የኢትዮጵያ የትግራይ ግጭት በቅርቡ ያበቃል - ኡሁሩ ኬንያታ


 

 

ከወሰንሰገድ መርሻ (ጮራ ዘአራዳ)

>

 

 - ኡሁሩ ኬንያታ  “አዲሱን ዓመት ብቻ ሳይሆን የሰላምንም ገናን በታላቅ ተስፋ እናጣጥማለን።” ብለዋል።

በኢትዮጵያና በህወሓት መካከል ያለው ድርድር

- የኬንያው ፕሬዝዳንት  ዊልያም ሩቶ ለኢትዮጵያ ሰላም  መስፈን ሁሌም ከጎኗ ነን አሉ።

 

 - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትግራይ ሥራውን ጀመረ 

ት ያለውን ጦርነት በማቆም መደበኛ ሁኔታው እንደገና ለመመለስ ፓርቲዎች ተከታታይ እንቅስቃሴዎችንና እርምጃዎችን  መውሰዳቸውን የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ገለጹ።

 

 በዚሁ ስብሰባ ማጠቃለያ ላይ ጡረተኛው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል በቅርቡ ሰላም እንደሚሰፍን ያላቸውን እምነት ገለፀዋል።

 https://youtu.be/TL1qfKnn-y4

 

 የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ከፍተኛ የፓናል አባል የሆኑት ኡሁሩ በኢፌዴሪና በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ መካከል የተጀመረው ድርድር በትክክለኛው አቅጣጫ እየሄደ ነው  ብለዋል።

 "አዲሱን አመት ብቻ ሳይሆን የሰላም ገናን በታላቅ ተስፋ እናጣጥማለን" ሲሉም ኡሁሩ ከሁለቱም ወገኖች የተውጣጡ የጦር አዛዦችን ያሰባሰበው ሁለተኛው የሰላም ስብሰባ ከተጠናቀቀ በኋላ ተናግረዋል።

 

 ኡሁሩ እንዳሉት የአፍሪካ ህብረት ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ በድርድር መሃል ላይ ለነበሩ ፓርቲዎች በጣም ደስተኛና አመስጋኝ ነውም ብለዋል።

 

 "በእርግጥ ትልቅ እድገት እያደረግን ነው።  በትግራይና በኢትዮጵያ ያለውን መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ ፓርቲዎች ተከታታይ እንቅስቃሴዎችንና እርምጃዎችን መውሰዳቸው ጥሩ ነገር ነው ።” ብለዋል።

 

 በክልሉ ተገኝተን ድርጊቱን በምንከታተልበትና በማጣራት ላይ የምንገኝበት ትክክለኛ መግለጫ እንዲሰጡ ተስማምተናል።

 

 ባለፈው ሐሙስ የተጠናቀቀው የሁለተኛው የከፍተኛ አዛዦች ስብሰባ በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ተወካይና በቀድሞው  የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴንጎ ኦባሳንጆ ናይሮቢ ከሚገኙ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ የፓነሉ  አወያዮች አባላት ጋር በመሆን  ውይይቱን መርተዋል።

 

 ስብሰባው ህዳር 2020 ከተካሄደ ከወራት ውጥረት በኋላ የተቀሰቀሰውንና  የበርካቶችን ህይወት ያወደመውን ጦርነትን ለማስቆም የሚደረገው  ጥረት አንዱ አካል ነውም  ተብሏል።

 

 በትግራይ 5.2 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታ አሁንም የሚያስፈልጋቸው ሲሆኑ 3.8 ሚሊዮን ህዝብ ደግሞ የጤና እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቋል።

 

 በእርስ በርስ ጦርነቱ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል። በሁለቱም  ወገኖች ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች  ክስ ተመሠርቶባቸዋል።

የሰብአዊ እርዳታ ሰራተኞች ያለምንም  እንቅፋት እንቅስቃሴ እንዲያደርጉና ሁለቱም ወገኖች  እንደሚያመቻቹ  ተገልጿል።

 

 "ፓርቲዎቹ በስምምነቱ በተደነገገው  መሰረት ለሰብአዊ  እርዳታ ሰራተኞችና ድርጅቶች ደህንነት እንዲሁም የሲቪሎችን ጥበቃ ለማድረግ ተስማምተዋል።" ተብሏል።

 

p>

አዲሱ የኬንያ ፕሬዝዳንት ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በኢትዮጵያ ያለውን ጥላቻ እንዲያበቃ  ማድረጋቸው  ታውቋል።

 

ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጦርነቱን ለማቆም የሁለቱም ወገኖችን  አመራሮችን አመስግነዋል።

 

 ፕሬዝዳንቱ ዊሊያም ሩቶ ሰሞኑን በሰሜን ኢትዮጵያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ለመመርመር የተደረገውን ስብሰባና የኢትዮጵያ መንግስትና የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ አመራሮችን ለሰላሙ  ያላቸውን ቁርጠኝነት ሳያደንቁ  አላለፉም።

 

 ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የሁለቱም ወገን አመራሮች ጦርነቱን ለማቆም ቁርጠኛ መሆናቸውንና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ለማድረግ ሀገራቸው  ቃል መግባታቸውን ተናግረዋል።

 

 "የአካባቢውን ሰላም በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።" ብለዋል።

 

ይህን ተከትሎ  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትግራይ ክልል ጦርነት በተከሰተባቸው አንዳንድ ከተሞች የፋይናንስ አገልግሎት መጀመሩን ገልጾ፣ ከአንድ አመት በላይ በዘለቀው አገልግሎት ነዋሪዎቹ ገንዘባቸውን እንዲያገኙ  መደረጉን  ተናግሯል።

 

 

