የፕሪቶሪያ የሰላም ውይይትና የጦርነቱ ሁኔታ


ከወሰንሰገድ መርሻ ደምሴ

(ደራሲ፣ጋዜጠኛና ማህበራዊ ሀያሲ)

 

 በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስትና በትግራይ ክልል አማፂያን  መካከል የተካሄደው የሰላም ድርድር ባለፈው ማክሰኞ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ተጀመ ውይይቱ  ዛሬና እሁድም  ቀጥሎ ይውላል 

ጦርነቱን ማቆም በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ከፍተኛ ውይይት እየተደረገ ነው

 

ይሁንና እስከ ዛሬ  ድረስ ጋዜጠኞች ከቦታው አጥር ውጭ እንዲቆዩ በማድረግ የመገናኛ ብዙሃን ስለውይይቱ እንዳይዘግቡ  ተደርጓል

 

የሚዲያ ማፈኛዎች   በርካታ አውሎ ነፋሶች በዓለማችን ላይ አሉ ከነዚህ መካከል ጋዜጠኛን ማሰርና በክስ ማንገላታት ይገኝበታል።ሌላው  ጋዜጠኛውን በጥይት መምታትም አለ።በቅርቡ በፊሊፔንሲ ጋዜጠኛ ላይ ኬንያ ውስጥ  በኬንያ ወታደሮች በጥይት እሩምታ  በተተኮሰ ጥይት  መሞቱ ተሰምቷል።  ኬንያኖች በስህተት በተተኮሰ ጥይት ነው  የሞተው  ሲል ሁኔታውን አስተባብለዋል።ያም ሆነ ይህ ግን በጣም ብዙ የፖሊስ ግድያዎች በነፃ ጋዜጠኞች ላይ ተመልክተናል። ፕሬስን አፋኝ የሆኑ ሀገሮች ጋዜጠኞች ማሰርና ማንገላታት ብቻ ሳይሆን ጋዜጠኞች የሞቱባቸው ሀገራት አሉ እንደው  ለመጥራት ያህል ካናዳ፣ ሜክሲኮ፣ ኩባ፣ ሄይቲ፣ ብራዚል፣ አውስትራሊያ፣ አፍጋኒስታን፣ ካዛኪስታን፣ ሰሜን ኮሪያ፣ ምያንማር፣ ፊሊፒንስ፣ ሲሪላንካ፣ ቻይና፣ ሆንግ ኮንግ፣ ህንድ፣ ካሽሚር፣ ፓኪስታን፣ እስራኤል፣ ፍልስጤም፣ ሊባኖስ፣ ማሊ፣ ኢትዮጵያ፣ ቱኒዚያ  አልጄሪያ፣ ፈረንሳይ፣ ሃንጋሪ፣ ቤላሩስ፣ ሞልዶቫ፣ ሩሲያ እና ዩክሬን የሚጠቀሱ  ናቸው።

 

ስለኢትዮጵያ የሰላም ውይይት ለሚዲያ ክፍት ያልሆነውም  በአፍሪካ ብሎ  በሀገሪቱ ላይ የሚዲያ አፋኝ ስርዓት ጭምር ስላለ ነው።

 

 የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ሃላፊ ፊሊፖ ግራንዲ በናይሮቢ ኬንያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በጎርጎሮሳውያኑ ጥቅምት 25 ቀን 2022 የኢትዮጵያን የትግራይ ግጭት ለማስቆም ስለሰላም አስፈላጊነት  ተናግረዋል።  

 

 በኢትዮጵያ ጦርና በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክልል  በሚገኙት የትግራይ ክልል ሃይሎች መካከል ለሁለት አመታት የዘለቀውን ጦርነት ለማስቆም ያለመ የመጀመሪያው መደበኛ የሰላም  ድርድር ማክሰኞ እለት በደቡብ አፍሪካ ተጀምሮ ነገ እሁድ እንደሚጠናቀቅ የደቡብ አፍሪካ መንግስት አስታወቋል

 

 በሕዝብ ብዛት በአፍሪካ ሁለተኛ ደረጃ ላይ በምትገኘው ኢትዮጵያ ያለው የእርስ በርስ ጦርነት ሰፊውን የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ አለመረጋጋት  እንዲፈጠር አድርጎታል። በሺዎች የሚቆጠሩትን  ሰዎች እንዲሞቱ  ያደረገ ሲሆን፣ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን  ፈናቅሏል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩትን ደግሞ በረሃብ አለንጋ እንዲገረፉ ያደረገውን ይህ ግጭት  ለማስቆም የደቡብ አፍሪካው ድርድሩ ከፍተኛ አስተዋጾ አለው 

 

