በትግራይ ውስጥ ዘረፋ፣ አስገድዶ መደፈር ተባብሷል፤በሌላ በኩል በኬንያ ..,.


 

 

ከወሰንሰገድ መርሻ (ጮራ ዘአራዳ)

 ፎቶ  የኬንያው አደራዳሪ  የቀድሞ  የኬንያ ፕሬዝዳንት ኬንያታና 

 

 

 በትግራይ ጦርነት በህወሓትና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል የሰላም ስምምነት ተደርሶ ወደ ተግባራዊነት የተሸጋገረ ቢሆንም ።በክልሉ የዘረፋ፣የአስገድዶ መድፈርና የማፈናቀል ዘመቻ እየተከናወነ መሆኑን 

 
  ፎቶ  በትግራይ ርዕሰ መዲና መቀሌ የሚገኘው የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ሀኪሞች በሰኔ ወር በከተማው ገበያ ላይ ከደረሰው አሰቃቂ የአየር ጥቃት በኋላ በፎቶው ላይ ይታያሉ ።
 
 
 

በሰሜናዊ ክልል የሚገኙ ነዋሪዎችና የሰብአዊ እርዳታ ሰጪ  ድርጅት ሰራተኞች ለኤ ኤፍ ፒ ገልፀዋል።

 

 

 ለሁለት ዓመታት የዘለቀውን ግጭት ለማስቆም  ህዳር 2 የሰላም  ስምምነት ከተፈረመበት ጊዜ አንስቶ ዕርዳታ ወደ ትግራይ በአሁኑ ወቅት እየገባ ይገኛል።የስልክ መስመሮች በከፊል ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው  እንዲመለሱ ተደርጓል። የክልሉ ርዕሰ መዲና የሆነችው መቀሌ ከብሔራዊ ኤሌክትሪክ አውታር ጋር  እንድትገናኝ  ተደርጓል

 

 ወደ ትግራይ መድረስ በጣም የተገደበ 

የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ውስን መሆን ነው።በዚህም የተነሳ  ጋዜጠኞች መሬት ላይ ያለውን እውነታ ከገለልተኛ ወገኖች ማረጋገጥ እንዳይችሉ አድርጓቸዋል

 

 

ነገር ግን ኤኤፍፒ ከትግራይ 

ስምንት ነዋሪዎችና የረድኤት ሰራተኞች ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ሰላማዊ ሰዎች ከደህንነትና ከሰላማዊ ሁኔታ ርቀው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።በተለይም የኤርትራ ወታደሮችና ከአጎራባች  ክልል የመጡ  የአማራ ክልል ታጣቂዎች በግድያ፣ አስገድዶ መድፈርና ሌሎች በደሎች ክስ ቀርቦባቸዋል።

 

 በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ በምትገኝ ሽሬ ከተማ በኤርትራና በአማራ ክልል ታጣቂዎች ወረራ ምክንያት በአካባቢው የፍርሃት ድባብ  ያንዣበበ ሲሆን ዘረፋና አፈና በስፋት መኖሩን አንድ ነዋሪ ገልጸዋል።

 

 የኢትዮጵያ የትግራይ ግጭት

 

 

በታህሳስ ወር አጋማሽ ላይ "ሽሬ የሙት ከተማ ናት ነበረች ማለት ይቻላል" ሲሉ አንድ የትግራይ ተወላጅ  ለኤኤፍፒ ተናግረዋል። በክልሉ የሚኖሩ ሲቪሎች ከፍተኛ ምግብ እጥረት፣ የነዳጅና የገንዘብ እጦት ምክንያት እየተሰቃዩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

 

 

 "ሴቶች ጾታዊ ጥቃትን በመፍራት ቤታቸውን ለቀው  ወደ አደባባይ መውጣትን ይፈራሉ።"

 

 - ዘረፋ አፈና አስገድዶ መድፈር -

 