 በያዝነው ሳምንት እንደተገለፀው ባለፈው ወር በፌደራል መንግስትና በትግራይ ተወላጆች መካከል በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን አስከፊ ግጭትና ሰብአዊ ቀውስ ለማስቆም ያለመ የሰላም ስምምነት መፈራረሙን ተከትሎ ነው ይህ ተግባራዊ የሆነው ተብሏል።በቅርቡ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በሽሬ፣ አላማጣና ኮረም ከተሞች ያሉን ቅርንጫፎች ከውጭ እና ከሀገር ውስጥ የተላከ ገንዘብ መቀበል እንዲሁም ገንዘብ ማስገባት መጀመራቸውን የሀገሪቱ ትልቁ ባንክ በላከው መግለጫ  መላኩን አልጀዚራ ገልጿል።

 

 "ባንካቻችን ከዚህ በፊት በሰሜናዊው የሀገሪቱ ክፍል በተፈጠረው አለመረጋጋት ምክንያት የባንክ አገልግሎቶችን ለማቆም ተገደን ነበር።" ሲል በመግለጫው ላይ ተገልጿል።

 

 "አገልግሎታችንን ለማስፋት በሁሉም ቅርንጫፎች ደረጃ በደረጃ ለማስጀመር በምናደርገው ሁኔታዎችን እያየን  መክፈታችንን እንቀጥላለን።" ብሏል።

 

 የሰሜን ኢትዮጵያ መዳረሻ በከፍተኛ ሁኔታ የተገደበ ሲሆን፤ትግራይ ከአንድ አመት በላይ በኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተዘግታ ቆይታለች። ይህም ጋዜጠኞች በገለልተኛ ደረጃ መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ ማረጋገጥ አልቻሉም።በደቡብ አፍሪካ ህዳር 2 የሰላም ስምምነት ከተፈራረሙበት ጊዜ ጀምሮ በፌዴራል ወታደሮችና በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ መካከል ውጊያው የቆመ ሲሆን ህወሓት 65 በመቶው ሠራዊቱ  ትጥቁን በመፍታት ወደ ሰላማዊ ህይወቱ ተመልሷል።።

 

 በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የሀገሪቱ ኤሌክትሪክ ኦፕሬተር እንደገለፀው  በግጭቱ ምክንያት ከአንድ አመት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋረጦባት የነበረው  የትግራይ ዋና ከተማ መቀሌ  ከብሔራዊ የኃይል አውታር ጋር መገናኘቱን አስታውቋል ።

 

 የእርስ በርስ ጦርነቱ ትግራይን አውድሟታል። መሰረታዊ አገልግሎቶችን ማለትም የባንክ፣ የመብራት፣ የነዳጅና የመገናኛ ብዙሃን አቅርቦት እጦትም ከአንድ አመት በላይ  ቆይቶ  ነበር።

 

 ከስምምነቱ በኋላ የሰብአዊ እርዳታ ወደ ሰሜን ትግራይ ክልል ገብቷል ነገር ግን የህዝቡን አጣዳፊ ፍላጎቶች ማሟላት ግን አልተቻለም።የሚገባው እርዳታ  በጣም  አናሳ  ነው።

 

 በጦርነቱ ምክንያት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ግልጽ ባይሆንም ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ ፤ቲንክ ታንክና አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጦርነቱ  ብዙ ሰዎች ያለቁበት ከአለም ደም አፋሳሽ ጦርነቶች  አንዱ ነው ሲሉ ገልፀውታል።

 

ሁሉም ወገኖች በፈፀሙት በደል የተከሰሱ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ደግሞ ግጭቱ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ከቀያቸው ማፈናቀሉን እንዲሁም  በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩትን ለረሃብ አደጋ  ማጋለጡን አስታውቋል።

 

 የሰላም ስምምነቱ ግጭቱን ለማስቆም፣ የትግራይ ታጋዮችን ትጥቅ በማስፈታት፣ የፌደራል መንግስት ስልጣንን ለመመለስና ወደ ክልሉ ሰራዊቱን ለማስገባት  ያለመ  ነው  ተብሏል።

 

 ነገር ግን ስምምነቱ በግጭቱ ወቅት የኢትዮጵያን መንግስት የሚደግፉትንና በአሰቃቂ በደል የተከሰሱትን የኤርትራ ሃይሎች ከሀገር መውጣታቸውን የሚገልጽ ነገር የለም።

 

 እርቁ ከተደረሰበት ጊዜ ጀምሮ ህወሓት የኤርትራ ወታደሮችን በትግራይ የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈፅመዋል በማለት በየጊዜው እየከሰሰችና እያወገዘች ነው። ሰሞኑንም ዘረፋ ፤አስገድዶ መድፈርና ወጣቶችን እያፈኑ መውሰድ የኤርትራ ወታደሮች እየፈፀመ ነው  ሲል መግለፁ አይዘነጋም።

 

 እንደ የተባበሩት መንግስታት የአለም የምግብ ፕሮግራም መረጃ እንደሚያሳየው በሰሜን ኢትዮጵያ ከ13 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በሰብአዊ እርዳታ ላይ የተመሰረተ ሲሆን ከነዚህም መካከል ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው የትግራይ ህዝብ የሆነው  ስድስት ሚሊዮን ህዝብ  መሆኑን ገልፆ ነበር ።

 

 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በህዳር ወር 2020 ወታደሮቻቸውን ወደ ኢትዮጵያ ሰሜናዊ ጫፍ በመላክ በወቅቱ የክልሉ ገዥ ፓርቲ ህወሓት የፌደራል ጦር ካምፖች ላይ ጥቃት ፈጽሟል በማለት  በመክሰስ ጦርነቱ እየተፋፋመ  መሄዱ  ይታወሳል።

 

 የኖቤል የሰላም ተሸላሚው ዶክተር አብይ በ2018 ስልጣን ከመያዛቸው  በፊት ለሶስት አስር አመታት የአፍሪካ ቀንድ ሀገር የሆነችውን ኢትዮጵያ ህወሓት ተቆጣጥሮ  እንደነበር ይታወሳል።

https://youtu.be/TL1qfKnn-y4

 

 

  ግጭቱ እንዴት ?በማን ? ተጀመረ?

