ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለምን በኢትዮጵያውያኖች ጭምር ተቀባይነት እያጡ መጡ?


አይቀበሉትም እንዲያውም አሁን በክልሉ ለተፈጠረው የሰላም ችቦ መብራት መንግስታቸው ግንባር ቀደም መሆኑን በመጥቀስ አብዛኛዎቹ የሚሰነዘሩትን አስተያየቶች ና ትችቶች  ውድቅ  ያደርጋሉ በሰሜን የሰላም ሁኔታው  እሰይ ቢያስብልም  በኦሮሚያ ክልል ያለው ጦርነት ሌላ ችግር ሆኖ መጥቷል።  

 

 

ብዙ ጊዜ፣ ይህ አይነቱ ነቀፋዎች በሚሰነዘርባቸው ወቅት ዶክተር አብይና ደጋፊዎቻቸው አካባቢ ብስጭት ይታይባቸዋል።በግል ጥቃቶች ወይም በሴራ ንድፈ ሃሳቦች ውስጥ የተሳተፉትን አሜሪካና ምዕራባውያንን በድርጊቱ ውስጥ መኖራቸውን የሚገለጥ ሲሆን ሁለቱም ወገኖችም  ማለት የፌድራል መንግሥትና የህወሓት ወገኖችም ሆኑ እራሳቸው ዶክተር አብይም ቢሆኑ  ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በወቅቱ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት  እየሻከረ መምጣቱን  ያሳያል።  በዚህም የተነሳ ሌሎችን አካሎችን መውቀስ የሚያረካ ሊሆን ይችላልነገር ግን ድርጊቶቹ ያልበሰለ እንጭጮች ናቸው ። ዶክተር አብይ የዓለምን ትተው በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተቀባይነት እንዴት እንዳጡ  ማወቅ ከፈለጉ ግን ከዚህ በፊት ለህዝባቸው  ቃል የገቡበትንና እየሄዱበት ያለውን  አካሄድና እስካሁን የወሰዷቸውን የራሳቸውን የእርምጃ ተግባር ብቻ ማጤን  እንደሚኖርባቸው   አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች  ይናገራሉ  

 

ዶክተሩ ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ አይደሉም  በማለትም ይተቻቿዋል። በእርግጥ አሜሪካዊ ዲፕሎማት ሚካኤል ሩቢን  ከወራት በፊት  ከኢትዮጵያ ካቢኔ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ተቀምጠው የመወያየት ዕድል ማግኘታቸውን ይገልጻሉ።የዶክተር 

አብይ መንግስት ካለፉት ሁለት አመታት የእርስ በእርስ ጦርነት ምን ትምህርት እንደወሰደ ለመጠየቅ እድሉን አግኝቼ ነበር። ብለዋል። ከሁሉም በላይ በግጭቱ ውስጥ ሁለት ዋና ዋና አካላት አሉ,ስህተቱ በዶክተር አብይ ጠላቶች ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው ማለት አይቻልም።ዶክተር  አብይ እውነት ከጎናቸው ነው ብለው ቢያም እንኳን ኃላፊነት የሚሰማው  የፖለቲካና የወታደራዊ አመራር በየጊዜው  ስልቶችን መገምገምና ማስተካከል አለባቸው።  ዶክተር አብይ ግን እንደዚህ አይነት አይደሉም በማለት ይወቅሷቸዋል ። '' ዶክተሩ ቀላል ምክንያት  ላላቸው  ስሕተቶች  አይቀበሉም። እየተባሉም ይተቻሉ።

 

 

 ይህ አባባላቸው  ብዙ ተለዋዋጭ  ሁኔታዎችን ሊያመለክት ይችላልየትኛውም ነገር  ለኢትዮጵያ አይጠቅምም  በመጀመሪያ፣ ዶክተር ይ ትክክለኛ የሆነውን መንገ ስህተት መሆኑን በትክክል ሊያውቁ አይችም። በዚህም የተነሳ ዶክተር ዐብይ ሀገሪቱ ያለባቸው  ችግር  ውስብስብነት ሊኖረው ይችላል ።ይህንን ውስብሰብ ችግር ለብቻቸው ለመፍታት ምንም ማድረግ እንደማይች ያምኑ ይሆናል ሁለተኛ ደረጃ ዶክተር ይ በዙሪያው ላይ ያሉትን ወገኖች ራሳቸውን ሳንሱር ስለማያደርጉ  እራሱ የሚናገሩት  ነገሮች  ያሸብራቸዋል።አሊያም  እነዚህ በዙሪያቸው ያሉ ወገኖች አስተሳሰባቸው ከአለቃቸው ጋር ቃረን ይችላል ብለው ይፈራሉ።  በሌላ መልኩ የሳውዲው አልጋ ወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን የዋሽንግተን ፖስት አምደኛና የሙስሊም ወንድማማች ሁድ አክቲቪስት ጀማል ካሾጊ እንዲገደል ትእዛዝ ሰጥተዋል በተባሉበት ወቅት እንደዚህ አይነቱ ሁኔታ ተለዋዋጭነት ያለው ሊሆን ይችላል የሚል የፍራቻ አይነት በውስጣቸው  አለው ።  ብዙ የረዥም ጊዜ የኢትዮጵያ ጎብኚዎች ኢትዮጵያ በደርግ ጊዜ እንደነበረው አይነት ያጋጠማት ነገር አሁንም መቃረቡን የህዝብ ፍራቻው ከፍተኛ መሆኑን በመግለፅ ይህ አይነቱ ሁኔታ እንዳይገጠም ማስጠንቀቂያ  ከወዲሁ ሊሰጥ ይገባልም  ይላሉ

