በጃፓን የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው የውጭ አገር ዜጎች ለህይወታቸው ይፈራሉ


በጃፓን የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው የውጭ አገር ዜጎች ለህይወታቸው  ይፈራሉ 

 

ሮድሪግ  ማይላርድ  NHK 

 

ከወሰንሰገድ መርሻ (ጮራ ዘአራዳ)

(ደራሲ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሀያሲ)

በጃፓን የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች ለሕይወታቸው አስጊ ነ ሁኔታዎች ውስጥ ይኖራሉ።የህዝብ  ጤና አጠባበቅ አያገኙም።  ከመካከላቸው አንዱ የሆነው የኩርድ ታዳጊ ወጣት ሐመድ የልብ ቀዶ ጥገና ያስፈልገዋልነገር ግን እሱና ቤተሰቡ ምንም አይነት ኢንሹራንስ የሌላቸው በመሆኑ በጭንቀት ውስጥ  ይገኛሉ።

 አሚጎስ በትልቁ ቶኪዮ አካባቢ ኢንሹራንስ ለሌላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች የህክምና እርዳታ የሚሰጥ የድጋፍ ቡድን ነው።  ዋና ዳይሬክተር ናጋሳዋ ማሳታካ  ይባላሉ።የስደተኛ ማመልከቻቸው ውድቅ ከተደረገባቸው መካከክ  ሐመድና ቤተሰቡ ጋር በመደበኛነት  ይገናኛሉ።  ይህም ማለት የመኖሪያ ፍቃድ  አጥተዋል ስለዚህ የሕክምና ኢንሹራንስ ስለሌላቸው።ለማንኛውም  የሕክምና ወጪዎች መሐመድ ለእሱና ለቤተሰቡ ከኪስ መክፈል አለበት።

የድጋፍ ቡድኖች እነሱን ለመርዳት ደፋ ቀና ይላሉ 

የሰሜን ካንቶ የህክምና አማካሪ ማህበር ዋና ዳይሬክተር ናጋሳዋ ማሳታካ እንደሚሉት "ስልኬ ያለማቋረጥ ከጠዋት ጀምሮ ሙሉ  ቀን ይጮሀል በማለት ምን ያህል ስደተኞችን ለመርዳት ጊዜ እንኳን እንደሌላቸው  ይናገራሉ

 የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ብዙ የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖሪያ ፍቃድ  የሌላቸው ስደተኞች  እንደ አሚጎስ ባሉደጋግና ጃፓናውያን የሚመራ  ቡድን ሁል ጊዜ እንዲደገፉ አስገድዷቸዋል። እ.ኤ. አ በ2018 እና 2021 መካከልባሉት ጊዜያት የድርጅቱ ዓመታዊ ወጪዎች ከ12 እጥፍ በላይ መጨመሩን ተናግረዋል።  ባለፈው  አመት ወደ 200,000 ዶላር የሚጠጋ ወጪ  ድርጅቱ ያወጣ ሲሆን ግማሹ ያህሉ ለስደተኞቹ  ህክምና ወጪ የዋለ  ነበር።

ናጋሳዋ ያለ ገንዘብ ኑሯቸውን የሚገፉና የሚታገሉ ከጤና አጠባበቅ ስርዓቱ የተገለሉ ብዙ ሰዎች አሉ።  '' ይሉናል።''ብዙዎች ካንሰርና ስኳር በሽታን ጨምሮ ከከባድ በሽታዎች ጋር በጭንቀት የተነሳ የተጠቁ  ነው።'' ብለዋል።

መሐመድ የልብ መቆራረጥን ሊያስከትል የሚችል  ከአተነፋፈሳችን ውጭ የሆነ ያልተለመደ የልብ ምት (arrhythmia) እንዳለበት ታወቋል።  በሳይታማ  ህብረት ስራ ሆስፒታል ዶክተር ኢናባ ኦሳሙ ታዳጊው ወጣት የቀዶ ጥገና ያስፈልገዋል ብለዋል።