  

አንድ መታወቅ  ያለበት የትግራዩ ግጭት ኢትዮጵያ ውስጥ  ከበፊት ከአባቶቻችን ጀምሮ  የነበረ ጉዳይ ነው። አሁን እንደ አዲስ ሊታይ አይገባውም።የሩቅን ትተን በደርግ ጊዜም  ላለፉት 17 አመታትም ይህ ጦርነት በክልሉ ነበረ።በርግጥ ስልጣኑን ህወሓት ከተቆናጠጠ በኋላ ሀገሪቱን ስለሚመራ ጦርነቱ ለመቆም  ቻለ ።እንደገና ህወሓት ስልጣኑን ሲነጠቅ  ደግሞ ሌላ ጦርነት በክልሉ ተነሳ።

ኢትዮጵያ በመከላከያ እረገድ ከአፍሪካ በአሁኑ ወቅት ጠንካራ የጦር ኃይል ካላቸው ሀገሮች አንዷ ነች።ከፌድራል መከላከያ ኃይል በተጨማሪ የክልል ፖሊስ፣ልዩ ኃይልና ሚሊሻዎችን ጨምሮ   በርካታ  የታጠቁ ኃይሎች  በሀገሪቱ ውስጥ  አሏት።  

 

ከዚህ ቀደም  ከጎረቤት ኤርትራ ጋር በተፈጠረ ግጭት ምክንያት በትግራይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፌደራል ወታደሮችም  በአካባቢው  አሉ።  የየክልሉ መንግስታት በአብዛኛው የተከፋፈሉት ሥር በሰደደ የጎሳ መስመር  ወይም  ብሄርተኝነት  በተጠናወተው አካሄድ  ላይ  ያተኮሩ  

ናቸው  ።

 

 ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት ህወሓት ኢትዮጵያን ለሦስት አስርት አመታት በብረት መዳፍ ውስጥ በማስገባት  ህዝቡን እየረገጠ  ሲያስተዳድር የኖረ ሲሆን በእርግጥ  በሀገሪቱ  ላይ የመረጋጋትና የኢኮኖሚ እድገትን በመቆጣጠር  በኩል ይወደሳል። ይህም መሰረታዊ የሲቪል እንዲሁም የፖለቲካ መብቶች ዋጋ ላይ  መስዋዕትነት  ሲያስከፍል ቆይቷል ።በአንፃሩ  ፓርቲው አምባገነናዊ  አገዛዝ በመከተሉ ህዝባዊ አመጽን ቀስቅሶ በመጨረሻ እንደ እንዝርት የሚያሽከረክሯቸውን ከዶክተር አብይ በፊት የነበሩትን አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣናቸው  እንዲለቁ  አስገደዳቸው። 

 

 እ.ኤ.አ. በ 2018 ዶክተር አብይ ስልጣን ላይ ሲወጡ በገዢው ፓርቲ ኢህአዲግ የተሾሙ  ሲሆን ህወሓትም ዶክተሩን “ ከልጅነቱ ጀምሮ እኛ ያስተማርነውና ያሰለጠነው  ነው “ በማለት ምርጫውን ሙሉ ለሙሉ  ደግፈዋል።ዶክተር አብይም ውጥረቱን ለማርገብና በሀገሪቱ ላይ ለውጥ ለማምጣት ሲሉ ያረጀውን የፖለቲካ ስርዓት ለማሻሻል  ቻሉ። 

 

ነገር ግን ልክ ጠቅላይ ሚንስትር ሆኖው  ዶክተር አብይ እንደ ተሾሙ   ህወሓት የመሰረተው የገዢው ፓርቲ -- የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ወይም   ኢህአዲግ አራት ፓርቲዎችን ያቀፈውን -- ወደ አንድ አዲስ የብልጽግና ፓርቲ እንደገና ማዋቀራቸው ክፉኛ  አስቆጣው ። በዚህም የተነሳ  በሂደቱ ወያኔን ማግለላቸው  በህወሓትና በቀሪው  የኢህአዲግ  አባላት  ዘንድ  ከፍተት  እንዲፈጠር  

አድረገው  ።

 

 አዲሱ የተፈጠረውን ብልፅግናን  የፖለቲካ ድርጅት ለመመስረት ባደረጉት እንቅስቃሴ፣ የሀገሪቱ የፌደራል ስርዓት -- እንደ ትግራይ ላሉ ክልሎች አልተዋጣላቸውም ።ጉልህ  የሆነ የራስ ገዝ አስተዳደር የሚያረጋግጥ - ስጋት ነው  የሚል በአንዳንድ ክልሎች ዘንድ ፈጥሯል። በዚህም የተነሳ  የትግራይ መሪዎች ወደ ሰሜን ወደሚገኘው  ተራራማ  እምብርታቸው  ሄደው የራሳቸውን ክልላዊ መንግስት መቆጣጠራቸውን  ቀጠሉ ።

 

 እ.ኤ.አ. በሴፕቴምበር 2020 የትግራይ ተወላጆች በኮራና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የኢትዮጵያ  መንግሥት ያዘገየውን የሀገሪቱን ምርጫ አንቀበልም  አሉ።ክልሉ የምርጫ ቦርዱን  ውሳኔን በመቃወም የትግራይ ክልልን የፓርላማ ምርጫ  እራሳቸው አስመራጭ ኮሚቴ አዋቅረው  ምርጫውን አካሄዱ።  ከምርጫ  ቦርዱ እውቅና ውጭ  የተካሄደው   ምርጫ  ቦርድን ብቻ  ሳይሆን የዶክተር አብይ ፓርቲንና ሌሎች ፓርቲዎችን አስቆጣ።  በዚህም የተነሳ ዶክተር አብይና ፓርቲያቸው  ምርጫውን  ሲቃወሙ ውጥረቱ ይበልጥ ከረረ።  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ምርጫውን ሕገወጥ ሲሉ የፓርላማ አባላት ለሕወሃት አመራር የሚሰጡትን የገንዘብ ድጋፍ በማቋረጣቸው በክልሉና በፌዴራል መንግሥቱ መካከል ፍጥጫው  ይበልጥ እንዲፈጠር አድርጓል።