  ቃለ መጠይቅ  ኤኤፍ ፒ ያደረገላቸው  ለደህንነት ሲባል ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቀ በሽሬ የሚኖሩ የእርዳታ ሰራተኛ ድርጅታቸው 11 የአስገድዶ መድፈር ጉዳዮችን መመዝገቡን  ገልጿል

 

 

 ከህዳር  ወር መጨረሻ እስከ ታህሣሥ መጀመሪያ ድረስ በትግራይ ዙሪያ በስፋት ተዘዋውሮ ከኤርትራና ከአማራ ኃይሎች ጋር በክልሉ ተገናኝቶ ያያቸውን ነገሮች ነው የተናገረው። ይህ አስተያየቱ በሌሎች የረድኤት ሠራተኞች የተደገፈ  አስተያየት  እንደሆነም   ኤኤፍፒ  አረጋግጧል

 

 በህዳር ወር በተደረገው   ሌላ ቃለ ምልልስ ሽሬ ላይ "የአማራ ሃይሎች ቤትና የመንግስት መስሪያ ቤቶችን በመዝረፍ እንዲሁም  በዋነኛነት ወጣቶችንና ሴቶችን በማፈን ላይ ናቸው" ብሏል።

 

 “የኤርትራ ወታደሮችም ወጣቶችን እየዘረፉ  ይዘው መሄዳቸውን ቀጥለዋል፤ የኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል እየተመለከተ ነው እንጂ ጣልቃ እየገባ ድርጊቱ እንዲቆም እያደረገ አይደለም” ሲሉም አክለዋል።

 

 በአድዋ የሚኖሩ አንድ ነዋሪ፣ ኤ ኤፍ ፒ በዚህ ሳምንት እንደተናገሩት  የምታውቃቸው የሰባት ቤተሰብ አባላት በማዕከላዊ ትግራይ ከተማ ዳርቻ በኤርትራ ወታደሮች መገደላቸውን ተናግረዋል።

 

 ባለፈው ሳምንት የመንግስታቱ ድርጅት የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ቴዎድሮስ አድሃኖም ገብረእየሱስ በሰጡት መግለጫ  አጎታቸው “በኤርትራ ጦር ከተገደሉት 50 መንደርተኞች መካከል አንዱ  ነበር” ብለው  እንደነበር  አይዘነጋም

 

የኢትዮጵያ መንግስትና ህወሓት የ ትግራይ የሰላም ስምምነት በፕሪቶሪያ ህዳር 2 ቀን  የተፈራረሙ  ቢሆንም  የሰላሙ ስምምነት  ተግባራዊ  አልሆነም  በማለት  የትግራይ ተወላጆች  እየገለፁ  ነው  የሚገኙት 

 

 ከአዲስ አበባ መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነቱን የፈረመው የክልሉ ገዥ ባለስልጣን ህዝባዊ ወያ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የኤርትራን ሃይሎች የጅምላ ጭፍጨፋ እየፈፀሙ  ነው  ሲልም  ወንጅሏል።

 

 በሰላማዊ ድርድር ላይ የኤርትራም ሆነ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ያልተሳተፉ ሲሆን ስምምነቱ የኃይላቸውን መገኘትም ሆነ የመውጣት ቃላቸውን የተናገረ ነገር የለም።

 

 

 ሁለቱ ወገኖች በግጭቱ ውስጥ ግንባር ቀደም ተዋናዮች ሲሆኑ የኢትዮጵያን ጦር በመደገፍ አስከፊ የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈፅመዋል በሚባል ሁኔታ ውንጀላ ቀርቦባቸዋል።

 

 ኤርትራውያን ከህወሓት ጋር ያላቸው ጠላትነት ከ1998-2000 ዓ.ም  በኤርትራ ኢትዮጵያ መካከል በተካሄደው ደም አፋሳሽ የድንበር ጦርነት ባካሄዱበት ወቅት ነው። በወቅቱ የትግራይ ፓርቲ ህወሓት የብሄራዊ መንግስቱን የበላይነት በያዘበት ወቅት እንደነበር  አይዘነጋም

 

