ወደ ጃፓን በሥራ አማካይነት በደላላ የሚገቡ የውጭ ዜጋ ሰራተኞች በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛሉ


 

 

ከወሰንሰገድ መርሻ (ጮራ ዘአራዳ)


 

 የNHK  የዓለም  አቀፍ ተንታኝ  የሆነችው  ኦኖ ሞሞ

ወደ ጃፓን በደላላ አማካይነት ለሥራ ተብለው  የሚገቡ  የውጭ ሀገር ዜጎች ከፍተኛ ችግር ውስጥ  እየገቡ እንደሆነ እንደሚከተለው  ዘግባዋለች። 

 በጃይካ ወይም በግል ደላሎች አማካይነት በተለያየ ሙያ ወደ ጃፓን የሚገቡ የቴክኒክ ሰልጣኞች በአብዛኛው  ማለት ይቻላል።የውጭ ዜጎች ላይ ከባድ የሥራ ሁኔታዎች ያጋጥሟቸዋል።  በአሁኑ ጊዜ ከ328,000 በላይ የሚጠጉ ሰልጣኞች ወደ ትውልድ አገራቸው ከመመለሳቸው በፊት በግንባታ፣ በግብርና ወይም በሌሎች መስኮች ላይ ልዩ ሙያዊ ስልጠንስ እንዲያገኙ ይደረጋል።  በአንዳንድ ሁኔታዎች እነዚህ ሰልጣኞች ከስራ ቦታቸው  ውጪ ከሰዎች ጋር መገናኘት ወይም ሌላ ሰው ጃፓን ውስጥ ማግባት አይፈቀድላቸውም።

 ማግባት  የተከለከለችው  ወጣት

የሠላሳ ዓመቷ ሳሜያን ኬኦ ከካምቦዲያ የመጣች የቴክኒክ ሰልጣኝ ነች።  ከሁለት አመት በፊት ወደ ጃፓን የመጣችው የልብስ ስፌት ቴክኒኮችን ለመማር ነው።  ኬኦ በጃፓን ካገኘችው ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነት ውስጥ  ትገባለች ።  ለአሰሪዋ የትዳር አጋሯን ማግባት እንደምትፈልግ ስትነግራት ያልጠበቀችው  ምላሽ አገኘች። እንዲህ የሚል "የኩባንያው ፕሬዝደንት እንዳገባ እንዳልተፈቀደ ነግረውኝ ነበር። ኩባንያው ከእንግዲህ ሊቀጥሩኝ እንደማይችሉና ወደ ካምቦዲያ መመለስ እንዳለብኝ ተነግሮኛል።" ትላለች።

 

በጃፓን ህግ መሰረት ሰልጣኞች ትዳር መመስራት ጃፓን ውስጥ አይችሉም ።ምንም ይሁን ምን ስልጠናቸውን አጠናቀው ወደ ሀገራቸው መመለስ አለባቸው።በእርግጥ ያላቸው ልምዳቸውን ማዳበር ጃፓን ውስጥ ቆይጠው መቀጠል ይችላሉ ።በዚህም የተነሳ ኬኦን ኩባንያው  አሰናብቷታል።

ኪኦ (Keo)  በኩባንያዋ ላይ ያጋጠማት ችግር የጋብቻ መፈፀም  ብቻ አልነበረም።  የመኝታ ደንብ እዛው ኩባንያው ባዘጋጀላቸው  ቤት ውጭ ማደርና ከሰው ጋር መገናኘትም አይችሉም።ይህም  የግል ነፃነታችንን እንድንነፈግ አድርጎናል ትላለች።  “ከኩባንያው  ውጪ  ካሉ ሰዎች ጋር እንዳንገናኝ አልተፈቀደልንም።የእኛ የሰብአዊ መብት እጦት አሳዘነኝ ነው።” ትላለች።

 ባለፈው አመት ኪኦ ከተባረረች በኋላ ምትሄድበት ቦታ አልነበራትም።  አሁን የምትኖረው  ለሠልጣኞች በድጋፍ ቡድን በሚመራው መጠለያ ውስጥ  ነው።

 በአካባቢው የሠራተኛ ማኅበር ዳይሬክተር የሆኑት ዜን ካይ ረድተዋታል።  ዠን ከቻይና ወደ ጃፓን የመጣው ከብዙ አሥርተ ዓመታት በፊት ነው።  አሁን ሰልጣኞችን ከጉልበት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ በጃፓን በሚፈፀም  የጉልበት ብዝበዛን ተንተርሶ ሰዎችን ይመክራል።  ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከግል ነፃነት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎች በከፍተኛ ደረጃ እየጨመሩ መምጣታቸውን ተናግሯል።