 

 ህዳር 4 ቀን 2020 ህወሓት ከትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና መቐለ ወጣ ብሎ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ የፌደራል ጦር ሰፈር ላይ ጥቃት ፈጸመ። ህወሓት የመከላከያ ሠራዊት  መሳሪያዎቹን ሰርቀም ተባለ።ይህ ሁኔታ ደግሞ  የኢትዮጵያ መንግሥትን አስቆጥቶ ዶክተር አብይ በአማፂ ቡድኑ ላይ ወታደራዊ ጥቃት እንዲፈፀም ትእዛዝ  እንዲሰጡ  አደረጋቸው።ከዚህ ሌላ ከትግራይ አጎራባች ክልሎች ከአማራ ክልልና ከአፋር  ክልል  የመጡ  የሀገር ወታደሮችና ተዋጊዎችን በጣምራ  ወደ ትግራይ  ክልል ላኩ።  የኤርትራ ወታደሮችም  ከእነዚህ ኃይሎች  ጎን  በመቆም  የትግራይ  አማፂያንን  ለመውጋት  ቻሉ።

 

ዶ/ር አብይ የመንግስት ሃይሎች መቀሌን ከያዙ ከሶስት ሳምንታት በኋላ ጥቃቱን በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በመግለፅ ለአዲስ አበባ ታማኝ የሆኑ ጊዜያዊ አስተዳደር በትግራይ እንዲሾም  አደረጉ።  ከአንድ አመት በኋላም ቢሆን ጦርነቱ ግን  ዶክተር አብይ እንዳሉት አልተጠናቀቀም  ነበር።

እንደገና  ጦርነቱ  አገረሸ።

 

 ምን አይነት ችግሮች  ተፈፀሙ  ? 

 

 ለወራት በተካሄደው ግጭት ከፌድራል መንግሥት ጋር አብረው በቆሙት ላይ የአስገድዶ መድፈርና በትግራይ ተወላጆች ላይ የዘር ጭፍጨፋ  እየተካሄደ ነው። የሚለውን ሁኔታ  ዶክተር አብይ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ምንም አይነት ጉዳት ሠራዊታቸው እንዳላደረጉ እንዲሁም  የኤርትራ ወታደሮችም  ወደ ትግሉ ከኢትዮጵያ መከላኪያ  ሠራዊት ጋር አለመቀላቀላቸውን አስተባበሉ። p>

 

 ነገር ግን ከአለም አቀፍ ታዛቢዎች፣የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጋር  የሲኤንኤን የተገኙ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት በህወሓት የተነሱ አቤቱታዎች  ትክክል መሆናቸውን  ሲ ኤን ኤን አረጋግጫለው  ሲል  ዘገበ።የኢትዮጵያ መንግሥት ግን የሲ ኤን ኤንና የሌሎች ዓለም አቀፍ ዘገባዎችን ከእውነት  የራቀ  የሐሰት ፕሮፓጋንዳ  ነው  በማለት ሁኔታውን አጣጠለ።

 

 እንዲያውም ሲ ኤን ኤን በትግራይ በኩል በአማራና በአፋር ክልሎች ስለተፈፀሙ  የሰበአዊ ጥሰቶች  ያለው  ነገር  የለም።

 

 በውጊያው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል፣ የስደተኞች መጠለያ ካምፖች፣ ዘረፋ፣ ጾታዊ ጥቃት፣ እልቂትና ከህግ አግባብ ግድያ ጋር በተያያዘ  ሁኔታ ሁለቱንም ወገኖች የአውሮፓ ህብረትና ዓለም አቀፍ የሰበአዊ መብት ተከራካሪዎች ተጠያቂ ማድረጋቸውም  አልቀረም ።  

 

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርስ በርስ ጦርነቱ ከሁለት አስርት አመታት በፊት ከታየው እጅግ የከፋ ነው ሲል ገለፀ።ከኢትዮጵያ በርካታ ስደተኞች  ወደ ጎረቤት ሀገር ሱዳን ተሰደዋል። ይህ ደግሞ  የጎሳ ግጭት እንዲፈጠር ምክንያት እንደሆነና በአፍሪካ ቀንድ ያለውን  አስከፊውን  የግጭት   ሁኔታ  ያሳያል ሲል ሁኔታውን  ገለፀ።

 

 የኢትዮጵያ መንግስት የጋዜጠኞችን ተደራሽነት በእጅጉ እንዲገደብ  አድርጓል። በመንግስት የተደነገገው የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት  (ቴሌ፣ትራንስፖርት፣ሚዲያዎች ወዘተ, ) በትግራይ መቋረጡ በክልሉ የሚታዩ ድርጊቶችን በትክክል  ማወቅ  አልተቻለም።በዚህም የተነሳ የችግሩን መጠን ለመለካት ወይም በእርስ በርስ ጦርነቱ የተረፉ ሰዎችን ለይቶ ለማረጋገጥ ሁኔታውን  ፈታኝ አድርጎታል።

 

 ነገር ግን የጭካኔ ድርጊቶችን የሚያሳዩ ማስረጃዎች በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ በሁለቱም ወገኖች  መውጣት ጀምረው ነበር።

 

 የትግራይ ተወላጆች የካቲት 28 ቀን 2021 ከመቀሌ በስተሰሜን በምትገኘው በውቅሮ ከተማ በጅምላ መቃብር መገኘቱ  ተገለፀ።

 

 በየካቲት ወር ሲ ኤን ኤን እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባደረጉት የተለየ ምርመራ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ደንገላትና አክሱም ከተሞች ባለፈው አመት መጨረሻ ላይ ያደረሱትን ጭፍጨፋ የሚያሳይ ማስረጃ  በቴሌቪዥን  ጣቢያው  ላይ  አቀረበ።

 