 

 ለዶክተር አብይ ስም  መፈራረስ አስተዋፅዖ ያደረገው የኢትዮጵያ መንግስት ለትችትና ለሚያሳየው ዲፕሎማሲ ውጤታማ ያልሆነ ምላሽ በመስጠቱ ነው።  ብዙ ጊዜ፣ ዶክተር አብይና አገዛዛቸው በህዝብ ያገኙትን የድምጽ መጠንን በተጨባጭ  ወደ ሚፈልጉበት የአመራር ሂደት እንዲጓዙ ሊያደርጋቸው ይችላል ሲሉም ይናገራሉ ።  በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዲፕሎማቲክ እረገድ ያለው ተሳትፎ ወይም የዲፕሎማቶቹ ኢትዮጵያ ላይ ያላቸው ዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ዝቅተኛ እንደሆነ ይጠቁማሉ ።

 

 የዶክተር አብይ መንግስት በሙያ ከመሰማራት ይልቅ በድሮኖች መመካትን ይመርጣል።  እንደነዚህ ያሉት ዘዴዎች ሁል ጊዜ ወደ ኋላ ይመለሳሉ።  ለሶማሊያ ሞሃመድ ፋርማጆ ወይም ለቱርክ ሬክ ማቻር ይህ ሁኔታ አልሰም።  ይልቁንም መሪዎቹ ራሳቸው ደመወዝ የሚከፈላቸው  ምብ የሚባሉትን ፍርድ ቤቶች ከህጋዊ አስተያየቶች ጋር ማደናገር ሲጀምሩ የኦንላይን ፖለሚክስ (በአንድ ሰው ወይም በሆነ ነገር ላይ ጠንካራ የቃል ወይም የጽሑፍ ጥቃት)

 ራሳቸውን የሚያሸንፉ አድርገው  ሲመለከቱ ቆይተዋል።  ድሮኖች አልፎ አልፎ የፖሊሲ አውጪዎችን አስተያየት ይቀየራሉ ምክንያቱም  ኢላማ የሆኑ ቦታዎችን እንኳን ድሮኖቹ ቢመቱ ለፖለቲካ መጠቀሚያ ተብለው  ሰላማዊ ሰዎች ሞተዋል ተብለው ዓለም አቀፍ ተፅእኖዎች  እንዲፈጠሩ ያደርጋል።ይህ ደግሞ ፖለቲካ መጠቀሚያ  በማድረግ  ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ላይ የበላይነት  ውስጥ  አመራሩ እንዲገባ ሊያደርገው ይችላል 

 

 የኢትዮጵያ መንግስት የማይወዷቸውን አስተያየቶች ለመቅጣት ኖችን ቢጠቀምም ሀሳቡን ከመቀየር ይልቅ ጉዳዩን ማለትም  የሰላሙን ሁኔታ ሊያናጋው  ይችላል ።  የዶክተር አብይ መንግስት በአላማቸው ፍትህና በዲሞክራሲ  የሚያምኑ ከሆነ፣ ዝም ብሎ ከመሳደብ ይልቅ በፋክት፣በሪያሊቲና በሎጂክ በዙሪያቸው ያሉትን  በአጠቃላይ ለማሳመንና  ተቃራኒዎቻቸውን በሙሉ በዓለም ፊት ለማሸነፍ እውነታዎችን መጠቀም መቻል አለባቸው ።  ምናልባት ዶክተር  አይ የሚያቀርቡት አስተያየቶች ዲፕሎማቶችን፣ የውጭ  ተንታኞችንና  ምሁራንን ለማጥቃትና እንደተለመደው በኦፊሴላዊ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ላይ ሊጠቀሙ እንደሚች ያም ይሆናል።  