 የቀዶ ጥገናው  ዋጋ

 ይሁን እንጂ የመሐመድ አባት ባይራም ለቀዶ ጥገናው መክፈል አልቻለም።  22,000 ዶላር አስቀድሞ ማቅረብ እንዳለበት ተነግሮታል።  ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቤይራም ከአምስት ሆስፒታሎች ጋር ለልጁ ሲወያዩለት ቆይተዋል።  እሱ የጃፓን ብሔራዊ የጤና መድህን አካል ከሆነ፣ ከኪሱ የሚወጣው ወጪ  ከ400-800 ዶላር ብቻ ይሆናል።ግን የመኖሪያ ፍቃድ ስለሌለው የጤና መድህን ዋስትና  የለውም።

 እስከዚያው ድረስ መሐመድ የሚጥል በሽታን ለማከም የሚረዳ በሐኪም የታዘዘ መድሃኒት ይወስዳል  ለ 10 ክኒኖች 25 ዶላር ያስወጠዋል ይህም በአሚጎስ የሚከፈል ነው።

 ናጋሳዋ እንዳሉት በጃፓን የሚገኙ ብዙ ሆስፒታሎች ያልተጠበቀ የጤና ሁኔታ ሲያጋጥም ሆስፒታሎችን ከባሎኒንግ ወጪዎች ለመጠበቅ ለውጭ አገር ዜጎች ከፍተኛ የህክምና ክፍያዎችን እንዲከፍሉ ያስደርጋሉ ወይም ያዘጋጃሉ በአንዳንድ አጋጣሚዎች ታካሚው  መክፈል ከሚኖርበት በሦስት እጥፍ እንዲከፍሉ ይደረጋል።ይህም ክፍያው  እስከ 300%  ማስከፈል  የተለመደ  ነውይህም በጣም የሚያሳዝን መሆኑን ነው  ናጋሳዋ  የሚገልፁት።

 ይህ ማለት ኢንሹራንስ የሌላቸው  የውጭ  ሀገር ዜጎች ብዙ ጊዜ ሳይታዩ ወደ ህክምና ቦታ እየሄዱ ይታከማሉ ማለት ነው።  ናጋሳዋ "ለቀላል ጉንፋን ዶክተርን መጎብኘት ከኪስ ውስጥ  25 ዶላር ያወጣል" ይላ ። '' ነገር ግን ገቢ የሌለው ኢንሹራንስ የሌለው የውጭ  ሀገር ዜጋ ለተመሳሳይ ምክርና ህክምና እስከ 250 ዶላር እንዲከፈል ይደረጋል።''  በማለት  ተናግረዋል::

 ከቱርክ ለመሰደድ ተገደደ

ቤይራም  ሚስቱ ዩክሴልና አራቱ ልጆቻቸው ጥገኝነት ጠያቂዎች ናቸው።  ቤተሰቡ ጃፓን የገባው  ከአምስት ዓመት በፊት ነው።  ቱርክን ለቀው  ለመሰደድ እንደተገደዱ ተናግሯልስደት ደርሶብኛል፣ ወላጆቼ ስደት ደርሶባቸዋል። ልጆች ከወለድኩ ነገሮች ይሻሻላሉ ብዬ አስቤ ነበር። ነገር ግን ትምህርት ቤት እየተማሩ እያሉ እናንተ ኩርዶች ናችሁ።” እያሉ እንደሚናገሯቸውና  ''እናትተ አሸባሪዎች ናችሁ። ከአጠገባችን አትቀመጡ። ስለሚሏቸው ፈርተን ማምለጥ ስለነበረብን አምልጠን ጃፓን መጣን  ''  ይላሉ።

 ቤይራም መጀመሪያ ላይ ለስደተኛነት  ሲያመለክ የነበረው የስድስት ወር ጊዜያዊ ቪዛ ይሰጠው ነበር።  በዚህም  በግንባታ ቦታዎች ላይ ሥራ አገኝቶ መሥራት ጀመረ

ባለፈው  ዓመት፣ ቤተሰቡ አዲስ አባል የሆነውን ህፃን ሃሰንን ተቀብሏል።  መሐመድ አሁን በሶስተኛ ዓመቱ በአካባቢው ጁኒየር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ሲሆን ጃፓንኛ አቀላጥፎ ያውቃል።  ነገር ግን በልቡ ሕመም ምክንያት የአካል ማጎልመሻ  ትምህርት በሚሰጥበት ጊዜ መቆም  አለበት