 በሰኔ ወር የወጣው ሌላ የሲኤንኤን ምርመራ በጥር ወር በትግራይ ክልል ማኅበረ ደጎ ከተማ በኢትዮጵያ ወታደሮች ስለተፈጸመው ጭፍጨፋ አዲስ መረጃ ማጋለጡን  ይፋ አድርጓል።  

 

ሪፖርቱ የጅምላ ጭፍጨፋውን ከፈጸሙት መካከል ጥቃቱ በተፈጸመበት ቦታ ላይ የጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ እንዳለው  ገልጿል።

 

 ኤፕሪል ወር ላይ ከትግራይ በቀረበው ልዩ ዘገባ ላይ ፣ ሲኤንኤን የኤርትራ ወታደሮችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን  ለማየት ተችሏል - አንዳንዶቹ የድሮ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ዩኒፎርም ለብሰው -በማእከላዊ ትግራይ ሙሉ በሙሉ ከቅጣት ነፃ ሆነው ሲንቀሳቀሱ፣ የፍተሻ ኬላዎችን እየጠበቁ እንዲሁም ዶክተር አብይ ቃል ከገቡ ከአንድ ወር በላይ በረሃብ ለሚሰቃዩ ህዝቦች አስፈላጊ የሆነ ሰብአዊ እርዳታ እንዳይደረስ አግዷል በማለት  ገለፁ። ሲ ኤን ኤ  በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ  ስለተደረገው የሰበአዊ ጥሰት ያለው  ነገር  የለም ።የማይክድራውንና ሌሎች   

ጭፍጨፋዎችን ትተን  በአፋር ክልል በዞን4 ግምባር በያሎ ወረዳ በመድፍ የጨፈጨፋቸው ንፁሃን የጅምላ መቃብር  መገኘቱ።አሁንም  በርካታ ሰዎች ህወሓት በፈጸመው የከባድ መሳሪያ ጥቃት 5 የአንድ ቤተሰብ አባላት ሕይወት ማለፉንንም  እየሰማን ነው ይሁንና ሲ ኤን ኤ  በዚህ ጉዳይ ላይ ያለው  የለም ።

 

ህወሓት  በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አበርገሌ ወረዳ በፈጸመው በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት አምስት የአንድ ቤተሰብ አባላት ሕይወት አለፏል ተብሏል። ከአምስቱ ሰዎች በተጨማሪ በአንድ ሰው ላይ የአካል ጉዳት መድረሱም  ተገልጿል። በርካታ ቤቶችም ወድመዋል ተብሏል፡፡ ሌላው ቀርቶ “በአሸባሪው ህወሓት መሪዎች ምክንያት በርካታ የትግራይ ክልል ልጆች እያለቁ ነው” - በማለት  በምዕራብ ግንባር  በቅርቡ  የተይዙ የትግራይ  ምርኮኞች  መግለጻቸውን በመንግስት  ሚዲያ ላይ እያየናቸው  ነው።

 

ህወሓት ወደ ጦርነት ልኳቸው ከነበሩ ምርኮኞች መካከል በመከላከያ ሰራዊታችን እና በጥምር ጦሩ የተማረኩ የትግራይ ክልል ወጣቶች ስለ አስከፊው ጦርነትና ከተማረኩ በኋላ የተደረገላቸውን እንክብካቤ  ለመንግሥት  መገናኛ ብዙሐን  እንደተናገሩት  ከሆነ። 

 

ለቤተሰቧ የመጀመሪያ ልጅ የሆነችው አፀደ ወልደ ሚካኤል፣ በግዳጅ ወደ ጦርነት መግቧቷን እና በየጦር አውድማው በርካታ የትግራይ ክልል ወጣቶች ማለቃቸውን ተናግራለች። 

 

ሌላኛው፣ የ16 አመቷ መርሀዊት ግደይ ስልጠና ወስዳ መግባቷን ገልፃ በነበረው ጦርነት አስቸጋሪ ጊዜያትን ማሳለፏን ገልጻለች ።

 

 ህወሓት በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ የብርብር አንደኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤትን አውድሟል። 

የትምህርት ቤቱ ርእሰ መምህር አበበ ደባሽ እንደነገሩት በ1992 ዓ.ም ተገንብቶ ሥራ የጀመረው  ይህ ትምህርት ቤት በሥሩ ሁለት የሳተላይት ትምህርት ቤቶች አሉት። ባለፈው የትምህርት ወቅት በአጠቃላይ ከ8 ሺህ 550 በላይ የሚደርሱ ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተምር ነበር። አሸባሪው ሕወሓት በአካባቢው በወረራ በቆየባቸው ወራት ትምህርት ቤቱን አገልግሎት መስጠት እንዳይችል አድርጎ እንዳወደመው   ገልጸዋል፡፡ 

 

ርእሰ መምህሩ በ2015 ዓ.ም የትምህርት መርሃ ግብር ብርብር አንደኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትመህርት ቤትን ከደረሰበት ውድመትና ዘረፋ አንጻር ሥራ ማስጀመር የሚከብድ ነው ብለዋል።

አሁን ላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ መመዝገብና ትምህርት ማስጀመር የሚያስችል ሁኔታ የለም ነው ያሉት ርእሰ መምህሩ፡፡ 

የተማሪዎች ሰነድና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ሁሉ በሽብር ቡድኑ ወድመዋል ብለዋል። አቶ አበበ እንደገለጹት የሽብር ቡድኑ በትምህርት ቤቱ ላይ ድጋሜ በፈጸመው ወረራ የተማሪዎችን መማሪያ መጽሐፍት፣ ኮምፒውተሮች፣ ጠረጴዛ፣ ጥቁር ሰሌዳ፣ የትምህርት ቤቱ በርና መስኮቶች እና ሌሎችም የትምህርት ግብዓቶችን ሙሉ በሙሉ  አውድሟል፤ ዘርፏል። 

የሽብር ቡድኑ በየደረሰበት ሁሉ ተቋማትን አውድሟል፤ የሚችለውንም ዘርፏል፤ የብርብር አንደኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤትም የጥፋት ቡድኑ ሰለባ ኾኗል ያሉት ደግሞ የብርብር ቀበሌ ሊቀመንበር ቄስ አበበ መንግሥቴ ናቸው። 