 የአማራ ብሄርተኞች በበኩላቸው  የምዕራብ ትግራይን ለም መሬት ይገባኛል ጥያቄ ለረጅም ጊዜ ሲከራከሩ ቆይተዋል፣ ግዛቱም በህዳር 2020 ግጭት ተቀስቅሶ በአማራ ሃይሎች  ዳግመኛ  መያዙ  ይታወሳል

 

 - 'ፈራን' -

 

 በታህሳስ ወር መጀመሪያ ላይ በደቡብ ምዕራብ ትግራይ የሚገኘው የማይ ፀብሪ ነዋሪ የከተማዋ የአማራ ባለስልጣናት "የትግራይ ተወላጆችን እያፈናቀሉና ንብረታቸውን እየዘረፉ ነው" ሲሉ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል።

 

 " ተጨንቀናል፣ ለደህንነታችንና ለወደፊት ህይወታችን እንሰጋለን" ብለዋልም

 

 "አዲሶቹ አመራሮች የአማራ ብሄር ተወላጆች ናቸው ። '' የሚሉት ነዋሪዎች  አዲሶቹ ባለስልጣናት ''አዲስ ለመጡ ሰፋሪዎች መታወቂያ መስጠት ጀምረዋል" ብለዋል ።

 

 

 

 ባለፉት ሳምንታት ምዕራብ ትግራይን የጎበኘው የሽሬ ተወላጅ የሆነው የእርዳታ ሰራተኛ ''የአማራ ሰፋሪዎች በአካባቢው መድረሳቸውን አረጋግጦ የትግራይ ተወላጆች ግን ወደ ሌላ ክልል እየተፈናቀሉ ወይም ወደ እስር ቤት እየገቡ ነው '።'' ብሏል።

 

 የሰሞኑ ውንጀላ በተመለከተ በአሜሪካ መንግሥት በምዕራብ ትግራይ  ተወካይ ከጎርጎርጎሮሳዊው 2021 ዓ.ም ጀምሮ  እየተፈፀመ  ያለውን ድርጊት ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ቢሆንም በአማራ ባለስልጣናት በኩል ውድቅ  ተድርጓል።

 

 በአዲስ አበባ የሚገኘው የፌደራል መንግስትም ሆነ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ከኤኤፍፒ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ  አለመስጠታቸውን ኤኤፍፒ  ገልጿል

 

 - 'የተሰበረ እና የተጨነቀ'
-

 

ህወሀት በዚህ ወር ብቻ  65 በመቶው  የሚሆኑ ተዋጊዎቹ ትጥቃቸውን በመፍታት ከጦር ሜዳ “ተፈናቅለዋል” ነገር ግን መቀሌ አሁንም በህወሓት ታጣቂ ቁጥጥር ስር እንዳለች ተናግሯል።<

 

 

 

 

 

 

 በሌላ በኩል ''በአይደር ሪፈራል ሆስፒታል፣ ሁኔታው ​​​​ከዚህ በፊት ከነበሩት 18 ወራት ጋር ተመሳሳይ ነው ።'' ሲሉ የመቀሌ ዋና የህክምና ተቋም ከፍተኛ ባለስልጣን አቶ ክብሮም ገብረስላሴ ተናግረዋል።

 

 "በጀት የለም፣ የምናገኛቸው መድሃኒቶች ከአንድ እስከ ሁለት ቀን የሚደርሱ ከልገሳዎች የተገኙ  ብቻ ናቸው" ሲል በዚህ ሳምንት ለ ኤኤፍፒ ተናግረዋል።

 

 በመቀሌ የሚገኘው የሰብአዊ ሰራተኞች በዚህ ወር ለኤኤፍፒ እንደተናገረው ነዋሪዎቹ በሁኔታው የዘኑና የተጨነቁ መሆናቸውን ገልፀው  በአጠቃላይ የምግብ፣ የመድሃኒትና የመኖሪያ ቤት እጥረት እንዳለ ተናግረዋል።በእርግጥ የእርዳታ ኮንቮይዎች  ወደ ክልሉ መግባታቸውን ቢቀጥሉም።