 በአካባቢው የሰራተኛ ማህበር ዳይሬክተር የሆኑት ዜን ካይ

 ዜን ጋብቻዋ ለምን ችግር እንደፈጠረ ለማወቅ ከቀድሞው የኪኦ አሰሪ ጋር ተገናኝቶ ተወያይተዋል።  " ዋና ስራ አስፈፃሚው ሰልጣኞች ወደ ጃፓን መጥተው የተወሰኑ ክህሎቶችን እንዲያገኙና የማግባት ሁኔታ በጃፓን የቆይታ ጊዜያቸውን አላማ እንደሚያስለውጥ ።'' ተናግረዋል። ''ኩባንያው ትክክለኛ ምክንያቶች እንዳሉት እርግጠኛ ነው" ብለዋል ዠን ከዋናው  ሥራ አስኪያጁ  ጋር ከተነጋገሩ  በኋላ በሰጡት ምላሽ።

 ዜን ከኤን.ኤች.ኬ ለቀረበለት ጥያቄ ኩባንያው የኬኦ ጋብቻ የቪዛ ሁኔታዋን እንደሚቀይርና ስራዋን መቀጠል እንደማትችል ከኦፊሴላዊ ድርጅቱ  እንደተረዳ  ተናግሯል።

 

 የእገዳዎች  ምክንያት

 NHK የውጭ ሰልጣኞችን ወደ ጃፓን በማምጣት ላይ የሚሳተፉ ደላሎችን  ቃለ መጠይቅ አድርጓል። አብዛአዎቹ ደላሎች  ስማቸው እንዳይገለጽ ይፈልጋሉ።በዚህም NHK ተስማምቷል።

 "አንዳንድ ሰልጣኞች በድንገት የሚሰሩበትን ቦታ ከለቀቁ በኋላ ነገሮች ተለውጠዋል። በተለይም አሰሪዎች የሚያሰሯቸውን  ሰልጣኞች ከሌሎች የውጭ ሀገር ሰልጣኞችና አለም አቀፍ ተማሪዎች ጃፓንን በተመለከተ መረጃ እንዳያገኙ መገደብ ይፈልጋሉ።" ይላል።

ከውጭ ሀገር ወደ ጃፓን በሥራ ሰልጣኞች ተብለው የሚገቡ አብዛኛው  ልምድ የሌላቸውን በአነስተኛ ክፍያ ነው ካምፓኒው ሥራ የሚያሰራቸው።አንዳንድ አሰሪ ካምፓኒዎች ሰልጣኞች ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚገናኙ ከሆነ ስለተሻለ የስራ ሁኔታና ክፍያ  ማወቅ ስለሚችሉ ከካምፓኒው ሊጠፉና ስራቸውን ሊለቁ እንደሚችሉ  ስለሚያውቁ በዚህ በኩል ይጨነቃሉ።

 በጃፓን ይህ ሥራ የሚሰራው ደላላው አንዳንድ ሰልጣኞች ወደ ጃፓን ከመምጣታቸው በፊት ገዳቢ በሆኑ ውሎች እንዲስማሙ  እንደሚደረግ  ገልጿል።

"እነዚህ የተከለከሉትን የሚገልጹ ስምምነቶች በእጅ የተፃፉና በደላሎች የተያዙ ናቸው።ሁላችንም ሥራው ህገወጥ እንደሆነ እናውቃለን።ነገር ግን ድርጊቱ ህገወጥ ቢሆንም እነሱም  ተስማምተው ነው ወደ ጃፓን የሚመጡት ።ስለዚህ ሁላችንም ችግር አለ።በመሆኑም ያልተነገረው  ህግ  ዝም  ሊባል ይችላል።" ይላል።

ጃፓን በነበርኩበት ወቅት በወር በአነስተኛ ክፍያ የሚሰሩና የጉልበት ብዝበዛ የሚደረግባቸው  ሴት ኢትዮጵያውያንና ወንድ ቻይናውያን  አግኝቼ አውርቻቸው ስለነበረ ነገሩ እውነታነት ያለው ነው ።እነዚህ ኢትዮጵያውያኖች  ብቻ  ሳይሆን  ቻይናውያንም የሚሰሩበት ቦታ እራቅ ያለ በመሆኑ ከሰዎች ጋር መገናኘት እንደማይችሉ ።አብዛኛዎቹም  ከሰውነት ውጭ ሁኔታ ሆነው  ተመልክቻለው። የሚሰሩት የቻይና ካምፓኒ ወይም  ከኢትዮጵያውያን ጋር ግንኙነት ያላቸው  ካምፓኒ ውስጥ  ነው። በወር እስከ 117 ሺህ የን ያገኛሉ።በዚህ ላይ የቤት ክራይ ፣የመብራትና የጋዝና የውኃ ክፍያ ከሚያገኙት ላይ እንዲቆረጥባቸው  ይደረጋል።በተለይም  ቤተሰብ ለነበረው  ቻይናዊ  ቹንግ ወዳጄ  ሥራው አስቸጋሪ ነበር።ከቹንግ  ጋር  ለአንድ ወር አብሬው ሰርቻለው።እኔ የሚከፈለኝ ክፍያና እሱ የሚከፈለው ክፍያ እኩል አይደለም።በሙያውም ከእኔ የተሻለ ነው። እኔ የሥራውን አስቸጋሪነት ተመልክቼ የካምፓኒውን ባለቤት ክፍያውን አስተካክልልን አልኩት።አንድ አሜሪካው  እንዲያውም  ሥራውን ለመስራት መጥቶ ሶስት ሰዓት ብቻ ሰርቶ ነው ይህ  ሰው መሥራት የሌለበት  ሥራ ነው ብሎ ያቆመው።እኔ ግን እውቀቱን  በደንብ መቅሰም  ስለምፈልግ መሥራቱን ቀጠልኩ ለሁለታችንም በሰዓት የካምፓኒው ባለቤት  900 የን ለመክፈል ቃል ገባ።እኔ ግን በሰዓት 1000  የን ካልከፈልክ አልቀጥልም ብዬ  ሥራውን አቆምኩ።ቹንግ ግን ሦስት ልጆች ስለነበሩትና ማሽኑን እንዲያንቀሳቅስ ከቻይና ሀገር ያስመጣው  የሀገሩ ሰው  የሆነው የካምፓኒው ባለቤት ስለሆነ በዛው  ቀጠለ።እኔ ሥራውን ካቆምኩ በኋላ በተሻለ ክፍያ 1100  የን ሌላ ቦታ ሥራ አገኘው።