 በአፍሪካ ህብረት ሸምጋይነት የተካሄደው ይህ ድርድር የተጀመረው መንግስት ባለፈው ሳምንት በርካታ የትግራይ ትላልቅ ከተሞችን በመቆጣጠር በትግሉ ሜዳ ከፍተኛ እመርታ እያስመዘገበ  እያለ  መሆኑን እየገለፀ  ባለበት ወቅት ነው

 

ከጎረቤት ኤርትራ ከመጡ  አጋር ወታደሮች ጋር በመሆን  በጥምረት የተካሄደው የመንግስት ጥቃት፣ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ስጋት ፈጥሯል፣ የአፍሪካ፣ የአሜሪካና የአውሮፓ መሪዎች እንዲሁም  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ተዋጊ ወገኖች የተኩስ አቁም አድርገው አስቸኳይ ድርድር እንዲያደርጉም  ከድርድሩ በፊት  ጠይቀው  ነበር ።

 

 "ወታደራዊ መፍትሄ የለም"

 

 የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ድርድሩን በደስታ ተቀብለው  በሰጡት መግለጫ ።

 

 "ለዚህ ግጭት ምንም አይነት ወታደራዊ መፍትሄ የለም ፤ ​​እነዚህ ንግግሮች ለመላው ኢትዮጵያውያን ዘላቂ ሰላምና ብልጽግና ለማምጣት እጅግ ተስፋ ሰጪ  መንገድን ያመጣሉ" ብለዋል።

 

 የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት የሂደቱን መጀመር በደስታ ተቀብለዋል።

 

ፓርቲዎች ለሰላም ያሳዩት ቁርጠኝነት ቀደም ብለው በማሳየታቸው አበረታታቸዋለው ” ነው  ያሉት 

 

 በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የሰብአዊ ርዳታ ፈላጊዎችን ያስከተለውን ጦርነት ለማቆምና እንደ አሜሪካ ግምት በግማሽ ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎችን ለሞት የሚዳርግ ጦርነት ለማቆም ዲፕሎማሲያዊ ጫና መፍጠር  አስፈላጊ  ነው

 

 ውይይቱ በመካሄድ ላይ ያለው የፌደራል ሃይሎችና አጋሮቻቸው  ከኤርትራ ጦር ጋር በመሆን የበላይ ሆነው እየታዩ ባለበትና በትግራይ የሚገኙ ስትራቴጂካዊቷን የሽሬ ከተማን ጨምሮ በርካታ ከተሞችን በያዙበት ወቅት  ነው።

 

 ስድስት ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርባት ትግራይ - በአብዛኛው መገናኛ ዘዴዎች ስለተቋረጠ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ መድረስ በጣም የተገደበ በመሆኑ የጦር ሜዳ ለውጦችን ማረጋገጥ  አይቻልም።

 

 በያዝነው ወር መጀመሪያ የአፍሪካ ህብረት ሁለቱን ወገኖች ወደ ድርድር ለማድረስ ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል፤ ዲፕሎማቶች የሎጂስቲክስ ጉዳዮች  ዝግጁ አለመሆን ለውይይቱ መደናቀፍ  ተጠያቂ  አድርገዋል

 

 አንድ የምዕራቡ ባለስልጣን በዩናይትድ ስቴትስ የተደራጁ ሚስጥራዊ  ግንኙነቶች በሲሼልስና በጅቡቲ ሁለት ጊዜ ተካሂደዋል ብለዋል ።

 

 የፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ቃል አቀባይ ቪንሴንት ማግዌንያ ከድርድሩ በፊት እንዳሉት ደቡብ አፍሪካ "ውይይቱ ገንቢ በሆነ መንገድ እንዲቀጥል  ለመላው  እህት ሀገር ለሆነችው ለኢትዮጵያ ህዝቦች ዘላቂ ሰላም የሚያመጣ ስኬታማ ውጤት እንደሚያስገኝ ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል።

የአፍሪካ ህብረት የሽምግልና ቡድን የተመራው በቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታና የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ፉምዚል ምላምቦ-ንጉካ በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ ነው።

 

 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ና የዩናይትድ ስቴትስ ተወካዮች በታዛቢነት  በድርድሩ  ወቅት መሳተፋቸውን የአፍሪካ  ህብረት ገልጿል

 

በተለይም የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር የምስራቅ አፍሪካ ኢጋድ ዋና ፀሃፊና የቀድሞ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካይ በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል

 

 ምንም እንኳን እነዚህ በይፋ የታወጁ የመጀመሪያ ንግግሮች ቢሆኑም፣ ቀደም ሲል በሲሸልስ እና በጅቡቲ ሚስጥራዊ ግንኙነቶች  ይደረጉ እንደነበር የምዕራቡ ምንጮች ይገልጻሉል።

 

 የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ በኬንያ ናይሮቢ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ " ድርድሩ በፕሪቶሪያ የሚካሄደውን ድርድር  በጉጉት እየተመለከትነው  ነበር ። ይህ ብቸኛው  የሰላም መንገድ ነው" ብለዋል።  "ፓርቲዎቹ በድርድር መፍትሄ ላይ ትርጉም ባለው መልኩ ካልተሳተፉ እኛ ለዘላለም በዚህ ሁኔታ ውስጥ  ልንቀጥል  እንችላለን።" ሲሉ ተናግረዋል።

 

 "ሰው  ሰራሽ ረሃብ"

 

 ግጭቱ የመነጨው  ህዝባዊ ወያ ሓርነት ትግራይ (ህወሀት) የተባለው  የአማፂ ንቅናቄ የሀገሪቱ  ዋንኛ ፖለቲካ ፓርቲ  በመሆን እስከ ጎርጎሮሳውያኑ  2018 ከቆየ በኋላ የኢትዮጵያን ገዢ ፓርቲን  ኢህአዲግን በዋንኛነት በመምራት ለሦስት አስርት አመታት ከመራበት ወንበሩ በመፈናቀሉ የተነሳ በነበረው  ቅሬታ ነበር ወደ ጦርነቱ  ለመግባት  የቻለው

 

በአገር አቀፍ ደረጃ ሥልጣኑን ህወሓት ካጣ በኋላ በሰሜን ክልሉ ምሽጎ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሚመራው የፌዴራል መንግሥት ጋር ፍጥጫ  ውስጥ  ለመግባት በቃ

 

 ''መንግስት ህወሀትን ብሄራዊ የበላይነቱን በጉልበት ለማስመለስ እየፈለገ ነው።'' ሲል ህወሓት በበኩሉ ''መንግስት የትግራይ ተወላጆችን መጨቆንና ስልጣንን ከሚገባው በላይ ተጠቅሞ የክልሉን ህዝብ እየጨቆነ ነው ''  ሲል ሁኔታውን ያስተባብላል

 

 የትግራይ ልዑካን ቡድን በደቡብ አፍሪካ በተደረገው ውይይት ትኩረቱን ያደረገው ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም፣ ያለገደብ ወደ ትግራይ ሰብአዊ ርዳታ መድረስና የኤርትራ ኃይሎች ከስፍራው እንዲወጡ የሚሉ  ይገኙባቸዋል  

 

 መንግስት ውይይቱን ግጭቱን ለመፍታትና "በመሬት ላይ ያለውን የሰላም ሁኔታ ይበልጥ እንዲሻሻል በማድረግ የእርዳታው ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲደርስ ለማድረግ " እንደሚፈልግና  የሰላሙ ድርድር ለዚህ መልካም አጋጣሚ እንደሆነ ገልጿል።

 

 ጦርነቱ በኢትዮጵያ የተከሰተውን ድርቅ ጨምሮ ሌሎች አሳሳቢ ችግሮችም በሀገሪቱ  ውስጥ  ረሃብን አባብሶታል - በአራት አስርት ዓመታት ውስጥ  የከፋው - የምግብ ቀውስ  በሀገሪቱ ላይ አስከትሏል ።የሀገሪቱን  ኢኮኖሚውንም  ጎድቷል

 

 ባለፈው  ማክሰኞ ትግራይ ተወላጅ የሆኑትና በኢትዮጵያ መንግስት ውስጥ  በሚኒስትርነት ማዕረግ ያገለገሉት የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ የሆኑት ቴዎድሮስ አድሃኖም  ገብረእየሱስ  በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት እየወሰደ ባለው  እርምጃ ተከታታይ ትችት ሲሰነዝሩ  ቆይተዋል

"በኢትዮጵያ #ትግራይ ውስጥ በተካሄደው ከበባ ምክንያት ባለፉት 2 ዓመታት ብዙ ሰዎች በረሃብ፣ በተለይም ሰው ሰራሽ በሆነ ረሃብና አስፈላጊ የሆነ የመድሐኒትና የጤና አገልግሎት እጦት በርካታ ትግራውያን ሞተዋል" ሲ ቴዎድሮስ በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል

 

 የኢትዮጵያ መንግስት ግን  ወደ ትግራይ እርዳታዎች እንዳይገቡ መንግሥት እየከለከ ነው በሚል ከሰብአዊ ድርጅቶች የቀረበበትን ውንጀላ አስተባብሏል። እንዲያውም ዶክተር ቴድሮስ ለትግራይ ሃይሎች የጦር መሳሪያና ዲፕሎማሲያዊ  ድጋፍ እንዲያገኙ እየሞከሩ  ነው  ሲል  ከሷል

 

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ ወደ ትግራይ ሰብዓዊ አገልግሎት እንዲሰጡና የኤርትራ ጦር ኃይሎች ከትግራይ ለቀው እንዲወጡ  ጥሪ ሲያደርግ ቆይቷል።

 

 አምነስቲ ኢንተርናሽናል እያንዳንዱ  አካል በሰብአዊነት ላይ ወንጀል ፈጽሟል ሲል  ምርመራ እንዲካሄድ ያለፈው ረቡዕ  በሰጠው  መግለጫ  ተናግረዋል ።

 

 "የሰብአዊ መብት ረገጣ በሰነድ  የተደገፈ...