ትምህርት ቤቱን መልሶ በመገንባትና አስፈላጊውን ግብዓት ሁሉ ተሟልቶ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ መሥራት እንደሚገባ ነው የተናገሩት።  

በወረራ ወቅት ሳተላይት ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የጠላት ምሽግ ኾነው እንደነበር የተናገሩት የትምህርት ቤቱ ርእሰ መምህር አበበ ደባሽ   መንግሥት ቅድሚያ ሰላምብ ማረጋገጥና አካባቢውን ማጽዳት አለበት ብለዋል። ትምህርት ቤቱን ወደ ነበረበት የመማር ማስተማር ሥራው ለመመለስ የሚመለከተውን ሁሉ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግም  ጥሪ  አቅርበዋል።የህወሓት ቡድን በያዛቸው አካባቢዎች ሁሉ ትምህርት ቤቶችና የመሰረተ ልማት አውታሮችን እያወደመና እየዘረፈ እንደሚ ሄድ የአማራ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ገልጿል።

 

 በተራሮች ላይ  የታዩ እልቂቶች

 

 ሁሉም በግጭቱ ውስጥ ያሉ ተዋናዮች አሰቃቂ ድርጊቶችን ፈጽመዋል ተብሎ ተከሰዋል።በተለይም የኤርትራ ኃይሎች ከአንዳንድ በጣም አሰቃቂ ድርጊቶች ጋር  የተያያዘ ነበር።  የኤርትራ ወታደሮች የጅምላ ግድያና አስገድዶ መድፈር ከመፈጸም በተጨማሪ በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች የምግብ እርዳታ ሲዘጉና ሲዘርፉም  ተገኝተዋል በማለት  ሲኤን ኤ  ገልጾ  ነበር።

 

የኤርትራ መንግስት በትግራዩ ህዝብ ላይ ጭካኔ እንዳላሳየ  በተደጋጋሚ ሲናገር   ቆይቷል።  የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ማንኛውንም ጥፋት ለማጣራት ቃል ገብቷል።

 

 በኢትዮጵያ ባለፉት አስርት ዓመታት የከፋውን የበረሃ አንበጣ ወረራ ተከትሎ በመኸር ወቅት የተቀሰቀሰው ግጭት፣ ትግራይን ለከፋ የምግብ ዋስትና እጦት ዳርጓል።

 በሴፕቴምበር ወር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት “በእርግጥም  የሰብአዊ ዕርዳታ እገዳ” በማለት፤ በትግራይ ውስጥ ከ 5 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ማለትም 90% የሚሆነው ህዝብ ለችግር ተዳርጓል ሲል ገለፀ። - ሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን 400,000 ሰዎች በረሃብ ክፉኛ በመውደቃቸው  አስቸኳይ ምግብ ያስፈልጋቸዋል  ሲል  ተናገረ ።ጦርነቱ ግን እነዚህ ሰዎች አስቸኳይ ምግብ እንዳያገኙ  ክፉኛ እየገደበ ነው  መሆኑንም  የተባበሩት  መንግሥታት  ገለፀ። 

 .

 በዚያ ወር መገባደጃ ላይ የመንግስታቱ ድርጅት የእርዳታ ሃላፊ ማርቲን ግሪፊዝ በጦርነት የተመሰቃቀለውን አካባቢ “ሰው ሰራሽ” ረሃብ እያስጨነቃቸው  መሆኑን በማወጅ የኢትዮጵያ መንግስት ተደራሽነቱን እንዲያመቻች አሳስበው  ነበር።

 

 የኢትዮጵያ መንግስት ዕርዳታን እየከለከለ ነው የሚለውን ውንጀላ በተደጋጋሚ ውድቅ ሲያደርግ  ቆይቷል።  የግሪፍዝ አስተያየት ከቀናት በኋላ ኢትዮጵያ ሰባት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣናትን ከሀገሪቷ እንዲባረሩ አዘዘች። ከነዚህም መካከል የእርዳታ ስራዎችን ከሚያስተባብሩ ድርጅቶች ውስጥ  ይገኙባቸው  ነበር እንደ ሲ ኤን ኤን ዘገባ ከሆነ።

 

 ዶክተር አብይ እንዴት ትልቁን የኖቤል የሰላም ሽልማትን አገኙ?

 

 የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በትግራይ አማፂያን ላይ ጦርነት ከማወጃቸው  አንድ አመት በፊት ጦርነትን "የገሃነም ምሳሌ" በማለት  የኖቤል የሰላም ሽልማት በተቀበሉበት ወቅት  ንግግር አድርገው  ነበር።  ከጎረቤት ኤርትራ ጋር ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን ግጭት በማስቆም ና በኢትዮጵያ ጉልህ ለውጦችን በማድረጋቸው ለነበራቸው ሚና ትልቁን የክብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

 

 ኤርትራ በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ አካል ነበረች፣ ግን በ1993 ከ30 ዓመታት የትጥቅ ትግል በኋላ ነፃነቷን አገኘች።  እ.ኤ.አ. ከ1998 እስከ 2000 ዓ.ም  ኢትዮጵያና ኤርትራ ጦርነት ሲያካሂዱ  ቆይተዋል።ከሁለቱም ወገን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ጦርነቱ ገድሏል ። ዶክተር አብይ ስልጣን ከያዙ በኋላ ግን ከኤርትራ ጋር የነበረው አለመግባባት ተወግዶ  የእርስ በርስ ትብብርና በአካባቢው  ፍፁም  መረጋጋት ተፈጠረ።

ዶክተር  አብይ ስልጣን እንደያዙ  ከኤርትራ ጋር ያለውን ግንኙነት ወደ መደበኛ ደረጃ እንዲሸጋገርና አብረው ከዚህ በፊት ይኖሩ እንደነበሩት ሁሉ የሁለቱን ሀገር ህዝቦችን አንድ ለማድረግ በፍጥነት ለመንቀሳቀስ  ችለዋል።