ሊሆኑ የሚችሉ መፍትሄዎች

 

ከአመት በፊት መጋቢት ወር የጃፓን የፍትህ ሚኒስቴር በሰልጣኞች የግል ህይወት ላይ ገደቦችን ማድረግ ህገ-ወጥ መሆኑን በመግለጽ ለአስተናጋጅ ኩባንያዎች  አስተላልፏል።

 ነገር ግን በውጭ አገር የጉልበት ጉዳዮች ላይ ልዩ ባለሙያተኛ የሆኑት ሾቺ ኢቡሱኪ መግለጫ አውጥቶ ማስተላለፉ  በቂ አይደለም ብለው ያምናሉ። የጃፓን መንግሥት ወደ ሀገሪቱ በደላሎች  አማካይነት በሥራ እየተባሉ የሚገቡት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርጉና ከሚነሱበት ሀገር ካለው ውጭ ጉዳይ መሥሪያቤትና የፖሊስ አካላት ጋርም ግንኙነት በማድረግ ጫና ማድረግ አለባት ይላል።  “ጃፓን የሠልጣኞቹ መብት እንዲከበር ከአጋር አገሮች ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ልትፈራረም ትችላለች፣ በነዚያ አገሮች ያሉ ደላሎች የተቀማጭ ገንዘብ፣ የቅጣት ወይም ሌሎች የሠልጣኙን ሰብዓዊ መብት የሚጥሱ ሁኔታዎችን የሚጠይቁ ከሆነ ፈቃዳቸው በአስቸኳይ መሰረዝ አለበት።  ጃፓን አጋር በደላላ የሚመጡ ሰራተኞች ብዙ ችግር ውስጥ እየገቡ ነው።ስለዚህ ከሀገራት ጋር በመመካከር ከተስራ ችግሮቹ ይቀረፋሉ። እንዲህ አይነት ደላሎችን በቅጣት እንዲቀጡ ም ጃፓን ልትጠይቅ ትችላለች።'' ሲል ገልፀዋል።

 ብዙ ያልተዘገቡ  ጉዳዮች

የኬኦ ጉዳይ የበረዶ ግግር ጫፍ ብቻ እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ።  ''አንዳንድ ሰልጣኞች የሞባይል ስልክ ለመጠቀም ነፃ እንዳልሆኑና ፓስፖርታቸው አንዳንድ ጊዜ በአሰሪያቸው እንደሚወሰድ ባቸው ነግረውኛል '' ይላ ል ዜን ።  በተጨማሪም አንድ ኩባንያ ነፍሰ ጡር የሆነች ሴት የወሊድ ፈቃድ መስጠት ስላልፈለገ ፅንስ እንድታስወርድ ሲገፋፋ የነበረበትን ጉዳይ ሰምቻለሁ።  ይህ ሁሉ በጃፓን ሕገወጥ  ነው ሲል ተናግሯል።

''ችግሩ ሰልጣኞቹ ራሳቸው መደበኛ ቅሬታ ለማቅረብ ፍቃደኛ አይደሉም። ምክንያቱም የሥራ ቦታቸውን እንዳያጡና ከካምፓኒው  እንዳይባረሩ ስለሚፈሩ ነው።በዚህ የተነሳ የጃፓን ባለሥልጣናት ደረሱ የተባሉ የሰበሀዊ ጥሰቶችና በደሎችን መለየት አስቸጋሪ ያደርገዋል።  ብዙ ኩባንያዎች ሰልጣኞቻቸውን እንዴት አድርገው  ጭካኔ  በተሞላበት ሁኔታ ይይዛሉ።''ሲል ዜን  ሳይናገር  አላለፈም።

 ''የጃፓን መንግስት ትክክለኛ የስራ ሁኔታን ለማረጋገጥ እርምጃ መውሰድ አለበት።  ምንም ነገር ካልተደረገ።እነዚህ የውጭ ዜጎች ወደ ሌላ ሀገር ሄደው ለመሥራት ሊመርጡ ይችላሉ። ያ ደግሞ በጃፓን ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል።'' በማለት ዜን አስተያየቱን  አጠቃሏል።