ይሄ ማንንም አይጠቅምም ማንንም አይጎዳም ።  በመንግስት የሚከፈላቸው ሚዲያዎች ድሮኖች  የእሳት ኳሶችን ሲወረውሩ የታለሙ ኢላማዎችን ተመታ ከማለት በስተቀር ሌላ ማለት አይችሉም።

 

 

የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶችና ሚኒስትሮች በሙሉ  ቢሆኑ በእሳቸው  ስለሚመሩ ስህተቶች እንኳን ቢኖሩ ለምን የሚል ጥያቄም  አያነሱም ።  

 

 ምናልባት የዶክተር አብይ በሰሜን ያለው ትህዛዝ  የሚቀጠል  ከሆነ ዲፕሎማሲያዊ ስልት አንዱ ምክንያት ኢትዮጲያዊ ላልሆኑ ሰዎች ያላትን አስፈላጊነት አጋንኖ የሚያሳይ አስተሳሰብ ሊሆን ይችላል።  በመሰረቱ ዶክተር አብይ ከእሳቸው  ጋር ሙሉ በሙሉ የማይስማማውን ሁሉ እንደ ጠላት ነው የሚመለከቷቸውም  እያሉ  ይተቿቸዋክ።  የቱርክ ፕሬዝዳንት የሆኑትን የኤርዶጋንን ልምድ  በመከተል እሳቸውም በኢትዮጵያ ባሉት ላይ ተቃራኒ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎችን  ከኃላፊነት ቦታዎች ላይ እንደሚያነሷቸው  ነው የሚነገረው ።  ምዕራባውያን በአንድ ወቅት ኤርዶጋንን እንደ ልከኛና ድልድይ ሰሪ አድርገው አይተውቸዋል።  ነገር ግን ለዓመታት ቀላል ትችቶችን እንኳን ሲቀርቡባቸው  ከአሸባሪ ቡድኖች ጋር ግንኙነት ለመመስረት ማስረጃ በማቅረብ  ውድቅ  ሲያደርጉ  ይስተዋሉ  ነበር ።  የዶክተር አብይ ተቺዎች፣ ዲፕሎማቶችና ቀደምት  መሪዎቹ ሳይቀሩ ዝም ከማለት ይልቅ እውነታውን መያዙን መጠራጠር ጀመረዋል።  በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ  አገር ብዙ ሰዎችን በማናጋት ዛሬ በራሳቸው ቤተሰብ ላይ ብቻ መመካት  ጀምረዋል  እየተባሉም   ይተቿቸዋል

 

 “ከኛ ጋር የሚቃረን” አስተሳሰብን ለሀገር ውስጥ ፖለቲካ መጠቀም ትክክል አይደለም።  የዶክተር አብይ ደጋፊዎች በትግራይ ጦርነት አካሄዱ ላይ ትችት ሲሰነዘርባቸው  ከህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሀት) ጋር መተሳሰር ማለት ነው በማለት ይናገሩ ነበር።  ደጋፊዎቻቸው በዶክተር አብይ ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶች በተሰነዘረ  ቁጥር ለትግሬዎች ማዳላት ዘረኝነት ነው ማለታቸውም አልቀረም ነበር። 

ይህ  ሁኔታ  ሲቀረፍ ደግሞ የኦሮሚው ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱ ሁላችንንም  አሳስቦናል።አሁንስ  ምን ይባል ይሆን ? እንደዚህ  ማለቱ ዶክተር አብይን ምንም  አይጠቅማቸውም።  ለምሳሌ በሩሲያ ላይ አሜሪካና ምዕራባውያን ለዩክሬን የሚያደርጉትን  ድጋፍ በፀረ-ነጭ ስሜት ተነሳስተው እንደሆነ የሚጠቁም ያህል ምክንያታዊ  ሁኔታዎች  እየታዩ  ነው ።

 

 

ግራ የሚያጋባ ፕሮፓጋንዳ ከእውነታው  ጋር

 

 ያለፈው ቢያልፍም ዶክተር ይ በአጠቃላይ አለም በተለይም ዋሽንግተን ስለ ህወሓት አማፂ ቡድን አሸባሪ ቡድን በማለት መግለጻቸው አባባሉን አለመቀበላቸው  አበሳጭቷቸው ነበር  ።  