 

 ዶክተር አብይ በኢትዮጵያ ውስጥም በሚደረገው የለውጥ እንቅስቃሴም ከፍተኛ ለውጥ በማምጣት ዘላቂ የሆነ ሰላምና መረጋጋት ለመፍጠርና ለውጥ ለማምጣት ተስፋ አድርገው ነበር።  እንዲሁም ከኤርትራ ጋር እርቅ ለመፍጠር፣ ከባድ የደህንነት ህግን ለማንሳት ችለዋል።በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት፣ የቴሌኮሙኒኬሽን ኢንዱስትሪውን ለመክፈት እና የግል ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋትም   ይበልጥ  ተንቀሳቅሰዋል።

 

 ነገር ግን ኢትዮጵያን አንድ ሊያደርጉ ይችላሉ  የተባሉት መሪ ስማቸው በፍጥነት እያሽቆለቆለ ሄዶ ከኤርትራ ጋር ያደረጉት እጅግ የተወደሰ የሰላም ስምምነት ሁለቱ አገሮች ከጠላታቸው ከወያኔ ጋር ጦርነት ውስጥ እንዲገቡና እንዲለያዩ  የሚያደርገውን መንገድ  የከፈቱ  ይመስላል።

 

 ግጭቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ብሔርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ወደ ሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ሲደርሱ ቆይተዋል። ከነዚህም መካከል የዶክተር አብይ የትውልድ ክልል በሆነው በኦሮሚያ ክልል ጨምሮ በሌሎች  ክልሎች  የታጠቀው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) በአብይ መንግስት ላይ “ሙሉ ጦርነት”  ከፍቶ ይገኛል።

 

የብሄር ብሄረሰቦችን መለያየት ለሀገሪቱ የማይጠቅም  በመሆኑ ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች በአንድነት እንዲኖሩ ለሰላማዊ ዲሞክራሲያዊ  ሽግግር መንገድ ለመዘርጋት ቃል ቢገባም  እንደታሰበው  ግን  አልሆነም  ።ከጊዜ ወደ ጊዜ የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎቶችን በመዝጋት ጋዜጠኞችን በማሰር እና ተቺዎችን በማፈን እንዲገኙ  አድርጓል። ዶክተር  አብይ የትግራዩን ግጭት “አረም” እና “ካንሰር” እያሉ  የሽምቅ ተዋጊዎችን ሲተቿቸው ቆይተው  ነበር።

 

 በሐምሌ ወር በጦርነቱ መሃል ዶክተር አብይ ፓርቲያቸውና ተቃዋሚ ፓርቲዎች  የተሳተፉበት ምርጫ አካሄዱ።ምርጫው  ምንም እንኳን በተሳካና ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ የተከናወነ ቢሆንም። በሎጅስቲክስ ጉዳዮች አንዳንድ ችግሮች የታዩበት ነበር።ከትግራይ ተወላጆች በስተቀር  በርካታ መራጮች በተሳተፉበት በዚህ ምርጫ   ብዙዎችን አሳምነው  ነው  ምርጫውን  ለማሸነፍ የቻሉት -  በእርግጥ  የዶክተር አብይን ፓርቲ ሕዝቡ  የመረጠው  ከምርጫው በፊት የታዩ አንዳንድ  መልካም ነገሮች  ስለነበሩ እነዚህን    የታዩ መልካም ነገሮችን የዶክተር አብይ ፓርቲ  ብልፅግና  ያስቀጥላል የሚል እምነት የመረጠውም ያልመረጠውም የኢትዮጵያ ህዝብ ስለነበረው ሁሉም መራጮች  ማለት ይቻላል  የዶክተር ዐብይን  መንግሥት  ነው የመረጠው።ይሁንና  ቀስ በቀስ ግን ካለፉት አንድ አመት በላይ የታዩት የኑሮ ሁኔታ ማሸቀብ፤የሥልጣን መባለግ ማለትም ሙስናና ብልሹ አሰራር የመሳሰሉት ችግሮች  ይበልጥ እየጎላ በሀገሪቱ ላይ መምጣታቸው በዶክተር  አብይ  የሚታዩ ችግሮችን ይቀርፋሉ  በማለት በራስ መተማመን የነበረውን ህዝብ አይደለም  ያልመረጣቸውን ብቻ ሳይሆን የመረጧቸውንም  ሳይቀር ብዙዎችን አሳዝኗል።

ምክንያቱም ዶ/ር አብይ ከሶስት አመት በፊት ቃል የገቡት የዲሞክራሲ ሽግግር እውን ይሆናል ብለው ትልቅ ተስፋ  በህዝቡ  ዘንድ ተሰንቆ  ስለነበረ  ነው።

 

አሁን ምን እየሆነ ነው?

 

 የግንባሩ መስመር ከሰሜን ወደ ኦሮሚያ አቅጣጫ በማስፋት የኦሮሞ  ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ ሽኔ) በርካታ  ዘርን ተኮር ያደረገ ጭፍጨፋ  እያደረገ ይገኛል።

 

 የኦነግ ሽኔ  ቃል አቀባይ ለሲኤንኤን በአንድ ወቅት እንደተናገሩት ከህወሓት ጋር በመሆን በሚያደርጉት ውጊያ ዋና ከተማዋን ለመያዝ ከሳምንት እስከ ወራቶች ድረስ ሊቀራቸው  እንደሚችሉና ከአዲስ አበባ 160 ኪሎ ሜትር (90 ማይል) እርቀት ላይ እንዳሉ  ኦዳአ ታርቢ  መናገራቸውን  የውጭ   ሚዲያዎች  ሳይቀሩ  ማስተጋባታቸውን ሰምተን ነበር ።

 

ይሁንና ወሬው ከሽብር ያልዘለለ ቢሆንም  በኦሮሚያ አካባቢ  እየፈፀመ  ባለው ሁኔታ ወገኖቻችን እያጡ ባለው የሰላም ማጣት ሁኔታ ግን አንጀቱ ያላረረ ኢትዮጵያዊ የለም  ለማለት አልደፍርም።   ።

