውኛ ስንመለከተው  በጣም ያሳዝናል።

 

በሌላ በኩል የእኛ ሃገር ጦርነት አለቀ ሲባል ተጀመረ ይመስላል ፤ ወያኔ አለቀለት ብለን ስንጠብቅ  እንደገና አንሰራርቶ ሌላ ጦርነት ሲከፍት ቆይቶ የእነሱ ጉዳይ ወደ  ሰላም  ሲመጣ  የኦሮሚያ ክልል ደግሞ  በእርስ በርስ ጦርነት እንድትታመስ በሚፈልጉ ወገኖች  እንደገና  ጦርነት  መከፈቱ የሚገርም ነው።

 

በዚህ በኩል ደርግ ኢሠፓዎች ከአሁኑ ፖለቲከኞቻችን በጭ ንቅላት የተሻሉ ነበሩ ማለት  ይቻላል።ሌላው ቀርቶ ብርሃኑ ባየና አዲስ ተድላ 30 አመት በጣሊያን ኢምባሲ ውስጥ የቁም  እስራኛ ሆነው  ቆይተው  ነው 

በሰላም  ወጥተው  ከቤተሰቦቻቸው  ጋር ለመቀላቀል የበቁት 

 

ከፊሎችም  ቢሆኑ እጃቸውን ለወያኔ በሰላም  ሰጥተው የተፈረደባቸውን እሥር ጨ ርሰው ከ ቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል።የወያኔ ባለስልጣኖች ግን...አሟሟታቸው እራሱ በጣም  ያሳዝናል።

 

 በዚች አገር ላይ በርካታ ፍትህ ያዛቡ  ወገኖች  ሞልተዋል።

ላለፉት 100 አመታት በወንጀል ተጠያቂ ናቸው  እየተባለ ጠዋትና ማታ ስማቸው  እየተነሳ የሚጠቀሱ ለአገሪቱ መልካም  የሰሩም  ያልሰሩም 

ወገኖች አሉ። 

 

 ዚምቧቤ  ያሉት ኮሎኔል መንግሥቱ ብቻ ሳይሆን አጤ ምኒልክና ራስ ጎበናም በሕይወት ቢኖሩ ኖሮ በማዕከላዊ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት ለፍርድ ካላቀረብናቸው  የሚሉ ወገኖች አይጠፉም  የሚል እምነት አለኝ።

 

  ይህንን ያለ ምክንያት አላልኩም  ሐውልት እናፈርሳለን ብለው  የመጡ ወገኖች ለፍርድ ይቅረቡ ብለው ሆ  ብለው  መነሳታቸው እንደማይቀር ማሰብ  አያቅተንም  ለማለት ነው።

 

በእኔ እምነት እነዚህ ሰዎች ይህን ለማድረግ ተሰባስበው በዛን ወቅት የመጡት ፖለቲከኞቻችን በስማ  

በለው የሚያካሂዱት የፖለቲካ ርዕዮት ዓለምና የሚያወሩት ተረት ተረት ታሪክ ግንዛቤ  ወስደው ነው  እንጂ  ስለ አጤ  ምኒልክም  ሆነ ስለራስ ጎበና በቂ  እውቀት ኖሯቸው  ነበር  ብሎ ለመቀበል ይከብዳል።

 

 

ምክንያቱም  እኔ እንደሚገባኝ ባለፈው  ታሪካችን እንዳንኮራ ፤ነገን አሻግረን እንዳንመለከት  የሚፈልጉ ወገኖች  በየሚዲያውና በማህበራዊ  መገናኛ ብዙሐን ላይ የሚ ኑዙት መርዝ  ምን ያህል አደገኛ እንደነበር በእነዚህ ጥቂት አመታት የተመለከትነው  ሁኔታ በቂ ይመስለኛል።

 

በቆንጨራና በቀስት እንደ ጥንታዊ  የጋርዮሽ  ሥርዓተ ማህበር እየተፋለምን መጨራረስ በአሁኑ ወቅት ማብቃት ይኖርበታል።ለዚህ ደግሞ መንግሥታችን የአገሪቱን ሰላም በማስፈኑ በኩል ቁልፉ ሚና ያለው  በእሱ እጅ መሆኑን መዘንጋት የለበትም።በሌላ በኩል በአጠቃላይ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ፖለቲከኞቻችን 

እንዲሁም  አክቲቪስት ነን ባዮች  ፖለቲካኞቻችን ዝም ብለው መቅደዳቸውንና  መቦተለካቸውን  ማቆም አለባቸው  የሚል እምነት አለኝ።

 

ፖለቲከኞቻችን  ማውራተን

ብቻ ሳይሆን መተግበርን በማስየት አገራችን ወደ እድገት ማማ  ከፍ ብላ እንድትወጣ  የበኩላቸውን ማድረግ  እንደሚኖርባቸው ለማሳሰብ  እወዳለው።

 

የልባችሁን ፍላጎትና መሻት ተከተሉ (follow your heart)

እንደሚባለው  መሆን ግን አይኖርበትም።የራስን ስልጣን ወይንም  ጥቅም  ለማሳካት ብቻ ሲባል በአገሪቱ ውስጥ  ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ሁኔታ ለእኔ ምንም  ስሜት አይሰጥም it doesn't make any sense የሚሉ ወገኖች ካሉ መሳሳት ብቻ ሳይሆን ከታሪክ ተወቃሽነት የሚ ያመልጡበት መንገድ አይታየኝም።ስለሆነም  የታሪካ ተወቃሽ ከመሆንና መስሎ ከመኖር ፖለቲከኞቻችን  እራሳቸውን ሊጠብቁ ይገባል እላለው   ።ዶክተር ዐብይ እንደ እምዬ ምኒልክ ባይሆኑልንም  ሌላው  ቢቀር እንደ ጁሌስ ኔየሬሬ  አይነት መሪ  ለመሆን ይጣሩልን ።

አበቃው !  ክብረት ይስጥልኝ!