ወያኔ አዲስ አበባ አልቃይዳ ደግሞ ለዋሽንግተን አሸባሪ  ነው  የሚለው  መከራከሪያ ነጥብ ሊያስኬድ  ይችላል። በተመሳሳይ ኦነግ ሸኔም እንደዚሁ ለኦሮሚያ ክልል ብቻ ሳይሆን  ለአዲስ አበባችን ጭምር አሸባሪ  መሆኑን እያየን ነው።በተለይም በአምባገናናዊነት  እ.ኤ.አ. ከ1991 እስከ 2018 ባለው ጊዜ ውስጥ ህወሓት የሀገሪቱ አውራ ፓርቲ  ሆኖ  ሲመራ ቆይቶ በኢትዮጵያውያን ላይ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ያለፈን ፓርቲ እንክ እንትፍ ብሎ እንዳልተፋው  አሁን ከዶክተር ዐብይ መንግሥት ይሻል  ነበር በማለት መናፈቅ  ጀምሯል።  ይህ መሆን የሌለበት ነገር ነው ።ዶክተሩ የራሳቸውን አመራር እንዲፈትሹም  የሚያስደርግ ነው።

 

  ከኤርትራ አምባገነን ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ሰላም መፍጠር አንድ ነገር ነው።  ከእሱ ጋር በንቃት መተባበር ግን ሌላ ነገር ነው።ዶክተር  አብይ የኢትዮጵያን የውጭ ወረራ የባረኩት ይመስላል  ።  ኢሳያስ ከኢትዮጵያ ግዛት ለምን እስካሁን አልወጣም ? ይህ የአብዛኛው ጥያቄ ነው።ኢሳያስ ከቀድሞው የሶማሊያው ፕሬዝዳንት መሀመድ ፋርማጆ ጋር ያለው ጥምረት ከአልሸባብ ጋር በመተባበር በህገወጥ መንገድ የራሱን የስልጣን ጊዜ ለማራዘም ሲጥር የነበረው ያን ያህል ህወሓት ማጥላላት  ላይ ነው 

የሚገኘው።   በቀላል አነጋገር፣ የኢሳያስ ጥላቻ ወደ ወንጀለኞች እቅፍ አድርሶታል።  ኢሳያስ የውጭውን ዓለም ተጠያቂ  ሲያደርግ  ይስተወላል።ወታደሮቹ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ገብተው በር ፣መስኮት፣ ወንበር ሳይቀር እየዘረፉ  በመኪና እየጫኑ ሀገራቸው  ሲልኩ ዝም ብሎ መመልከት ከማሳፈር አልፎ የሚያሳዝን ነው።ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ  የኑሮ ውድነት፣ሙሰኝነት፣ሥራ አጥነት በየቀኑ እየጨመረ ነው።የኑሮውን ሁኔታ ስንመለከት ሌላውን ትተን ዳቦ ኢትዮጵያ ውስጥ ገንዘብ ያለው ካልሆነ በስተቀር የሌለው ሰው መግዛት አቅቶት ከሸገር ዳቦ ቤት አለቀ እየተባለ ሀዝኖ ሲመለስ እያየን በአንፃሩ በጦርነት ያለችው ዩክሬን ስንዴ እንካችሁ ብላ ስትልክን።በአንፃሩ እኛ ደግሞ  ስንዴ ወደ ኬንያ ኤክስፖርት ማድረግ መጀመራችን  የሚያስኬድ አይደለም።ዶላር ካስፈለገ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ኢኮኖሚስቶችን ሰብስቦ ምን ብናደርግ ይሻላል ብሎ  መጠየቅ የሚሻል ይመስለኛል።ገበያን ለማረጋጋት በሚል ሁኔታ ቅዳሜና እሁድ የተጀመረው በየአካባቢው  እየተሸጠ  ያለው የአትክልትና የሸቀጣ ሰቀጦች ዋጋ ስናየው ከነጋዴው ጋር ብዙም የተለየ አይደለም። እንዲያውም ሸማቾች ጋር ያለው የዋጋ ሁኔታ ሲታይ መርካቶ ወይም አትክልት ተራ ጋር ካለው  ሲነፃፀር በፍጹም ተቀራራቢ አይደለም።እንዲያውም የመርካቶ ያለው ዋጋ በአብዛኛው  ይሻላል።ለምሳሌ ሶፍት ፔፐር መርካቶ በ 25  ብር ይገኛል።ሸማቾች ከ33  ብር በላይ ነው።ብዙ ዕቃዎችን እያነፃፀርን መናገር እንችላለን።ለዚህም ነው ሸማቾችና ቅዳሜና እሁድ ብለው የሚሸጡ አካሎች  ጋር ያለው ዋጋ መርካቶ ካለው  አከፋፋዮች  ዋጋ ጋር ሲነፃፀር ዋጋውን ማረጋጋት ሳይሆን የዋጋ መናርን እየተመለከትን ነው ያለነው።ይህዝብን ፍቅር እንደበፊቱ ማግኘት ከፈለጉ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶክተር ዐብይ  እራሳቸውንና ኃላፊነት ያሰቀመጧቸውን  ሰዎች እንደገና ሊፈትሹና ሊገመግሙ  ይገባል እላለው።አበቃው ! ክብረት ይስጥልኝ።q