 

 

 ''ወደ ዋና ከተማዋ የመግባት ጥያቄ "ከፌዴራል መንግስት ጋር ወደ ድርድር ለመግባት ምን እንደሚፈጠር ማየት ይቻላል።ድርድሩ በእኛ ኃይል ሚዛን ላይ የተመሰረተ ነው" በማለት የኦነግ ሽኔ  መሪ ኦዳአ ጫካ ሆኖ መፎከሩም  አልቀረም።ቡድኑ በጣም  ጥቅጥቅ ባሉ ከተማ ውስጥ ሳይቀር ቀጥተኛ ወታደራዊ ግጭትን ለማስወገድ በእኛ በኩልም ተስፋ  እናደርጋለን  ሲል ተናገረ።  

 

ዶክተር አብይ የመንግስታቸውን ጠላቶች "በደማችን እንቀብረዋለን “ ሲሉ  ቃል ገቡ ።

 የኤርትራ ከትግራይ እስከ አሁን አለመውጣት 

 

በህዳር 2020 በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ኤርትራ የኢትዮጵያን ጦር ለመደገፍ ወታደሮቿን ወደ ትግራይ ልካለች።አሁንም ጦሯ በትግራይ ክልል ይገኛል።

 የኤርትራም ሆነ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በተለያዩ ጊዜያት ይህንን በተመለከተ  የሚቀርቡ ዘገባዎችን አስተባብለዋል። በኤርትራ ወታደሮች በቡድን የተደፈሩ እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የጅምላ ግድያ በስፋት ቢነገርም።  ኤርትራ የነዋሪዎችንና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችን ውንጀላ አስተባብላለች።

 

 ኤርትራና ኢትዮጵያ ከ1998-2000 የድንበር ጦርነት አካሄደዋል።በወቅቱ የኢትዮጵያ መንግስት በህወሓት ስለሚመራ የበላይነት ነበረው።አሁንም ኤርትራ እና ህወሀት ጠላቶች ሆነው ቀጥለዋል።

 

 እ.ኤ.አ. በ 2018 የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን መጥተው ከኤርትራ ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራርመዋል - ይህ ድርጊት የኖቤል የሰላም ሽልማትን አስግኝቷል።  ነገር ግን በአብይ እና በህወሓት መካከል ያለው ግንኙነት አሁን መልካም  ይመስላል ።

 

 

 የአብይ መንግስት ህወሀትን በኢትዮጵያ ላይ የትግራይ ተወላጆችን የበላይነት ለማስከበር እየሞከረ ነው ሲል ሲወቅስ ህወሀት ግን አብይን ከስልጣን በላይ እንዳማከለና የትግራይ ተወላጆችን ጨቁኗል ሲል ይከሳል።

 

 ኤርትራ ከአንድ አመት በላይ በዘለቀው  በኢትዮጵያ እና በትግራይ አማፂያን መካከል እየተካሄደ ባለው  ጦርነት ተሳትፋለች በሚል ክስ ቀርቦባታል።አናዶሉም ሆነ ሮይተርስ  ይህን ዘገባ ከሌላ ወገን ማረጋገጥ  አልቻሉም።

 

 ኤርትራ ከ  በቀይ ባህር

 

 ጠረፍ 1,000 ኪሎ ሜትር (621 ማይል) ላይ ያለውን ግዙፍ ጂኦፖለቲካው  አቀማመጥ በዓለም ዘንድ ምቹና ተፈላጊ የሆኑ ስልታዊ ቦታዎችን ይዛለች።ሀገሪቷ የግዴታ ብሔራዊ ውትድራና አገልግሎት የምትሰጥ ም  ሀገር ነች።

የሂዩማን ራይትስ ዎች ባልደረባ ላቲሺያ ባደር “በብዙ መንገድ እየተነጋገርን ያለነው በዚህ አሁን ለሁለት ዓመታት በሰሜኑ ትግራይ ክልል በዘለቀው  ግጭት የተመዘገበውን የሰባዊ ጥሰት በተመለከተ ነው።አንዳንድ ጥቃቶችና በሰላማዊ ሰዎች ላይ ስለሚያደርሱት ተጽእኖ የሚያስተጋባ አዝማሚያዎች እየታዩ ነው” ስትል ተናግራለች።

 ያም ሆነ ይህ ከወያኔ ጋር  የተደረገው  የሰላም ስምምነት በኦሮሚያ ክልል ችግር እየፈጠሩ ካሉ ወገኖች ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ችግሮቻቸውን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እንዲፈቱ ማድረግ ያስፈልጋል። 

 

 በአሁኑ ወቅት የትግራዩ ቆመ ስንል በኦሮሚያ  ያለው  ግጭት እንደገና መፈንዳቱ የሚያሳዝን ነው።ጦርነት ለማንም አይጠቅምም  በተለይም በኦሮሚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም ይፈልጋል ።እንደገና  በጦርነቱ ምክንያት ህይወታቸው የተመሰቃቀለው ህበረተሰባችንን እንደገና  እንደ አዲስ መገንባት  እንጀምራለን  ብለን ስናስብ ሌላ የቤት ሥራ  ለመንግስታችን  መጥቷል።

 

 የኢትዮጵያ መንግስት የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና አንድነት መጠበቅ  ግዴታ አለበት። ስለዚህ የኤርትራ ጦር ወደ ድንበሩ ከምስጋና ጋር መመለስ አለበት።ምክንያቱም የትግራይ ዜጎቻችንን ሰላም መጠበቅም  ግዴታ አለበት።ሰላምና አንድነት ሁልጊዜ ከጦርነትና መለያየት እንደሚሻል  ለማንኛችንም  ግልፅ ነው።እግዚአብሔር ኢትዮጵያና ህዝቧን ከችግርና ከስቃይ ይጠብቅልን።ለዛሬው  በዚሁ አበቃው  ሰላም !