 የቤራም የስደተኛ ማመልከቻ ሶስት ጊዜ ውድቅ የተደረገ ሲሆን እሱና ቤተሰቡ ጊዜያዊ ቪዛ አጥተዋል።  ወደ ቱርክ እንዲመለሱ ቢታዘዙም ለመሄድ ፍቃደኞች  አይደሉም 

ሕይወት በሊምቦ ውስጥ

 ''የመኖሪያ ፈቃድ ማጣት የኑሮ መሰረትን ያበላሻል።''  ይላል ባይራም "የስራ እድልህን ታጣለህ ሆስፒታሎችንዶክተሮችንና የባንክ አገልግሎትን ታጣለህቤት ውስጥ ተቀምጬ ትሆናለክ።ግሬንና እጄን ታስሬያለሁ ቤተሰቤን መንከባከብ አልችልም ልጆቼ እንኳን ወደ ውጭ መሄድ ያስፈራቸዋል" በማለት ይገልጻል።

የመኖሪያ ካርድ ወይም የዛሪዩ ካርድ በጃፓን ውስጥ በህጋዊ መንገድ ለሚኖር  የሚሰጥ ነው።ስለዚህ የመኖሪያ ፍቃድ ሲኖር በማንኛውም ጊዜ መታወቂያውን ከክፍለከተማ ወይም ከኪያክሾ መወሰድ እንዳለበት ኢሚግሬሽኑ ይገልጻል ።  የአንድ ሰው  ቪዛ ካልታደሰ ክፍለከተማ ወይም ኪያክሾ መታወቂያውን ለማሳደስ ከመሄዱ በፊት መታወቂያውን የተቀበሉት፣ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ካርዱን ይበሱታል ።

 ይህ ሁኔታ ደግሞ  በርካታ በጃፓን የሚኖሩ የውጭ ሀገር ስደተኞችን በፍረሀትና በድብቅ እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል።

በመድ ላይ የቤተሰቡ ሁኔታ የበለጠ ጫና አሳድሯልልቤ እንዳይጎዳ እየተንከባከብኩ ነው” በማለት ለቤተሰቡ ሸክም መሆን ስለማይፈልግ ወደ ሆስፒታል ላለመሄድ  ታዳጊው ወጣት  እንደሚጥር ተናግሯል።

በጃፓን ውስጥ የሚኖሩ የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸው  የውጭ  ሀገር ተወላጆች ከ75,000 በላይ ናቸው። የውጭ ሀገር ዜጎች የሕክምና ፍላጎቶችን ለማሟላት ምንም ዓይነት ኦፊሴላዊ ስርዓት የለምየኢሚግሬሽን ባለሥልጣኖች  ለሀገሪቱ ሕዝብ ደህንነት ሲባል ለስደተኝነት ብቁ እንዳልሆኑና  በዚሁ ምክንያትም  አገሪቱን ለቀው መውጣት እንዳለባቸው  ይናገራሉ

 የጤና፣ የሰራተኛና ደህንነት ሚኒስቴርም ቢሆን  ለሆስፒታሎች  የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸው  ስደተኞች እንዳይታከሙ  ውሳኔ አስተላልፏል።  ይህም እንደ መሐመድና ቤተሰቡ ያሉ ሰዎችን በጭንቀት ውስጥ እንዲቆዩ ያደርጋል።

በሳይታማ ኅብረት ሥራ ሆስፒታል የጉዳይ ሠራተኛ ኃላፊ  የሆኑት ታክሞቶ ኮዞ ኢንሹራንስ ሌላቸው የውጭ አገር ዜጎች በመገናኘት በኩል ጥረት ሲያደርግ ቆይተዋ

 ርካሽ የሕክምና አገልግሎት

 በሚያዝያ ወር ናጋሳዋ ነፃ ወይም ዝቅተኛ ዋጋ ያለው የህክምና አገልግሎት ከሚሰጡ ሁለት ሆስፒታሎች መካከል አንዱ የሆነውን ሳይታማ የህብረት ስራ ሆስፒታል ቤይራምን አስተዋውቀውታል።  ሆስፒታሉ የተቋቋመው በመንግስት የተፈጠረው ለጃፓናውያን የጤና ጥቅማጥቅሞችን ለጊዜው ላጡ የሚረዳ ቢሆንም በአጋጣሚ ለውጭ ሀገር ዜጎች ጠቃሚ ሆኗል።  ሆስፒታሉ መን ብቁ ሆኖ ካገኘው የህክምና ወጪውን በከፊል  ሊሸፍንለት ፍቃደኞች  ናቸው 