 

 በታህሳስ  ወር መጀመሪያ ላይ ከሽሬ ወደ አድዋ የተጓዘ ሶስተኛው የእርዳታ ሰራተኛ በተቀረው ትግራይ ያለው ሁኔታ የተሻለ አልነበረም ብሏል።

 

በሰሜን ትግራይ ዙሪያ "በጣም አሳሳቢ የሆነ የመድሃኒት፣ የንፅህና እጦት አለ" ሲል ለኤኤፍ ፒ ተናግሯል።

 

 ነገር ግን ሁከትን መፍራት ዋነኛው ስጋት ሆኖ ቀጥሏል።

 

 የሰካም ስምምነቱ  የትግራይ ተወላጆች "ባዕድ ሃይሎች (ኤርትራውያን ማለታቸው ነው   ) ለቅጣት በማጋለጥ እንዲገደሉ አስደርጓል" ሲሉ ክብሮም  ተናግረዋል።

 

 "ሁሉም ጦርነቱ ሰልችቷቸዋል፣ሰላም ህዝቡ በጣም የሚፈልገው ነው።ነገር ግን ሁሉም የሚያሳስበው.። የሰላም ስምምነቱ በሰው ልጆች ላይ ለሚፈጸሙ ወንጀሎች ሁሉ መደበቂያ እንዳይሆን ብቻ ነው ።'' ሲል ተናግሯል።

 

 

 ባለፈው ረቡዕ ተጀምሮ ዛሬ በተጠናቀቀው  የኬንያ ናይሮቢው ስብሰባ "ሰላምን መውደድ ማለት ፍትህን መተው ማለት አይደለም።" በማለት ተገለፀ።

 

የኢትዮጵያና የትግራይ ባለስልጣናት የሰላም ስምምነትን በሚገመግሙበት ሁኔታ ላይም  ተስማምተዋል።

 

 

የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከዶክተር አልሃጂ ሳርጆህ ባህ የግጭት አስተዳደር ዳይሬክተር ጋር በመሆን በናይሮቢ በኢትዮጵያ እና በትግራይ መካከል በተደረገው ሁለተኛው የአዛዦች ስብሰባን  መርተዋል።

 

 

 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስት ከፍተኛ አዛዦችና የህዝባዊ ወያ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከፍተኛ ተወካዮች በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል ለሁለት አመታት የዘለቀውን ጦርነት ለማቆም በህዳር ወር መጀመሪያ ላይ የተፈራረሙትን የሰላም ስምምነት አፈፃፀም  ለመገምገም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተስማምተዋል።  .

 

 ይህም በአፍሪካ ህብረት የሚመራው ቡድን በደቡብ አፍሪካ የተፈረመውን ስምምነት በጥቂት ቀናት ውስጥ መከታተልና መገምገም እንዲጀምር መንገድ ከፋች ነው ተብሏክ

 

 ይህ የተገለጸው የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ የፓናል አባል እየተካሄደ ያለውን የሰላም ጥረት አስተባባሪ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በናይሮቢ በሰጡት የመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ከፌደራል መንግስት የተወከሉ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ባለስልጣናት ለመጨረሻ ጊዜ ከህወሓት ተወካዮች ጋር እየተገናኙ ባሉበት ወቅት ነው።  

 

የስምምነቱ ዋና ዋና ነገሮች በሙሉ በመሬት ላይ እየተተገበሩ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የአፍሪካ ህብረት ቡድን ሙሉ ኃላፊነት  ተሰጥቶት ሁሉንም  ነገር እንዲመለከት ተስማምተዋል።  ሁለቱም ወገኖች ሙሉ ቁርጠኝነት ስላላቸው  አንዳንድ ተግዳሮቶች እንደሚፈቱ እርግጠኛ ነኝ” ሲሉ የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ሚስተር ኬንያታ ተናግረዋል።

 