(ያጠቃልላል) አስገድዶ መድፈር፣ ጾታዊ ጥቃት፣ (...) ዘረፋ፣ ማሰቃየት እና ከህግ አግባብ ግድያ" በኢትዮጵያና ኤርትራ ተወላጆች ተፈፅሟል  ።በማለት የአምነስቲ ባለሙያ የሆኑት አቶ ፍስሃ ተክሌ ተናግረዋል።

 

 በናይሮቢ  በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ  ሁሉም ወገኖች፣ ትግራዋያን፣ አማሮች፣ ኤርትራዊያን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጽመዋል።''  ብለዋል።

 

 በአሁኑ ወቅት የማስረጃ ደረጃው  በቂ ስላልሆነ ብቻ ነው የዘር ማጥፋት ወንጀልን ክስ እያስወገድን ያለነው ” ሲሉም አክለዋል።

 

ድርድ ከሰላም  በላይ ነው

 

 በመንግስትና በትግራይ ታጋዮች መካከል የመጀመሪያው ቀጥተኛ ውይይት መደረጉ የሰብአዊ ደንቦችን ማረጋገጫ ሊያመለክት ይችላል  ተብሏል

 

 ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረችበት ጊዜ አንስቶ፣ የአገሪቱን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ፣ የኃይል አጠቃቀምን ለመገደብና የንጹሐን ሕይወትን ለመጠበቅ በተዘጋጁ ዓለም አቀፍ ሕጎች ላይ ዘላቂ ጉዳት እንደሚያደርስ ታዛቢዎች አሳስበዋል።  እነዚህ ሕጎች አሁን እድሳት የሚያስፈልጋቸው ሲሆን እድሳቱ ሊተገበርበት የሚችለው ሀገር ደግሞ አንዷ  ኢትዮጵያ ነ

 

 ከሁለት አመት የእርስ በርስ ጦርነት በኋላ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስት ተወካዮችና የአመፂው  መሪዎች ስለ ሰላም ለመነጋገር በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የመጀመሪያ ስብሰባውን ማካሄዳቸው ሊያስመሰግናቸው  ይገባል።  በደቡብ አፍሪካ ባለፈው ማክሰኞ  የተከፈተውና በሳምንቱ መጨረሻ ላይ እሁድ  የተጠናቀቀው ይህ የሰላም ድርድር ደካማ ነው  ሊባል አይችልም ። ምክንያቱም  ለሁለት ወራት የተጠናከረውን ውጊያን በማስቆሙ  በኩል ትልቅ ሚና ሊጫወት ይችላል የሚል አመለካከት  አለ። ይሁንና ወደ 3ኛ አመት ሊሞላው በተቃረበው ጦርነት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት በጦርነቱ አልያም በረሃብና በበሽታ መሞታቸው  ተሰምቷል።  የግጭቱ ትኩረት በሆነው በሚሊዮን የሚቆጠሩ የትግራይ ንፁሀን ዜጎች በእገዳና የምግብ  ንዲሁም  የመድኃኒት እጥረት ውስጥ ናቸው።  ከኦገስት መገባደጃ ጀምሮ፣ ለአምስት ወራት የዘለቀው  ሰብአዊ እርቅ ካበቃ በኋላ ምንም አይነት እርዳታ ወደ ክልሉ አልገባም ማለት ይቻላል።

 

 ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ  የኢትዮጵያና ጎረቤት ኤርትራ ታጣቂዎች እራሱን ከሚጠራው የትግራይ  የጦር ኃይል  ጋር ጦርነት ውስጥ  ገብተዋል።  በ ሰላማዊ ዜጎች ደም የረከሰውን ግጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ ማቆም አልተቻለም።ውጊያው  እየጨመረ ከመሄዱም ባሻገር በሀገሪቱ ላይ እየታየ ያለው ጥፋትና የጭካኔ አደጋ ብዙ ኢትዮጵያውያን የውጭ ዜጎች ጦርነቱ በፍጥነት በድርድር ይቆማል የሚል ተስፋ አድርገዋል።  

 

ይሁንና የኢትዮጵያ ጦሯና የኤርትራ አጋሮቻቸው በጦር ሜዳ ፈጣን ስኬት በማግኘታቸው በሰላሙ  ጉዳይ ለመነጋገር የቸኮሉም