 ሆስፒታሉ የሚገኘው  በካዋጉቺ ውስጥ ነው 2,000 የሚገመቱ የቱርክ ኩርዶችን ጨምሮ ብዙ የውጭ ማህበረሰብ ያለበት ከተማ  ነው ።  ብዙዎች  ኢንሹራንስ የላቸውም።  ርካሽ የሕክምና አገልግሎቶችን ይሰጣሉ። ነገር ግን ከመንግስት ምንም አይነት ድጎማ አይቀበልም ። ሙሉውን ወጪ ይሸፍናል  ስለዚህ ኢንሹራንስ የሌላቸው የውጭ አገር ታካሚዎችን ለመቀበል የተደረገው ውሳኔ ግን ለማስከፈል ውድ ነው እ.ኤ.አ. በ2020 ብቻ ሆስፒታሉ ለ81 ታካሚዎች በድምሩ 82,000 ዶላር ያልተከፈለ የህክምና ክፍያ ዕዳ  አለበት ።  "አንድን ታካሚ  ከህክምና ወጪያቸው ሁሉ ነፃ ማድረግ ለኛ የማይቻል ነገር ነው" ሲል በመሐመድ ላይ ጉዳዩን ወይም ዙን ሲያጠና  የነበረው  ታኬሞቶ ኮዞ ገልጿል።  ''ለሚያስፈልገው  ሰው ሁሉ የህክምና አገልግሎትን የሚያረጋግጥ ህዝባዊ አሰራር መኖር አለበት '' ይላል።

 ውሎ  አድሮ ሆስፒታሉ መሐመድን  ለዕለታዊ  የህክምና አገልግሎት በዝቅተኛ ወጪ  ለማከም መርሃ ግብሩ ተቀብሎታል ነገር ግን የሚፈልገውን የቀዶ ጥገና አይነት ማከናወን አልቻለም

 ተስፋ ማጣት

የመሐመድ ቤተሰብ ሌላ እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ገጥሞታል።  ሁለቱም ወላጆች ከሀገር ለመውጣት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በማንኛውም ጊዜ በኢሚግሬሽን ባለስልጣናት የመታሰራቸው  እድል የሰፋ ነው ።  በጃፓን የተወለደው ልጃቸው ሀሰን 16 አመት እስኪሞላው ድረስ ቪዛ  ያለው ብቸኛው  ልጅ መሆን ይችል ነበር ።ነገር ግን በዚያኑ  ቀን ቪዛው ተሰርዟል።እሱም የመኖሪያ ቪዛውን እንዲያጣ ተደርጓል ቤይራም መለመን ቀጠልኩ።  ነገር ግን ወደ አገራችሁ  እንመልሳችኋለን አሉኝ፡ ​​የሆስፒታል ሰነዶቻችንን ላሳያቸው  ሞከርኩ ነገር ግን የሆስፒታል ማስረጃውን  ማየት አፈልግም '' አሉ።

 በአሚጎስ ኦሳዋ ዩማ መሪነት የተካሄደው ጥናት የውጭ ሀገር  ዜጎች የመኖሪያ ሁኔታን በተመለከተ ድንቅ መረጃዎችን አውጥቷል ።  84 በመቶ የሚሆኑ ምላሽ ሰጪዎች በገንዘብ ነክ ምክንያቶች የህክምና ምርመራ ማድረግ እንዳልቻሉ ተናግረዋል ።

 ናጋሳዋ ስለጉዳዩ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እየሰ ነው።  በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ ድርጅታቸው 450 ኢንሹራንስ የሌላቸውን የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ የተደረገውን ጥናት ይፋ ለማድረግ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው  ነበር።  እጅግ  በጣም ብዙ የሆኑት 90 በመቶው የሆኑ  መኖሪያ ፍቃድ የሌላቸው የውጭ ሀገር  ተወላጆች የኑሮ ሁኔታቸው "በጣም አስቸጋሪ" ወይም "ህመም ወይም ችግር  የበዛበት ነው " ብለው ገልጸዋል