 ሚስተር ኬንያታ ጥረቱን እየመሩ ያሉት በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ተወካይና የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት የጠቢባን ቡድን አባልና የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶ/ር ፉምዚሌ ምላምቦ-ንጉካ ጋር በመሆን ነው።

 

የተፈረመው የሰላም ስምምነት አካል ሁለቱም ወገኖች ጦርነታቸውን እንዲያቆሙ፣ ሁሉም የውጭ ኃይሎች የትግራይ ክልልን ለቀው እንዲወጡ፣ እንደ ባንክ፣ ስልክና ውሃ ያሉ አስፈላጊ የህዝብ አገልግሎቶችን እንዲቀጥሉ እንዲሁም ሁለቱም ሰብአዊ ርዳታ በቀላሉ እንዲዳረስ እንዲጀመሩ  መፍቀድ  እንዳለባቸው  ተናግረዋል

 

 ሚስተር ኬንያታ በመቀሌ የሚካሄደው ስብሰባ እነዚህን ድርጊቶች መፈጸሙን ያረጋግጣል ብለዋል።

 

 "ሰነዶች አንድ ነገር ነው፣ አሁን የምንፈልገው ሊደርሱ የሚችሉ ናቸው ለዚህም ነው ወደ መቀሌ የምንሄደው ለዚህ ነው እኔ የምለው፣ ሲገናኙ የነበሩት ከፍተኛ የጦር አዛዦችና የሁለቱም ፓርቲ ከፍተኛ ተወካዮች መካከል ያለው መልካም የስራ ግንኙነት የሚደነቅ ነው።  እኛ ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ  እየሄድን እንደሆነ እርግጠኞች ነን” ብለዋል ሚስተር ኬንያታ።

 

 ፓርቲዎቹ በገለፃው ላይ ባይገኙም ሚስተር ኬንያታ በመቀሌ የስምምነቱ አፈፃፀም ሂደት ላይ ግልፅ መግለጫ ለመስጠት እድሉን እንደሚያገኙ ተናግረዋል።

 

 'አስደናቂ እድገት'

 

 "ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ በድርድሩ መሃል ላይ ለነበሩት ሁለቱም ወገኖች በጣም ደስተኞች ነን ስለዚህ እናመሰግናለን።  እጅግ በጣም ጥሩ እድገት እያስመዘገብን ነው ዛሬ ሌላ የመደመር ቀን ነው ሁሉም ተከታታይ እርምጃዎችና ተግባራት ትግራይን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመመለስና የኢትዮጵያን ሰላም ለማምጣት ያለመ ነው ''ሲሉም አክለዋል።

 

በስብሰባው ትጥቅ የማስፈታት ፣የማስወገድና የመልሶ ማቋቋም ሂደት አፈፃፀም ላይም ተወያይቷል።

 

 ሚስተር ኬንያታ እንዳሉት የቡድኑ ተስፋ ኢትዮጵያ የ2023 የፈረንጆቹን ገናንና አዲሱን አመት በሰላም እንዲያከብሩና  የሀገሪቱንና የዜጎችን የወደፊት እጣ ፈንታ በተመለከተ ትልቅ ተስፋ ያለው አዲስ አመት  ይሆናል ብለው  እንደሚያስቡ  ተናግረዋል 

 

 ለሁለት ዓመታት በዘለቀው ጦርነት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሕይወታቸውን አጥተዋል፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደግሞ ተፈናቅለዋል፣ አንዳንዶቹ ወደ ጎረቤት ሱዳን በመሸሽ የተቀሩት ደግሞ ሰብዓዊ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

 

 የእርዳታ ሰራተኞችን መገደል ጨምሮ በሁለቱም ወገኖች በአሁኑ ወቅት የተፈፀሙ ያሉ አሰቃቂ የመብት ጥሰቶችና ለተጎጂዎች ፍትህ እንዲሰጡ በተለያዩ የሰብአዊ መብት ኤጀንሲዎች  ክስ  ሲቀርብ  መቆየቱ  አይዘነጋም ።