 ተመሳሳይ አሀዝ እንደሚጠቁመው  የገንዘብ ችግር ያለባቸውና ወደ ህክምና ተቋም እንዳይሄዱ ያደረጋቸው ሲሆን 79 በመቶ ያህሉ ደግሞ ለመታከም አቅም የሌላቸው ነባር ህመምና ጉዳት አለባቸው ብለዋል።

በሰኔ ወር በአሚጎስ በኦታ፣ ጉንማ ግዛት ውስጥ የተደራጀ ነፃ የህክምና ምክር ክፍለ ጊዜ አለ

 ሁኔታውን ለመቅረፍ አሚጎስ በዚህ ሰኔ ወር በኦታ ፣ ጉንማ ግዛት ውስጥ ለተቸገሩ የውጭ ዜጎች ነፃ የህክምና ምክር ዝግጅት አዘጋጅቷል።  በወቅቱ ድንገተኛ አደጋ ተከስተ።አንዲት ናይጄሪያዊ ሴት የልብ ሕመምተኛ በድንገት ራሷን ስታ ወደቀችነገር ግን ዶክተሮች ለእሷ ሆስፒታል እንድታገኝ ለማድረግ  ታግለዋል  በዚያ ቀን በዙሪያዋ  የነበሩ የውጭ ሀገር ተውላጆች የሆኑ ሰባ (70) የሚያህሉ ሰዎች ለመመርመር ይጠባበቁ ነበር።  አንዳቸውም ግን የሕክምና ኢንሹራንስ አልነበራቸውም።

 የማህበረሰብ  ድጋፍ

 የጃፓን መንግስት የመኖሪያ ፍቃዳቸውን ውድቅ ቢያደርጉም መሐመድና ቤተሰቦቻቸውን በአካባቢያቸው የሚገኘው ማህበረሰብ እርዳታና እገዛ እያደረገላቸው ነው ።  በየምሽቱ ማለት ይቻላል መሐመድና እናቱ ቤት ያበስሏትን ምግብ ከመንገዱ ማዶ ያለው አከራያቸው ወደ  ቤታቸው  ይወስዱሏቸዋል።  የ79 አመቱ አንዶ ኬኒቺ ቤተሰቡ ከኪራይ ነፃ ሆኖ እንዲቆይ ፈቅደውሏቸዋል

 

በካዋጉቺ ከተማ አነስተኛ የቤት ጥገና ንግድ ያለው አንዶ ኬኒቺ "ባይራምና እኔ የጉልበት ሠራተኞች ነን። እንረዳዳለን" ብሏል።

 አንዶ ቤይራምን በህንፃ ጥገና ስራው በወቅቱ ይቀጥራል።  አንዶ እንዳለው  የጀርባ ጉዳት  ስላለበት ብዙ መስራት አልቻለም ይሁንና  የራሱን ሥራ ሳይደናቅፍ ባይራም አነስተኛውን ኩባንያውን ታድጎ አዳነው  ከዛ  በኋላ ጥንዶቹ ጓደኛሞች  ሆኑ።

ቤይራም ከሁለት አመት በፊት በአንዱ የአንዶ ጣብያ ላይ የጣራ ጥገና  የሰራ ነበር።

 አንዶ የእጅ ሥራ ለመሥራት ፈቃደኛ የሆኑ ጃፓናውያን ማግኘት አስቸጋሪ እንደሆነ ተናግሯል።  ብዙ ትናንሽ ድርጅቶች የውጭ ዜጎችን ብቻ መቅጠር ይችላሉ።  ባይራም ቪዛውን ሲያጣ  ግን አንዶ ሥራውን ለማቆም  ተገደደ።

 "እኔ ትልቅ ችግር ውስጥ ገብቻለሁ። እናም  ሁኔታው ​እንደ እኔ ላለ አዛውንት በጣም ተስፋ አስቆራጭ ነው ። ከጃፓኖች የበለጠ የሚሰሩትን ጥሩ ሰዎችን ካልተንከባከብንና  የመኖሪያ ፍቃድ እንዲያገኙ ካላደረግን በመጨረሻ ላይ የምንጎዳው እኛ ጃፓኖች ነን ብዬ አስባለሁ ።  እነዚያ የኢሚግሬሽን ወይም የፍትህ ሚኒስቴር የነጩ ​​የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ምን ያህል እነሱን እንደምንፈልጋቸው የሚገነዘቡት አይመስለኝም” ይላሉ  አንዶ።

 ከኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ጋር በመቅረብ አንዶ የቤይራም ዋስ ለመሆን  ይፈልጋሉ። ቤተሰብን ለመደገፍ በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎችን ፊርማዎችን ለመሰብሰብ  እያሰበ ነው።

 ማንነቱ ያልታወቀ በጎ አድራጊ

 በሳይታማ የህብረት ስራ ሆስፒታል ኬዝ ሰራተኛ ታኬሞቶ እና ሌሎች ሰራተኞች እንደ መሐመድ ካሉ ጉዳዮች ጋር ከተገናኙ በኋላ ለውጥ ለማድረግ እየሞከሩ ነው።  የተሻለ እንክብካቤ ለመስጠት ከኩርድ ማህበረሰብ ቡድኖች ጋር  ድጋፍ ለማድረግ ውይይት እየተካሄደ ነው።

 ታክሞቶ የሆስፒታሉ ሰራተኞች እውቀትና ግንዛቤ ማነስ ብዙ ነው። ኢንሹራንስ የሌላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች መፍትሄ ሲያገኙ እንዲባረሩ ምክንያት እንደሆነ ይሰማዋል።  ጉዳዮቹን ለመረዳት በህክምና ባለሙያዎች ዳሰሳ ላይ እየሰራ ነው።

 ለመሐመድ  ቢያንስ ወደ ልቡ ህክምና ሁኔታ እንዲመጣ ለማድረግ  መልካም ፍፃሜ ለመድረስ ያለ ይመስላል።  ያልጠበቀው እና ማንነቱ ያልታወቀ በጎ አድራጊ አሁን ረድቶታል።  በሰኔ ወር የናጋሳዋ ድርጅት በውስጡ ከ3,700 ዶላር በላይ የያዘ ፖስታ ተቀብሏል።  ማንነቱ ያልታወቀ ማስታወሻ ገንዘቡ ለመሐመድ ህክምና የሚውል መሆኑን ገልጿል። ናጋሳዋ እንደሚለው ማንነቱ ያልታወቀ ሰው ላከልን። እርዳታውን ላደረገው ሰው በእውነት ማመስገን አለብን።
 "ልክ እንዚህ በዚህ ተራ ፖስታ ውስጥ! ነው  የተላከው "  ይላል ናጋሳዋ።  ወዲያውኑ ወደ ታኬሞቶ ደረሰ። እሱም በምላሹ ቀዶ ጥገናውን ለማድረግ ሆስፒታል ማግኘቱን ነገረው።

 "ልቤ እንደገና እንደማይጎዳ በመስማቴ በጣም ደስ ብሎኛል" ይላል መሐመድ።  አሁን የበለጠ ንቁ ህይወት እንዲኖረኝ እየጠበኩ ነው.  "የምፈልገውን ስፖርት ለመስራት እችላለሁ."

 ቤይራምና መሐመድ  ምሥራቹን ከሰሙ በኋላ ከቤተሰባቸው ጋር በአንድ መናፈሻ ውስጥ እሁድን ሲዝናኑ በደስታ አሳልፈዋል።

 ባራም ተጨናንቋል።  ልጁ ዕድለኛ እንደሆነ ያውቃል።ግን በተመሳሳይ ሁኔታ ዋናው ችግር የመኖሪያ  ፍቃድ አለመኖር እንዳለ ይጨነቃል።

 “የውጭ ሀገር ዜጎች ቪዛና ኢንሹራንስ ያስፈልጋቸዋል።  እነዚህ የመኖር መሰረታዊ መብቶች ናቸው። ሁሉም ሰው በጃፓን የሚኖር  ሰው ያስፈልገዋል። የስደተኞች መሰረታዊ መብቶችን አለማወቅ ስደተኛ እንዲሰቃዩና አልፎ ተርፎም  በመኖሪያ ፍቃድ ሳቢያ  <